Tidarfelagi.com

ሞቱ በስርአት

ጥሩንባ ተነፋ
ህልፈት ተለፈፈ
እድር ቢያሰማራው ፤ህዝቤ ተሰለፈ
የቅፅር ጥድ መስሎ፤ የተከረከመ
በስልት እየሄደ፤በወግ እየቆመ
ፖሊስ ከነ ማርሹ፤
ቄሱ ከነፅናው ፤
ከሳሹ ወራሹ፤
ወዲህ አሰለቃሹ፤ወዲህ የሚያፅናናው፤
ሁሉም ባጀብ ያልፋል፤በፈሊጥ፤በፊናው፤

ከቀብር መልስ ግን፤የንቧይ ቤት ሆነና፤
ተቀልሷል ሲባል፤ተመልሶ መና
መንገድ ላይ ሲጋፋ
ሲራኮት ሲዳፋ
ለቀለብ ሲዋደቅ
ይቺን በመገፍተር፤ ያንን በመደቅደቅ፤
ጭምቱን ሲያቀውስ፤የበሰለን ሲያምስ
ደንብ እያበላሸ፤ቅፅር ሲደረምስ፤
ሞቱ በስርአት ፤ኑሮው በትርምስ፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *