Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦12)

“በቀላሉ እማ ገድዬ አልቀብርህም  በቁምህ አስቃይቼ እሄን እልህክን አበርድልሀለሁ። “አሉና ሽጉጡን ታፉ ውስጥ ቲያወጡት መርፌ ወግተው ወደ ሰውነቱ ያንቆረቆሩት ፈሳሽ ምን እንደሆን እንጃ  ታፉ ውስጥ የሚዝለገለግ ነጭ ፈሳሽ እየወጣ እንደቅድሙ ለመጮህ ተሳነው መሰል በለሆሳስ  እያቃሰተ ” ግደይኝ አንቺ አረመኔ ሴትዬ እነዛን ታስር በላይ የሆኑ ሚስኪን ደሀ ሰራተኛችን  አይናቸው እያየ  ያውሬ ሲሳይ እንዳደረግሻቸው ከፊሉን ደሞ ገለሽ በዚህ የሀጥያት አውድማ በሆነ ቤትሽ ቀብረሽ ድንጋይ  እንደጫንሽባቸው እኔንም ግደይኝ ለምን ግዜ ታጠፊያለሽ ግደይኝና ሄደሽ ተኝ  መቸስ  የሰላም እንቅልፍ  አትተኚ እንዳንቺ አይነት ሰው የሰላም እንቅልፍ ተተኛማ  ፈጣሪም  እንደሰው የሀብታም እና  የግፈኛች እንጂ የድሆች አምላክ አይደለማ! ህጅና ተኝተሽ ተህሊናሽ ጋር ትግል ግጠሚ።” ቲላቸው ….”ክክክክክክክ  ስለሰራተኛቹም ታቃለህ ለካ አየህ መርፌው ስራውን ጀመረ ማለት ነው ገና የምታውቀውን ሁሉ እየጎለጎለ ያስለፈልፍልኛል። ስማ እነሱ እኮ ስለተመረጡ ነው የተበሉት እንዳንተ አይነቱን ቆዳው በብርድና በችጋር የዛገ ዘበኛን ግን እንኳን የኔ ዘንዶ ሶስት ቀን ሙሉ ምግብ ያጣ የራበው ጅብ እንኳን ቢያገኘው አይበላውም።

እሄውልህ “አሉና በሽጉጡ ሰደፍ አናቱን ቁልቁል ዶቁሰው “ሰውን ያለ አንድ ጥቅም ገድዬ አላውቅም ገድዬ ከቀበርኩህ እማ  ጠቀምኩህ እንጂ መች ተጎዳህ ገድዬ ልቅበርህ እህህህህህም ሲያምርህ ይቀራል …ስንት አመት የዘበኛ  ደሞዝ እየተባለ ላንተ የወጣሁትን ብር በምን  እንደማወራርድ  ማወቅ ትፈልጋለህ?  ሻንቆ እስኪመጣ ጠብቅ  ነብስህ ሳይወጣ ሆድ እቃህን ዘርግፎ ኩላሊትህን ያወጣልኛል ሌላም ዋጋ የሚያወጣ ያልተጎዳ መቀያየሪያ ውስጥህ ከተገኘ  እሱንም ጨምሮ ይበልትህና  በቆዳ እና ዋጋ በማያወጣው  በድን አካልህ ያስቀርልኛል። ያኔ ካንድም ሁለት ግዜ እንደገደልኩህ ሳቅ ደስ እያለኝ በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ባለ ዶላር ዲታዋች እሸጥና ካወጣሁብህ በላይ  ገቢ አገኝብሀለሁ  ክክክክክ።

እሱንማ  ተጀመሩ ቆዩኮ ጠያቂ የለላቸውን ሰዋች ተሆስፒታል  ምንም የማያውቁ ህፃናትን  ተየመንገዱ እየለቀሙ  የኩላሊት ንግድ  መጀመሮን  የማላውቅ  መሰሎት ይልቅ  አይልፉ  ሰትዬ  እኔ   እንደሁ  ሁለቱም  ኩላሊቴ  ጤነኛም  አይደል  ይልቅ  ተፌቴ  ቆመው ተመለፍለፍ  በያዙት  ሽጉጥ  ይግደሉኝ  ለኔም  የርሶን  ፊት  ተማየት መሞቱ  ይሻለኛል  ”  ቲላቸው   ” ምን እንደሚያዝናናኝ ታውቃለህ  ሰዋች የሚፈሩትን ሞት እንዲህ ልክ  እንዳንተሲናፍቁት ማየት ክክክክክ   ግደሉኝ  እያሉ ሲለምኑ መስማት  ክክክክክክ”

እህን ግዜ መከረኛው  መንዘፍዘፍ  የየለት  ስራ  የሆነበት ሰውነቴ ተላይ  እስተ ታች ይንቀጠቀጥ  ገባ  ..እግዚዬ የሰው ክፋት ፣እግዚዬ የሰው ጭካኔ ፣እግዚዬ የፈጣሪ ትግስት አንተስ ሁሉን ቻይ ሆነህ ታገስህ  ጌታዬ እንደው እኝህን ሰትዬ ተሳክቶልኝ እንኳንስ በወጉ መግደል በጫጭቄ ብበላቸው ተሀጥያት ትቆጥርብኛለህ? “ባለጌን  ተወለደ ፣ የገደለው ይፀድቃል”  አለች እምዬ።

እናንተዬ… አይንና ጆሮዬ  የሚያየውንና የሚሰማውን  አምኖ መቀበል ተሚችለው በላይ  የሆነበት ጭንቅልቴ ሊፈነዳ ደርሶ  ማሰብ ተሳነው መሰል ደነዘዝሁ።  ተድንዛዜዬ ታልወጣ አጎንብሼ ቁልቁል ትመለከት በዛ  ውድቅት  ለሊት ተጀርባዬ  ጅኒ ይሁን ሰይጣን አልያም ሰው ማን እንደሆን  እንጃ   እመቀመጫዬ  ግድም ነካ ነካ ቲያረገኝ እምዬ  ድረሽ አልሁና በድንጋጤ  ተልቤ ውስጥ ቀዝቃዛ ውሃ ፍስስ ያለ መሰለኝ ….

ይቀጥላል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *