Tidarfelagi.com

ግን አንድ ሰው አለ

እርጅና ሲጫንሽ
እድሜ ተጠራቅሞ ፥እንዳስም ሲያፍንሽ
ሽበት እንዳመዳይ
በጭንቅላትሽ ላይ
በድንገት ሲፈላ
ያይንሽ ከረጢቱ ፥ በንቅልፍሽ ሲሞላ
ምድጃ ዳር ሆነሽ
መጣፍሽን ከፍተሽ
ያለፈውን ዘመን ፥ ከፍተሽ ስታነቢ
የኔን ቃል አስቢ፦

ስንቶች አፈቀሩት ፥ በሐቅ በይስሙላ
የገፅሽን አቦል፥ የውበትሽን አፍላ
ግን አንድ ሰው አለ
ከሌሎች ወንዶች ጋር ፥ ያልተመሳሰለ
በእፁብ ድንቋ ነፍስሽ ፥ ፍቅር የነደደ
የመልክሽ ፀደይ ሲያልፍ
ልክ እንደ መስቀል ወፍ ፤ጥሎሽ ያልነጎደ፤

መነሻ ፤ የዊሊያም በትለር የትስ -When you are old
(የማለዳ ድባብ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *