ታጋቹ ማስታወሻ

ቀሳ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቤቴ ውስጥ ያገኘሁት ምግብ ሩዝ ብቻ ነው ፤ ሰኞ ሩዝ በቲማቲም- ማክሰኞ ሩዝ በጅንጅብል- ረቡእ ሩዝ እንደወረደ፤ ወዘተ…ባጭሩ በሩዝና በሪዝ ተከብቤ ሰነበትሁ ማለት ይቻላል፤ አንዳንዴ ምግብ የቀየርኩ እንዲመስለኝ የምበላበትን ቦታ እቀያይራለሁ፤ ሳሎን ውስጥ ሁለት ማንኪያ እጎርስናማንበብ ይቀጥሉ…

የግል ስሜትና ብሄራዊ ምልክት

ባገራችን ህዝብ ከገዥ ጋር ተማክሮ የመረጠው ብሄራዊ ምልክት ኖሮ አያውቅም ፤ ያገር ገዥዎች የሆነ የስልጣን ምልክት ይመርጣሉ፤ ያ ምልክት በውድም ሆነ በግድ ብሄራዊ ምልክት ሆኖ ይቀራል ፤ገዥው አምራቹን ህዝብ( ገበሬውን፤አንጣሪውንና ነጋዴውን) አማክሮ የመረጠው ምልክት መኖሩን የሚያስረዳ ታሪክ ካለ አቅርብልኝ! የእድሜማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሗሊት!

ከእለታት አንድ ቀን፤ የሺዋ ሃያላን፤ ጭንቅ እማይችለውን ፤ሁሌም take it easy የሚለውን ፤ልጅ ኢያሱን በካልቾ ብለው ፤ከስልጣን ካባረሩ በሗላ የምኒልክን ልጅ ዘውዲቱን ዙፋን ላይ ዱቅ አደረጏት ! ተፈሪ መኮንን የተባለውን ጎረምሳ መስፍን ደግሞ “አልጋወራሽ” ና “እንደራሴ” የሚል ማእረግ ሸልመው፤ ወረፋማንበብ ይቀጥሉ…

የፈለጉት ነገር በቤታቸው ሞልቶ

በዳግማይ ምኒልክ ዘመን ባንዱ ገጠር ውስጥ አንዱ ባላገር የሌላውን ሚስት ወሸመ፤ባልየው ሲባንን ውሽምየውን በጥይት ልቡን አለውና ካገር ተሰደደ፡፤ ይህንን የሰማ ፤ ምህረቴ የተባለ ፤እንደ ሆመር አይነስውር የሆነ፤አውቆ አበድ ባለቅኔ እንዲህ ብሎ ገጠመ፤ “አገሩ ባዶ ነው፤ ያም ሄዶ ያም ሞቶ የፈለጉትማንበብ ይቀጥሉ…

ታማሚና ጠያቂ

ትወለጃለሽ፤ትኖርያለሽ፤ትሞቻለሽ፤ በየጣልቃው ግን ትታመምያለሽ! ሳይንሳዊ ሀቅ ነው!! በሽታ ድሮ ቀረ! ደሞ የዛሬ ልጅ ምን በሽታ ያውቃል? የኔ ትውልድ መኩራት ሲያንሰው ፤ እነ ፈንጣጣን፤ እነ ፖሊዮን፤ እነ ትክትክን፤ እነ አባ ሰንጋን ሸውዶ ነው እዚህ የደረሰው፤ በሽታ ብቻ ሳይሆን በሽተኛ ራሱ ድሮማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ምሽት

ከጥናት፤ከጥፈት እና ከዩቲውብ በተረፈኝ ጊዜ አውደለድልበታለሁ በተለይ አርብ ምሽት ፤በቤቴ አቅራቢያ ወደ ምትገኝ ባር ጎራ ማለት ደስ ይለኛል፤ እዛ አሪፍ የአይርሽ ድራፍት አዝዤ ወደ ባንኮኒው አፈጣለሁ፤ባንኮኒው ጀርባ የባሩ ባለቤት ቆማ አስተናጋጆችን ታሰማራለች ፤ባየችኝ ቁጥር ረጅም ፈገግታ ትለግሰኛለች፤ እኔም እንደ ውሃማንበብ ይቀጥሉ…

መንዲስ

ፈረንጆች አለመጠን ረጅምና ግዙፍ የሆነን ሰው Giant ብለው ይጠሩታል ። “ጋይንት” ብሎ እሚያነበው ስለማይጠፋ “ጃየንት” – /jai·uhnt መሆኑን አስታውሼ ልለፍ። በአማርኛ መንዲስ የሚል አቻ አለው። በታሪካንችን ዝነኛው መንዲስ ከታች ፎቶው ላይ ያለው ይመስለኛል። ይህ ሰማይ- ጠቀስ ሰውየ፤ መጀመርያ የቤኒሻንጉሉ ጌታማንበብ ይቀጥሉ…

ሞቱ በስርአት

ጥሩንባ ተነፋ ህልፈት ተለፈፈ እድር ቢያሰማራው ፤ህዝቤ ተሰለፈ የቅፅር ጥድ መስሎ፤ የተከረከመ በስልት እየሄደ፤በወግ እየቆመ ፖሊስ ከነ ማርሹ፤ ቄሱ ከነፅናው ፤ ከሳሹ ወራሹ፤ ወዲህ አሰለቃሹ፤ወዲህ የሚያፅናናው፤ ሁሉም ባጀብ ያልፋል፤በፈሊጥ፤በፊናው፤ ከቀብር መልስ ግን፤የንቧይ ቤት ሆነና፤ ተቀልሷል ሲባል፤ተመልሶ መና መንገድ ላይ ሲጋፋማንበብ ይቀጥሉ…

የስነፅሁፍ ምሽት ከየት ወዴት?

  ድሮ በሃይለስላሴ ዘመን ያዲሳባ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች፤ ባህል ማእከል ውስጥ፤ የስነፅሁፍ ምሽት አዘጋጅተው፤ጃንሆይን በንግድነት ይጠሩዋቸዋል። ጃንሆይ የተማሪዎችን ጥሪ አክብረው፤ካባቸውን ደርበው ፤ ከች ይላሉ:: ከዛ ኮከብ ተማሪዎች ተራ በተራ እየተነሱ ረጅጅምምም ግጥም ያቀርባሉ። በጊዜው ስለፍቅር፤ ስለውበት መግጠም እንደ ቅንጦት ይቆጠራልማንበብ ይቀጥሉ…

ሙገሳ ለሞጋሳ

በ1571 ገደማ በልዑል ፋሲለደስ እና በቦረን ኦሮሞ የገዳ ሰራዊት መካከል ጎጃም ውስጥ ጦርነት ተደረገ፤ ቦረኖች አሸንፈው ልዑል ፋሲል በጦር ሜዳ ላይ ወደቀ፤አሸናፊው የኦሮሞ አባዱላ ፤ ሱስንዮስ የተባለውን የልዑሉን ልጅ አገኘው። በጥንታዊት ኢትዮጵያ በጦርሜዳ የተሸነፈን ምርኮኛ ትንሽ ትልቅ ሳይሉ መረሸን ብርቅማንበብ ይቀጥሉ…