በውቄ ስዩም የተባለ ድህረ- ወጣት ተጋዳላይ ፤ ከተወለደባት እና ከተገረዘባት እናት አገሩ ተሰድዶ፤በዱር በገደሉ፤ በፓርኩ በሆቴሉ፤ በተራራው በስዊሚንግ ፑሉ ፤ሶስት ወር ሙሉ ለናት አገሩ ሲንከራተት ቆይቶ ፤በመጭው መስከረም ሰላሳ በድል ይመለሳል፤ በዚህ ታሪካዊ ቀን የጀግና አቀባበል ይደረግለታል፤ ያቀባበሉ ትንቢታዊ መርሀማንበብ ይቀጥሉ…
የባከነ ሌሊት!
ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ ሰይጣን አላሳፈርሁ። ሌቦች ደብድበውት አንዱን ምስኪን ላሥር ባምቢስ ድልድዩ ሥር ቆስሎ የወደቀ ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ ፊቱማንበብ ይቀጥሉ…
አይደለም ምኞቴ
አይደለም ምኞቴ ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም እይደለም ምኞቴ ከንፈርሽን ማለብ ቀሚስሽን መግለብ ከገላሽ ቆርሼ :ገላየን መቀለብ ደረትሽን ማለም ጡትሽን መሳለም በቁንጅናሽ ጅረት : ገነቴን ማለምለም አላማየ አይደለም:: ምኞቴን ልንገርሽ? ካለሺበት ቦታ: ቀልቤንማንበብ ይቀጥሉ…
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
” እኔ ልሙትልሽ” እያልኩኝ አልምልም ቃላቴን መንዝሬ: ለሞት ቀብድ አልከፍልም ያኔ ትዝ ይልሻል? “ራስህን ግደል” ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ እድሜ ለስጦታሽ: ታጠበ ሸሚዜ። ገደብ ጫፍ በሌለው: በልቤ መጋዘን ቢታጨቅ መከራ: ቢጠራቀም ሀዘን “ባለፈልኝ” እንጂ “በሞትኩ” ብየ አላቅም ካልጋ ላይ ነውማንበብ ይቀጥሉ…
ኢትዮጵያዊ ነን!
ፈቅደን ሲመሩን፤ ችቦ ተቀባይ ለሚነዱን ግን ፤ አሻፈረን ባይ ካልነኩን በቀር፤ ቀድመን ማንዘምት ከጋሻ በፊት ፤ ጦር የማንሸምት ኢትዮጵያዊ ነን! ህብር ያስጌጠው፤ ህይወት ለማብቀል ዘር ሳናጣራ ፤ የምንዳቀል ለነዱን ሰይጣን፤ ለመሩን ሰናይ ጌታን ከገባር፤ ለይተን ምናይ፤ ኢትዮጵያዊ ነን! ብዙ ህልሞችን፤ማንበብ ይቀጥሉ…
“የዘር በቆሎ” እና ሌሎች ነጥቦች
ሰሞኑን ኑሮ ተወዱዋል። ትንታኔና ትንቢት ጥንቡን ጥሉዋል። እኔም አይኔን አጥቤ ድርሻየን ልተነትን ነው። ቀልዱን እዚህ ላይ ላቆየውና ውደ ቁምነገሩ። ባጭር ጊዜ እንደ ዶፍ የወረዱት ክስተቶች እንኩዋን ለመተንተን ለመቆጠር እንኩዋ እንደሚያቸግሩ አላጣሁትም። በሁለት ጉዳዮች ላይ ብቻ ባገር ልጅነት የሚታየኝን ለማካፈል እወዳለሁ። አብይማንበብ ይቀጥሉ…
የዝዋል ድንኩዋን እንዳይሆን
ከጥቂት ወራት በፊት ሃያ ሁለት ማዞርያ ተቀምጠን ለገ ጣፎ ላይ ሲጨስ የተለመለከትን እኔና ብጤዎቼ አሁን ያለውን አንፃራዊ መረጋጋት እንደ ብርቅ ነገር ብንቆጥረው አይፈረድብንም። ያኔ ምንም ማድረግ ምንም ማለም የተሳነን ምስኪኖች ነበርን ። አሁን ከምስኪንነት ወደ ጀግናነት ተሸጋግረናል። “ጀግናነት ማለት ታላቅማንበብ ይቀጥሉ…
እያንዳንድሽ!
ወገን! ግጥሙ በሁዋላ ይደርሳል፤ ይሄ አጭር ማሳሰቢያ ነው! እያንዳንድሽ! ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ ፤ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በፀደይ ወቅት፤ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ ፤የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ፤አጎጠጎጤሽን በውሃ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፤ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ፤ በሽቦማንበብ ይቀጥሉ…
የዘገየው ዘማች
ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተገረበ ረጂሙ መስታውት ፊት ቆሜ ዘናጭ ሱፌን ለበስኩ። ክራቫት ማሰሩ ላይ ግን አልተሳካልኝም። የክራቫቴ ራስ ባንድ ጎን ተድቦልቡሎ የቡዳ መዳኒት መስሏል። ቁርሴን በልቼ በዳግማዊ ምኒልክ ሀውልት ስር የማስቀምጠውን አበባ ለመግዛት ወጣሁ። ገና አፋልቱ ላይ ልደርስ ስል አንዱ ብቅማንበብ ይቀጥሉ…
ግጥምና ገድል (ቅፅ 1)
“ከመዳኒት ፍቱን ወሸባና ኮሶ ከሰው መልካም ባልቻ : ከፈረስም ነፍሶ” ከላይ የጠቀስኩት ለስመጥሩው አርበኛ ለደጃዝማች ባልቻ ከተዘመሩት ግጥሞች አንዱ ነው። አዝማሪው ባልቻን ሲያሞጋግስ እግረመንገዱን ስለኖረበት ዘመን የህክምና ታሪክ ነግሮናል ። ስለኮሶ ምንነት ለማብራራት የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም። “ወሸባ ” የሚለውን ቃል ትርጉምማንበብ ይቀጥሉ…