አንድ ሰው በፈረንጅ አገር ካምስት አመት በላይ ከቆየ ጭንቀላቱ ሊናወጥ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ከወዳጄ በየነ ሌላ ማሳያ ሊኖር አይችልም፤ ባለፈው የሮፍናን ዜማ በራሱ ግጥም አንዲህ እያለ ሲያንጎራጉር ሰማሁተና አዘንኩ፤
ያገሬ ልጅ
ቪዛ አገኘሸ ወ—–ይ?
ያገሬ ልጅ
ዲቪ ወጣልሽ ወ—-ይ?
የኔስ ልብ እውነት አየ
መመለስ መቅረቴም አለየ
ግሪን ካርዴም ዘገየ፤
ጨላ አለኝ ብየ ስውተረተር
ስሜ ተጥፎ አየሁት በዱቤ ደብተር
ወስዷል ይላል
በልቷል ይላል፤
ግራኝ ግራ-ዝማችን ሳያሰልም
የግራ ፖለቲካ ሳይጨልም
እኔም ሳይገባኝ ግራ
ወደ ግራ-ጌ ተሻግራ
ጉዲት ሳትጥል እቁብ
አለም ሳይቆጥረን ከቁብ
ያገሬ ልጅ
የንጉስ አዋጅን ከሰማህ
አገር ሚስትህ ናት፥ አሜሪካም ናት ውሽማህ
ሰከላ
አባይን ወለደች
ግብጥም ክሬዲቱን ወሰደች