ዶሮዎች ለእኛ ምን አደረጉ ብላችሁ ከመጠየቃችሁ በፊት፥ እኛ ለዶሮዎች ምን አደረግንላችው ብላችሁ ጠይቁ፤
በቀደም አንዱ ጉዋደኛችን ሊያገባ እጮኛው ቤት ሽምግልና ተላክን
ገና ገብተን ወንበራችን ላይ ሳንደላደል “ ልጁ ምን አለው?” አሉ አባትየው ፤
ከጉዋደኞቻችን አንዱ ኮራ ጀነን ብሎ መለሰ፤
“ልጁ ፤ የራሱ ዩቲውብ ቻናል እና ሁለት ሺህ ሰብስክራይበር አለው”
ድንቅ እሚለኝ ነገር ፤ የመጨረሻ በቁመት በወርዱ የሰገጠው የአማርኛ ፊልም ባንድ ቀን አምስት መቶ ሺህ ተመልካች እና ሁለትሺህ አስተያየት ያገኛል ፤ እኔ ግን ተጠብቤ ተጨንቄ የለጠፍኩት ትረካ ላይ ያገኘሁት አስተያየት አንድ ብቻ ነበር፤ ባነበብሁት ጊዜም እንዲህ ይላል፦
“አስም በሽታን በቤትዎ እንዴት ማከም እንደሚችሉ ለመረዳት የሚከተለውን ተጭነው ቻናላችንን ይጎብኙ”
እድል ነው ከማለት ውጭ ሌላ ምን ሊባል ይችላል🙁
ዛሬ የመጣሁት በእንቁላሉ ጉዳይ ላይ አስተያየት ለመሰንዘር ነው፤ ያገሬ ሰዎች ሆይ! ዶሮዎች ለእኛ ምን አደረጉ ብላችሁ ከመጠየቃችሁ በፊት፥ እኛ ለዶሮዎች ምን አደረግንላችው ብላችሁ ጠይቁ!
የዱሮ አውራ ዶሮ እኮ መሬት ጫር ጫር አድርጎ ትላትል ይበላል፤ ደጅ የተሰጣ ስጦ ደፍቶ ይበላል፤ እና ከፍተኛ ጉልበት ስላለው ለስርያ አይሰንፍም ፤ የድሮ አውራ ዶሮ ሲነሳበት አይደለም ቄብ ዶሮ ጊደር ላም ከመስረር አይመለስም፤ ሴቱዋ ዶሮም እንክብካቤ ስለሚጎርፍላት ሽለሙቅ ነበረች ! የምትጥለው እንቁላል ባለሁለት አስኩዋል ነበር! ሌላውን ተውትና ጥንቱ አውራ ዶሮ የድምፁ ግርማ ሞገስ በራሱ ወደር አልነበረውም ! አንድ አውራ ዶሮ ማርቆስ ላይ አኩኩሉ ቢል ድፍን ደምቢያን ይቀሰቅሳል፤ ልረደው ብለህ ብትነሳ በቀላሉ አንገቱን አይሰጥህም! በክንፉ አጠናግሮህ የደፋህበትን ቅርጫት ተሸክሞ ደሙን እየዘራ ያመልጣል፤
ዛሬ ስጦ የለ፤ ትል የለ፤ መሬቱ ቢጫር የሚወጣው መአት አይነት የቢራ ጠርሙስ ቆርኪ ነው፤ የዛሬ አውራ ዶሮ አቅም ስለሌለው ፤ልጃገረድ ዶሮ ላይ ለመውጣት ሊፍት ያስፈልገዋል፤
ይህንና መሰል ወጎችን ለመስማት ወደ ቻናሌ ይደባለቁ
https://www.youtube.com/channel/UCle3G70CA6GFUK1K_YKX7CQ