ዘንዶው መስኮት የሚያህል አፉን ከፍቶ የተወረወረለትን ሰውዬ መሬት ታይነካ ቀለበው።ተመቅፅበት እስተወገቡ በመዋጥ ሰውየው ነብስ ይዞት ቲታገለው ተግራ ወደ ቀኝ ተቀኝ ወደ ግራ እያላተመ ወደ ውስጥ ያስገባው ዥመር።
ልጅቱ እትዬ ላይ እያፈጠጠይ ጨካኛይ ናችሁ አረመኔዋይ ናችሁ ፈጣሪዬ ለምን ዝም አልህ እባክህ ሀይልህን አሳይ እያለይ ትትጮህ እኔ ተላይ ሆኜ የምይዘው የምጨብጠው ነገር ጠፋይ።ዘንዶው ሰውየውን ቲያጣጥም እትዬ እንደሻማ የረዘመ ሆኖ እንደ እጣን የሚጨስ ነገር ይዘው እስተዛሬ ትኖር ሰምቸው በማላውቀው ቋንቋ እየለፈለፉ ዘንዶው ያለበትን የብረት ፍርግርግ ቤት እየዞሩ ይለፈልፋሉ። ሻንቆ የሚሉት የቀን ጭለማ አሜን አሜን ማለቱ ታይሆን አይቀርም ሁለት እጁን ከፍ አድርጎና አይኖቹን ከድኖ ከንፈሩን ያነቃንቃል።በልሁ እስታሁን መሬት መሬቱን ተማየት ውጪ ቀና አላለም።እትዬ የያዙት ነገር የሚያወጣው ጭስ መጠኑ ብዙ ትለነበር ቤቱ በጭስ ተሞላ።ዘንዶው የተገበረለትን ሚስኪን ውጦ እንደጨረሰ ተዘርግቶ ተኛ።ይህን ግዜ እትዬ የዘንዶውን ቤት መሽከርከራቸውን አቆሙ።ሻንቆ ወደ እትዬ ቀረብ ብሎ ያወራውን እንዣ ተመልሶ ወደ እምትንሰቀሰቀው ልዥ ቀረብ አለና…
ድንጋይ ተመሬት ውስጥ በሚፈነቅል ጎምዛዛ ድምጡ ልዥቱን ማናገር ዥመረ። ሰውየው እንኳን ቀረብ ብሎ ተርቁም ቲያዩት ያስፈራል። እኔማ ታስበው እሄን ሰውዬ ፈጣሪ መዥመሪያ ጉማሬ አርጎ ሊፈጥረው አስቦ ተላይ ዥምሮ ግማሽ ላይ ቲደርስ ሀሳቡን ቀይሮ ታይሆን አይቀርም ተወገቡ በታች ሰው ያደረገው።
ልጅቱን በዛ ሰፌድ በሚያህል እጁ አገጯን ይዞ ቀና አደረገና እንደ ጠጉር ቆራጭ ግራና ቀኝ እያወዛወዘ አፈጠጠባት። “በጣም ቆንጆ ሴት ቆንጆ ነሽ” ቲላት ልዥቷ ፍቷን ተእጁ መሀል ልታስለቅቅ ተፍጨረጨረይ።
“ሃሃሃሃ….” ብሎ ቲስቅ የከፈተው አፉ የዘንዶውን አካፋይ ታያክልም አይቀር።
“ስሚ አይጥ በወጥመድ ከተያዘች ቡሀላ ብትፍጨረጨር በሰላም ከመሞት ይልቅ ተጋግጣ ትሞታለች እንጂ ለውጥ አታመጣም ሃሃሃሃ… ልክ እንደዚህ አጠገብሽ እንዳለው ጅላጅል ዘበኛ ከእትዬ ጋር አፍ መካፈት በሰላም እና ቶሎ ከመሞት ይልቅ ስቃይን ማብዛት ነው ትርፉ ይልቅ ስቃይሽን መቀነስ ከፈለግሽ መፍጨርጨርሽን ተይና የምትባይውን ነገር አደብ ገዝተሽ አድምጪ!!” አለና እዛው ጨምድዶ እንደያዛት ወሬውን ቀጠለ…
“ያቺ ቆንጅየዋ ታናሽ እህትሽ ጋር እንደውላለን ሂወትሽን ማትረፍ ከፈለግሽ የማዝሽን ትነግሪያታለሽ የመጀመሪያው ትዛዝ ከኛ ሰዎች ጋር ተገናኝታ እዛ ቀይና ውብ ፊታ ላይ ንቅሳት ይሰራላታል ከዛ ለ ሶስት ቀን ብቻ ለአንድ ተልእኮ ሰዎቻችን በሚያስቀጥሯት ቤት በሰራተኝነት ትቀጠራለች ከዛ የምትባለውን ሰነድ ሰርቃ ትወጣለች ሃሃሃሃ…ቀላል ነው አደል?” አላት ጨምድዶ የያዘውን የልጅቱን ፊት የኋሊት እያሽቀነጠረ። ልጅቱ ተተወናጨፈችበት ትትመለስ…
“እሄን ሚስኪን ለምን ገደላችሁት ስራ የሌላት ሚስትና ሶስት ልጆች እንዲሁም የሚረዳት በሽተኛ እናት አለችው እኮ ጨካኛች ናችሁ ጨካኛይ አረመኔዋይ” እያለይ በመጮህ ትትንሰቀሰቅ …
“እትጩሂ!” አለና በዛ ሰፌድ በሚያህል እጁ እፊታ ላይ ከደነባት። ሁለት እጃ የታሰረው ሚስኪን ሴት ጥፊውን መቋቋም ትለተሳናት ተሽከርክራ ተመሬት ተደባለቀይ እትዬም ተጣራ በላይ ሳቃቸውን ለቀቁት።እሄን ተማይ ሞቴን ተመኘሁ። ማንሳት ባልችልም የወደቀችውን እህቴን ቁልቁል እያየሁ ተንሰቀሰቅሁ።ፈጣሪዬ እነኝህን ሰዎይ ግን እውነት አንተ ነህ የፈጠርሃቸው እንዲህ አይነት ሰዎይ እንደሚሆኑ ቀድመህ ታውቅ ተነበረ ስለምን እንዲኖሩ ፈቀድህላቸው አልሁ ፍጣሪዬን ሀዘኔ ታቅሜ በላይ ትለሆነብይ።
እወለሉ ላይ ባፍጢማ የተደፋችው ሚስኪን እዛው እንደወደቀይ ዝም ትትል ጎትቶ አነሳት ታአፍንጫዋ ደም ይንዥቀዥቃል ” ስሚ እሱ ቶሎ በሞሞቱ ካንቺ የበለጠ እድለኛ ነው ገባሽ አሁን የተባልሽውን ታደርጊያለሽ? አታደትጊም ?” አለና አንቧረቀባት መልስ ታትሰጠው ቁና ቁና እየተነፈሰይ ሽቅብ ትታየው አንገቷን እነቀና ግድግዳው ላይ ለጠፏት ….
ይቀጥላል