የሆነ ምሽት

ይሄ ንፍጣም ቫይረስ ወደ አገራችን ከመግባቱ ሁለት ወር አስቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደ ጉድ ጨፈርኩበት! ዛሬ እንዲህ ተጨማድጄ ልቀመጥ ያኔ እየዞርኩ የክለብ ምንጣፍ በዳንስ ሳጨማድድ አመሽ ነበር! የዚያን ቀን ምሽት ከጊድዮን ጋር ነበርሁ፤ ባለትዳር ነው፤ የሚስቱና (ዛዮን) የሶስት ልጆቹ ፎቶ በስልኩማንበብ ይቀጥሉ…

ከታጋቹ ማስታወሻ የተቀነጨበ

ብዙ ያሜሪካ ላጤዎች ውሻ አላቸው። እኔ ውሻ የማሳድርበት አቅም የለኝም፤ ቢሆንም በቅርቡ ቤት ውስጥ ከሚርመሰመሱት ጉንዳኖች መካከል የሰልፍ መሪውን መርጨ አለመድኩት፤ ምሳ ስበላ አንድ ሩዝ ፍሬ ጣል አደርግለታለሁ፤ ወደ ዘመዶቹ ይዞ ሊሄድ ሲል አንገቱን ይዤ አስቀረዋለሁ፤ እኔ የስዊድን ቮድካየን ስቀመቅም፤ማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ይሄ ቀሳ ግን ስንቱን አሳበደ? ቲክቶክ ምስክሬ ነው፤ የድሮ እብድ ሙዚቃ ቤት በር ላይ ይደንስ ነበር ፤ የዘንድሮ ዲጅታል እብድ ደሞ ሞባይሉ ካሜራ ፊት ይደንሳል ፤ እኔ ራሴን እየታዘብኩት ነው፤ አሁን“ ዘፈን ሃጢአት ነው አይደለም?” በሚል ክርክር ላይ በስካይፒ መሳተፌማንበብ ይቀጥሉ…

አመፅ!!

በለው! በለው! ዛሬ ታሪክ ተሰራ! ከተማውን ባንድ እግሩ አቆምነው!! “ሽጉጥ መትረይሱን አንግቶታል ያ ጥቁር ግስላ ደም ሽቶታል” የሚለውን የአለማየሁ እሼቴን ዘፈን በአለማየሁ ፋንታ ድምፅ እያንጎራጎርሁ ከቤቴ ወጣሁ ፤ ፓርኩ ላይ ስደርስ አንዲት ደርባባ ኤሽያዊት ሰልፈኛ ተዋወቅሁ፤ ከኢትዮጵያ እንደሆንኩ ስነግራት አይኗማንበብ ይቀጥሉ…

ትዝታየ በፎቶ ዙርያ

በልጅነቴ ትዝ ከሚሉኝ መፈክሮች አንዱ “ያልሰራ አይብላ” የሚል ነው። ስራ ብሄራዊ ሀይማኖት ሆኖ ነበር። ይሄ ደግሞ በጊዜው ፎቶ አነሳስ ላይ ሳይቀር ይንፀባረቃል ፤ አንድ ሰው ፎቶ ሲነሳ የሆነ ሰርቶ ማሳያ ነገር ፎቶው ውስጥ ማካተት ነበረበት፤ የቤት እመቤት ከሆነች ጥጥ እየፈተለችማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ፎቶ (ክፍል አንድ)

ልጅ እያለሁ ፎቶ ብርቅ ነበር ፤ ከእናቴ ጋራ የሆነ ግብዣ እሄዳለሁ፤ የቤት እመቤቲቱ ቡናው እስኪፈላ ከግድግዳው ላይ መስኮት የሚያህል ባለፍሬም ፎቶ መስቀያ አውርዳ በዳንቴል ወልወል አድርጋ ትጋብዘናለች። በፎቶው ውስጥ ሚስት ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ፤ገብረክርስቶስ ጫማ አድርጋ ቁጢጥ ብላ ትታያለች ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

የፖለቲካ ቋንቋችን

እጄን በሳሙና ከመታጠብ በተረፈኝ ጊዜ ለንጀራ የሚሆን ስራ እሰራለሁ፤ ማታ ማታ ደግሞ አፌ ላይ ነጭ ሽንኩርት፤ ትከሻየ ላይ ነጭ ጋቢ ጣል አድርጌ ዩቲውብ ላይ እጣዳለሁ፤ ከፊልሙም ከዘፈኑም ቀማምሼ ያገሬን ቃለመጠይቅ ወይም ውይይት መመልከት እጀምራለሁ:: አልናደድም፤ አላዝንም፤ እንቅልፍ ደርሶ ከነዚህ ስሜቶችማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ከፀሀይ በታች አሮጌ ነገር የለም ፤ ፀሃይ ራሷ በየሰኮንዱ ትታደሳለች፤ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፤ ተንጠራራሁና አይኔን ባይበሉባየ ጠራርጌ ከእምብርቴ በታች ያለውን ቃኘሁት፤ አጅሬ ከኔ በፊት ቀድሞኝ ተነስቱዋል ፤ የዛሬው ደግሞ የተለየ ነው፤ እስክንድር ነጋ ንግግር ባደረገ ቁጥር ባንዲራ ይዞ ከጀርባ እሚቆመውን ሰውየማንበብ ይቀጥሉ…

እህ እንዴት ነው ገዳዎ!

በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት የመጀመርያው የሰው ልጆች ስራ አደንና ፍራፍሬ መልቀም ነበር፤ አንድ ወንድ እና ሴት ተጣምረው ዱር ለዱር ይንከራተታሉ። እንጆሪ ለቅመው ወይም የዱር ፍየል አድነው በጋራ ይበላሉ፤ከእለታት አንድ ቀን ሴቲቱ ታረግዛለች፤ ሆዷ ገፍቶ እንደ ድሮው ዛፍ መውጣት ወይም መስክ በሩጫማንበብ ይቀጥሉ…

ድንጋይ ዳቦ ሆነ

አንዲት አረጋዊት ጥቁር ኢትዮጵያዊት ትመካበት የላት ባለፀጋ ዘመድ ፊቷ የለበሰ፤- ፅናት ላብና አመድ እሷ አለቃ ሆና፤ ክንዶቿን ቀጣሪ እሱዋ ድሃ ሆና ፤ የሀብታሞች ጧሪ:: እየተጋች አድራ እየለፋች ስትውል እድሜና ተስፋዋን፤ ያስተሳሰረው ውል ቢቀጥን ቢሳሳ ከሸረሪት ፈትል መሀረብ ዘርግታ ተዘከሩኝ ሳትልማንበብ ይቀጥሉ…