ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት

ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው jራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድርማንበብ ይቀጥሉ…

ወዛደር እና ወዝውዞ አደር

በቀደም አንድ የተባረከ ዜጋ “የዶሮ በሽታ ገብቷል” ሚል ወሬ ነዝቶ የእንቁላልን ዋጋ ቁልቁል ወሰደው፤ አጋጣሚውን ለመጠቀም ሞከርኩ፤ የቤት ሰራተኛየ “ዛሬ ምን ይሰራልህ?” ስትለኝ “ ቆንጆ ሽሮ አንተክትኪልኝና አንድ አምስት የተቀቀለ እንቁላል ጣል አርጊበት” እላታለሁ፤ ከጥቂት ቀናት በሁዋላ የሆነ ክሊኒክ ምርመራማንበብ ይቀጥሉ…

የወንዶች ሳሎን

በቀደም ዳጎስ ያለ ደመወዝ ተቀብየ ፥ ነጠር ነጠር እያልሁ በሰፈራችን ሳልፍ፥ “በውቄ ግባና ጸጉርህን ትንሽ ላሰማምርልህ “ የሚል ድምጽ ሰማሁ፤ የብዙ ዘመን ጸጉር አስተካካየ ሳሚ ነው ፤ ሚካያ በሐይሉ ‘ ጸጉሬንም ቆጥረሀል “ ብላ የዘፈነችው ለሳሚ ይመስለኛል፤ ሳሚ ፈጣን ነውማንበብ ይቀጥሉ…

ቀውስጦስ የት ነው?

ከጥንት አዋልድ መጻህፍት ባንዱ ያነበብኩት ታሪክ ይህንን ይመስላል፤ ባንዱ መንደር በሚገኝ ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ይካሄዳል፤ ወላጆቻውን ተከትለው የመጡ ጥቂት ህጻናት ወድያ ወዲህ እየተራወጡ ቅዳሴውን መረበሽ ጀመሩ፤ እግዚር ከላይ ሆኖ ሲያይ ተቆጣ፤ ረባሽ ህጻናትን እንዲቀስፉ መላእክትን ላካቸው፤ መላእክት ወርደው የህጻናቱን አንገትማንበብ ይቀጥሉ…

ሰሞንኛ ጨዋታ

ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ውስጥ በሚገኘው የ”አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼማንበብ ይቀጥሉ…

ሽልማቱ

“በምርጥ ነጠላ ዜማ ዘርፍ ያመቱ ኮከብ ተሸላሚ ማሞ መንገሻ “ ብሎ ለፈፈ ፥ የመድረክ መሪው አዳራሹ በጭብጨባ ተርገበገበ የማሞ ልብ በሀይል መምታት ጀመረ፥ ተሸላሚነቱን ከሰማ ጊዜ ጀምሮ መኪና እሸለማለሁ የሚል ሰመመን ጭንቅላቱን ተቆጣጥሮት ቆይቷል፤ ምን አይነት መኪና ይሆን እሚሸልሙኝ የሚልማንበብ ይቀጥሉ…

የተካደ ትውልድ

የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤ የተካደ ትውልድ አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤ ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍትማንበብ ይቀጥሉ…

አቦሌ

ከማውቃቸው ሰዎች መሀል በነውጠኝነቱ ወደር የሌለው አቦሌ ነው፤ ከብዙ ጊዜ በሁዋላ አንድ የጫማ መሸጫ ቤት ውስጥ ሳገኘው ገረመኝ፤ በፊቱ ያለው ውስብስብ ሰንበር የቀለበት መንገድ ይመስላል፤ ግንባሩ ላይ የብረት ቦክስ ጠባሳ አለ፤ ግራ ጉንጩ ላይ የሰንጢ ጭረት ይታያል፤ ማላመጫው ግድም የኮብልስቶንማንበብ ይቀጥሉ…

ኑሮ እና ብልሀቱ

የወሎ መንፈስ አድናቂ ነኝ፤ ስለወሎ ሲነሳ ይቺ ወግ ትዝ ትለኛለች፤ አንድ ሼህ እና አንድ ቄስ ወደ መስጊድ እየሄዱ ነው፤ ምንም አገሩ ወሎ ቢሆን ቄስና ሼህ ባንድ ላይ ወደ መስጊድ ሊሄዱ አይችሉም ልትሉኝ ትችላላችሁ፤ እሺ በቃ ፥ ቄሱ ሼሁን ወደ መስጊድማንበብ ይቀጥሉ…

ምንሽን

የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፥ በወጣሁበት እንዳልቀር አገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፥ ግና ምንድር ነው ማፍቀር እንዳስመሳይ አዝማሪ፥ ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስከዛሬ፥ ከጣቶችሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መቸ ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ፥ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላማንበብ ይቀጥሉ…