(ዊልየም የትስ Cloths of heaven ብሎ እንደፃፈው)
በእውቀቱ ስዩም ወደ አማርኛ እንደመነዘረው )
ባይመረመሬ ጥበብ ተሽቀርቅሮ
ከወርቃማ ብርሃን፤ ከብርማ ፀዳል
የተሰራ ሸማ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ስር፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ፥ ከህልሞቼ በቀር ፡፡
የኔ ውድ እንግዲህ
ሕልሜን እግሮችሽ ስር፥ ከዘረጋሁ ወዲህ፥
ቀስ ብለሽ ርገጪ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና የምትራመጂ፡፡
( የማለዳ ድባብ ፥ ገፅ 36)