ጥቂት ሀሳቦች

አንዳንድ ሰዎች ‘ የብሄር ፖለቲካ በህግ ይታገድልን ሲሉ’ እሰማለሁ፤ የብሄር ፖለቲካ አይጥመኝም፤ባገራችን ወትሮ የሚታየው መከራ ምንጮች አንዱ ያልተገራ የብሄር ፖለቲካ እንደሆነም አምናለሁ፤ ያም ሆኖ ዜጎች በቁዋንቁዋና በዘመድ የመደራጀታቸውን መብት መግፈፍ ሰላምና ደስታ ያመጣል ብየ አላስብም፤ብጤውን መርጦ መቡዋደን የሰው ባህርይ ነው፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ስለፍቅር በስምአብ ይቅር!!

በዙረት ካገኘሗቸው እውቀቶች አንዱን በማካፈል ወጌን ልጀምር። ያፍሪካ ስደተኞች ያንዱን ያውሮፓ አገር ድንበር አቋርጠው ይገቡና አንድ ከተማ ውስጥ አድፍጠው ይቀመጣሉ። በከተማው ባንድ ስፍራ ላይ መንግስት ገንብቶ ያልጨረሰው ባዶ ህንፃ ይኖራል። ስደተኞች ከለታት አንድ ቀን ተደራጅተው ህንፃውን ወርረው ይይዙታል። የህንፃውን አፓርታማማንበብ ይቀጥሉ…

እስቲ ስለ ራስሴ

እስቲ ስለ ራስህ ትንሽ ንገረኝ ባልሽኝ መሰረት ራሴን በትህትና እንደሚከተለው አስተዋውቃለሁ🙂 አነጋገሬ የሰለጠነ አረማመዴ የተመጠነ ስደሰት ፊቴ :የግዚሀር ባውዛ ስስም ከንፈሬ : ያበባ ጤዛ!! ካለት ያወጋሁ ከንብ የተጋሁ እንደ ዘንገና : ውሃ የረጋሁ ከጎህ ቀድሜ : ባይንሽ የነጋሁ። ባስብ በመላ-ብናገርማንበብ ይቀጥሉ…

ሰው በሰውነቱ

የምግብ ቤት ባለቤት የሆነ ሰውየ :በደንበኞቹ መሀል ሲዘዋወር አንድ ዝነኛ ጋዜጠኛ ይመለከታል። ወድያው ባለቤትየው አስተናጋጂቱን ጠርቶ ” እዛ ጥግ ላይ የተቀመጠው ጋዜጠኛ ይታይሻል? ሂጅና የሚፈልገውን እየጠየቅሽ ተንከባከቢው!! ወጥ ካነሰው ጨምሪለት!! እንዲያውም ለኔ ራት ከተሰራው ዶሮ አንድ ቅልጥም ብትሰጪው ደስ ይለኛል።ማንበብ ይቀጥሉ…

“የሚያጀግነውን የሚያውቅ ህዝብ የተባረከ ነው”

ባገራችን የነገስታት መታሰቢያ ሀውልት ማቆም: በጀግና ተዋጊዎች ስም ጎዳናዎችንና ትምርትቤቶችን መሰየም የተለመደ ነው። አገሩ በሙሉ በጦርና ጋሻ ምልክት የተሞላ ቢሆንም አሁንም በወታደሮች: በጌቶችና በእመቤቶች ስም ሀውልት የማቆም ግፊቶች ቀጥለዋል ። በፖለቲካው ግርግር መሀል: ለህዝብ መንፈሳዊ እና አእምሮአዊ እድገት መዋጮ ያደረጉማንበብ ይቀጥሉ…

ወዲህ በዳዊት ወዲህ በጋሻ!!!

ትላንትና ከባልንጀራየ ምኡዝ ጋር ተገናኝተን ቢራ ወይንና የመሳሰሉትን አልኮሎች ስንጠጣ:-አገርን በፍቅር ስለማስተዳደር አሰፈላጊነት ” በሰፊው ሰበክሁለት። እሱ እያዛጋና እየተቅበጠበጠ ሲሰማኝ ቆይቶ ሳያስጨርሰኝ የሚከተለውን ቀደዳ ቀደደ። “ማኪያቬሊ ስለተባለ ዝነኛ ደራሲ ሰምተህ ይሆን? ስለስልጣን ባህርይ እንደ ሌሎች ሳያለባብስ እቅጯን ፅፏል!! ይህ ሀቀኛማንበብ ይቀጥሉ…

ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ 

የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ ልቤን ክንዴን እያዛለ ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ። እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ። አሰታወሰኝ አስታወሰኝ። ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ ያለም ዘፋኝ የማያውቀውማንበብ ይቀጥሉ…

ግርምሽ ሲታወሱ

ግርማ ወልደጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሁኑው የተመረጡ እለት ብዙ ሰዎች ተገርመዋል ። ከእስክንድር ነጋ ጋዜጦች አንዱ ዜናውን የዘገበችው ” ወያኔ አበደች ” በሚል ርእስ እንደነበር ትዝ ይለኛል። አንድ አሙስ የቀረው ሽማግሌ እንዴት ለዚህ ሚና ይታጫል በሚል እብሪት የተቹ አልጠፉም ። ብዙዎቻችን “ሽማግሌማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ስንኞች

እንዳለመታደል ሁኖ የጎጃሙ ጌታ የራስ አዳል ልጆች አሪፍ ያገር አስተዳዳሪ አልነበሩም። እንደመታደል ሆኖ ደሞ የተዋጣላቸው ባለቅኔዎች ነበሩ። ግጥሞቻቸው ከኑሯችን ጋር በጣም የተቆራኙ ናቸው። ለምሳሌ የግፍ ዘገባ በሰማን ቁጥር የምንቀባበለው። “የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል” የሚለውን ገራሚ ግጥምማንበብ ይቀጥሉ…

ሁሉም ለምን ያልፋል?

የጣፈንታ መዳፍ ደስታና መከራን: እያፈሰ ሲናኝ “ሁሉም ያልፋል ” ብሎ : ማነው የሚያፅናናኝ? ግራ በተጋባ :በዞረበት አገር ካንቺ የምጋራው :ሰናይ ሰናይ ነገር ፊቴን የሚያበራው :ያይንሽ ላይ ወጋገን ዛሬ ተለኩሶ : የሚያሳየኝ ነገን ለምን ሲባል ይለፍ : ያንን መሳይ ፍቅር ደሰታሽማንበብ ይቀጥሉ…