– የተመጠጠ ቤት የሞላ ሽንትቤት ጭር ያለ ቤተሰብ የተጠረገ ድስት -ድርቅ የመታው ሞሰብ!! -ያደፈ ቄጤማ በበግ በሰው እግር- የተደቀደቀ ወዙ ባንድ ሌሊት -ተመጦ ያለቀ መጥረጊያ ሚጠብቅ -ወድቆ ተበታትኖ ትናንት ጌጥ የነበር- ዛሬ ጉድፍ ሆኖ!! -የተወቀጠ ፊት -የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት-ወለምማንበብ ይቀጥሉ…
ዜግነት እውነት ነው፤ ብሄረሰብነት እምነት ነው
ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ፤ ጥንታዊ ወታደር በባላገር ላይ ሲያደርስ የኖረውን በደል ፅፎ አይጠግብም፤ ባንድ ቦታ ስለ አንድ ገበሬ የሚከተለውን ይተርካል፤ •….“ከነዚህ መከረኞች አንዱ(ገበሬ) መልከ ቅን ምሽት ነበረችው፤ አንድ ቀን በቴዎድሮስ ጊዜ አንድ ቅማጫም ነፍጠኛ ተቤቱ ተመርቶ ገባና ባለቤቲቱ መልከ ቅንማንበብ ይቀጥሉ…
ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ
የሚከተለው ግጥም በሚታየው ታሪካዊ ፎቶግራፍ ንሸጣ የተፃፈ ነው፤ በፎቶው ላይ ሻምበል አበበ ቢቂላ የልምምድ ሩጫ ሲሮጥ ይታያል፤ ከሁዋላው አህያ እየነዳ የሚያልፍ አላፊ ጠፊ ገበሬ አለ፤ ግጥሙን የጣፍኩት ለዚህ አህያ ነጂ ገበሬ ነው፤ ) ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ ባሮጌው ጎዳና፤ በጮርቃውማንበብ ይቀጥሉ…
ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
(የሚያስተክዝ ወግ) ከየረር በር እስከ ቦሌ የሚሄድ ምኒባስ የመሳፈር እድል ያልገጠመው ሰው ስለ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ልተንትን ቢል ማን ይሰማዋል? እና ትናንት የተሳፈርኩበት ምኒባስ ካፍ እስከ ሰደፍ ሞልቶ ነበር፤ የምኒባሱ ነባር ወንበር የተሳፋሪውን ብዛት ባገናዘበ መልኩ ሽግሽግ ተደርግጎበታል፤ ወደ ሁዋለኛውማንበብ ይቀጥሉ…
ግጥሎት(ግጥምና ጠሎት)
ሲፈርድብህ በማለዳው እንዲህ ያለ ሀሳብ ይልክብሃል!! ግጥሎት(ግጥምና ጠሎት) አቤቱ ውሃን አየር ላይ ያረጋህ ከቀዳሚ ትውልድ ፤እስከ ከዳሚ ትውልድ ዘመንህን የዘረጋህ በጃርት ወስፌ ጠንቁለህ ፤ያሞራን አይን ያፈሰስህ ካላጣኸው እጄጠባብ፤ ኤሊን ድንጋይ ያለበስህ ካልቸገረህ ወጣትነት፤ አዳምን ባርባ ዐመት ያስረጀህ በህዳር በሽታ ዘመዶቼንማንበብ ይቀጥሉ…
የሃይገር ፍቅር
(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) በቀደም እለት : ” ወንድ ልጅ አይጣ” የሚል ጥቅስ ግንባሩ ላይ የተፃፈበት ሃይገር ባስ ተሳፈርሁ። ” ሃይገር ባስ ” ባለም የመጨረሻው መናኛ አውቶብስ ነው። ቻይና ላፍሪካ ቺስታ ሀገሮች አንድ ባቡር በሸጠች ቁጥር ምራቂ አድርጋ የምትሰጠው ሃይገር ባስንማንበብ ይቀጥሉ…
ጀምጃሚዎች (ቅፅ 2)
የቸኮልየት ሆቴል ባለቤት ጋሽ ካሌብ ባሁኑ ጊዜ ከጎኔ ይገኛሉ። የሆነች: በሳቅና በሳል ማሃል ያለች ድምፅ እያሰሙ አጠገቤ ያለውን ቁሞ-ቀር ሳይክል ይጋልባሉ። ጋሽ ካሌብ ወደ መጀምጀሚያው አዳራሽ የሚመጡት ሰውነቴን ላፍታታ በሚል ሰበብ የጂም ማሺኖች በጥንቃቄ መያዝ አለመያዛቸውን ለመሰለል ነው። “አልተቻሉም ጋሽማንበብ ይቀጥሉ…
ጅምጃሚዎች
(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ላሎ ወደ መርሀባ ተጠጋና ምንጣፉ ላይ በጀርባዋ አንጋለላት። ከዚያ በእግሮቿ ማሃል በርከክ አለና ቁልቁል ተመለከታት። ፊቷ በላብ ተጠምቋል!! ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። እግሯን ብድግ አድርጎ ወደ ደረቱ ሳበው። አንባቢ ሆይ! የወሲብ ታሪክ የምተርክልህ መስሎህ እግርህን በእግርህ ላይማንበብ ይቀጥሉ…
አቶ ሀዲስ አለማየሁ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች
አቶ ሀዲስ አለማየሁ በልቦለድ ፀሀፊነታቸው የተጋረደ የፖለቲካ ሰብእና ነበራቸው። በተለያየ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች እንደ ደረቅ ትንቢት የሚቆጠሩ ነበሩ። ለዛሬ: መጋቢት 19: 1985 አመተ ምህረት ባዲሳባ ዩንቨርሲቲ ካቀረቡት ንግግር የሚከተለውን ለመቀንጨብ ወደድሁ። በጥሞና አንብበን በሰከነ መንፈስ እንወያይበት። የንግግሩማንበብ ይቀጥሉ…
ምንሽን
የሰው አገር ሙጥኝ ብየ-በወጣሁበት እንዳልቀር ሀገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ -ግና ምንድር ነው ማፍቀር? እንዳስመሳይ አዝማሪ -ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስተዛሬ ከጣትሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መች ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላ ስለቅምማንበብ ይቀጥሉ…