ጉደኛ ስንኞች

እንኳን ለአለም መሃኖች ቀን አደረሰን እንዲህ የሚባል ቀን እንደሌለ አውቃለሁ። ግን እስከመቸ ሌሎች የደነገጉትን ቀን ብቻ ሳከብር እኖራለሁ ?! እኔም ቀን ልደንግግ እንጂ በድሮ ጊዜ ልጅ መውለድ የሴት ዋና ተግባር ተደርጎ ይወሰድ ነበር። ያኔ ዘጠና ሚሊዮን ገና አልሞላንም ። የተወለደውማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክ በመሰንቆ (3)

ባልቻ ፈረሱ ነፍሶ መድፉን ጣለው ተኩሶ ባልቻ ሆሆ ! ባልቻ ሆሆ🙂 ባልቻ አባ ነፍሶን በታሪክ ውስጥ ስመጥር ያደረገው አድዋ ላይ የፈፀመው ጅብድ ብቻ አይደለም። ምን የመሰለ ጀብድ ሰርተው ፣እንዳዘቦት ቀን የተረሱ ጀግኖች ሞልተዋል። የወሎየው አዝማሪ፣ የሀሰን አማኑ መሰንቆ፣ ለባልቻ ሳፎማንበብ ይቀጥሉ…

ተአምረ መኪና

(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ ) ወደ ረከቦት ጎዳና የሚወስደኝን አውቶብስ እየጠበቅሁ ነው። አውቶብሱ ከመድረሱ በፊት ከ’ፋኖቼ አንዱ በዚህ ካለፈ ሊፍት ይሰጠኛል ብየ ተስፋ አረግሁ። ፌርማታው፣ በጎዳና አዳሪዎች ሽንት ጨቅይቷል። እና የቆምኩበት ቦታ ለfan ሳይሆን ለጉንfan የተጋለጠ መሆኑ ገባኝ። ዙርያ ገባውን ስመለከት፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ረከቦት ጎዳና

ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ አዲሳበባ ድምጻዊት ከተማ ናት ። አዱ ገነት ውስጥ ፤ ከመኪና የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በብዛት፤ በሥራ ላይ የሚውለው ክላክሱ ነው። እንዲያው ሸገር ውስጥ መኪና- ነፊ እንጂ መኪና- ነጂ ያለ አይመስለኝም ። አንድ አሽከርካሪ ቆንጆ እግረኛ ሲመለከት ምሥራቅማንበብ ይቀጥሉ…

የተካደ ትውልድ

የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው የተካደ ትውልድ ፤ አብዝቶ የጾመ፤ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፤ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ ፤ የተወለደ’ ለት አምባሩ ካቴና፤ ማተቡ ሠንሠለት፡፡ ምቾትንማንበብ ይቀጥሉ…

“ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስአበባ”

ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ“ ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስአበባ“የተባለ ሸጋ መጽሐፍ ጽፈው ለገበያ አቅርበውልናል። ለፌስቡክ ባለንጀሮቼ በልበሙሉነት የምጋብዘው መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ያንድ ኢትዮጵያዊ የባዮሎጂ ሊቅ ግለታሪክ ቢሆንም፤ እግረመንገዱን ከጣልያን ወረራ እስከዛሬ ድረስ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በሚጣፍጥ አማርኛ ይተርካል ። ከባለታሪኩ ሕይወት ጋር የሩቅናማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

አሪፍ የፍቅር ግጥም ጽፌ ለመለጠፍ አስቤ ነበር። ግን ብለው ብሠራው “ እኔ እምልሽ ውዴ” ከሚለው ቃል ውጭ ጠብ ሊልኝ አልቻለም። እኔ እምልሽ ውዴ! ብለው ሳይጀምሩ- ስለፍቅር መጻፍ አይቻልም እንዴ? አንዳንድ ባለንጀሮቼ በውስጥ መሥመር ይሄን ድብርታም ዘመን እንዴት እያሳለፍከው ነው ምናምንማንበብ ይቀጥሉ…

ምክር እስከመቃብር

የሆነ ጊዜ ላይ ባንድ እውቅ ሆስፒታል ውስጥ ያማካሪነት ሥራ እሠራ ነበር። የሥልጠና መርሐችን ከአሜሪካኖች በቀጥታ የተኮረጀ ስለነበር ምክራችን ድሐን መሠረት ያደረገ አልነበረም። ከእለታት አንድ ቀን አንዱ ጎስቆል ያለ ሰው ወደ ቢሮየ መጥቶ ምርመራ ተደረገለት። ውጤቱን ተመልክቸ በደሙ ውስጥ ሻይረሱ እንደተገኘበትማንበብ ይቀጥሉ…

የተቀሸቡ ፎቶዎች

የተቀሸቡ ፎቶዎች ፤ ቁጥር 1 የሆነ ጊዜ ላይ የራስ አሉላ አባነጋን ፎቶ ፍለጋ ወደ ጉግል ተሠማራሁ ። ጉግል ሁለት የማውቃቸውን ፎቶዎችና አንድ አዲስ ጨምሮ አቀረበልኝ። አዲሱ ምስል ”አሉላ አባ ነጋ በወጣትነቸው ዘመን “የሚል መግለጫ አለው። ፎቶው “አረና ትግራይ “ተብሎ ለሚጠራማንበብ ይቀጥሉ…

ክብደትን የመቀነስ ጥበብ

(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ያኔ ባቡር ሳይወጠን- የሃያ ሁለት ማዞርያ አየር ባስመረት ሽሮ ሳይታጠን -ዓባይን የደፈረው መሪ(ሆስኒሙባረክ)ሳይከነበል-ታምራት ገለታ ቃሊቲን ሳይዳበል- ታምራት ላይኔ ጌታን ሳይቀበል-ካገር ወጣሁ። አሜሪካ እንደገባሁ በመጀመርያ የፈጸምኩት ተግባር ቢኖር መወፈር ነው። አትፍረድብኝ። አሜሪካ ውስጥ ሰው መንቀሳቀስ አቁሟል። ኑሮ ማለትማንበብ ይቀጥሉ…