“ነፃ ሆነን ብንፈጠርም በየሄድንበት እንደታሰርን ነው” ይላል ሩሶ… “Man is born free, and everywhere he is in chains. One man thinks himself the master of others, but remains more of a slave than they are.” ~ Jean Jacques Rousseau …ማንበብ ይቀጥሉ…
የአብሲት ተራ ወጎች
ልጅነቴ ከተጓዘባቸው ፈለጎች አንዱ ‘እንጀራ መሸጥ’ ነው። ቡታጅራ ውስጥ ‘ሶርሴ ተራ’ በምትባል የገበያ ቦታ የእማማን ለምለም እንጀራ ከፈላጊው ጋር አገናኝ ነበር። አንድ ሰው ለብቻው የማይጨርሰውን ‘ግብዳ’ እንጀራ [ውሻ በቁልቁለት የማይስበው የሚባልለትን] የብር አምስትና አራት ሽጬያለሁ። 5ቱ ሁለት ብር ሲገባም በዚያማንበብ ይቀጥሉ…
ላንችይቱ
[Come out of the circle of time and into the circle of love. ~ Rumi] ~ ምንኛ ነው ግን… ‘የነገን ማወቅ ፈለግሁኝ’ ብሎ ምኞት… ዛሬ ላይ ሳይቆሙ ወደ ነግ መጎተት… የሚያውቁትን ጥለው በማያውቁት መሳብ… ምንኛ ነው ‘ነገን ላየው እጓጓለሁ’ ማለት…ማንበብ ይቀጥሉ…
ድልድዮቹን ተውልን
እመሃል ላይ ተገምሰው ማዶ ለማዶ የሚያተያዩን ሰባራ ድልድዮች እየበዙ ነው… አንዳንዶቹን ሆን ብለን ሰብረናቸዋል… አንዳንዶቹ በሌሎች ሰንኮፎቻችን ዳፋ ተሰብረዋል… ሌሎቹን ግን መሰበራቸውን እንኳ አልተረዳንም… ~ አንዳንዶች የሚሰብሩትን ድልድይ ፋይዳ በወቅት ስሜታቸው ትኩሳት ውስጥ ብቻ ስለሚመዝኑ የሰባሪነት ወኔ እንጂ የአስተዋይነት ስክነትማንበብ ይቀጥሉ…
Nothingness!!
መስመር መስራት ስትጀምር ወዲህና ወዲያን ትፈጥራለህ… አጥር መገንባት ስትጀምር ውስጥና ውጭ ትፈጥራለህ… ፍርድ መስጠት ስትጀምር ክፉና ደግ ትፈጥራለህ… በመስመር – አጥርና ፍርድህ ምክንያት የልዩነት ዜማ ሰርክ ይቀነቀናል… እንዲህ ‘የሆኑ’ እና እንዲያ ‘ያልሆኑ’ ክልል ይበጃል… ‘የኛ’ እና ‘የእነርሱ’ ምድብ ይሰራል። ሕይወትማንበብ ይቀጥሉ…
ልጅነቴን አፋልጉኝ
ማደግ በመሰለኝ ረግረግ ውስጥ የጠፋች ልጅነቴን አፋልጉኝ – ማወቅ በመሰለኝ ጥልቅ ውስጥ የተደበቀች ልጅነቴን አፋልጉኝ – ከድቅድቅ ጽልመት ውስጥ የዘነጋሁዋትን እውነት አፋልጉኝ… ~ ዕድሜ የሥጋ ኑረት መስፈሪያ እንጂ የውዷ ሕይወት መግለጫ አይደለም… ሕይወቴ ልጅነቴ ነው… ዕድሜ ደግሞ የልጅነቴን ንጽሕና የነጠቀኝማንበብ ይቀጥሉ…
ጠፍታ አገኘችኝ
የደመናው ጽልማሞት በዝናብ ፍርሃትና በቀጠሮ አለማክበር ስጋት መሃል አዕምሮዬን እያላጋብኝ ወደ ታክሲ መያዣው የማደርገውን ግስጋሴ ትቼ ቅርቤ ወዳለ ካፌ ዘለቅሁ… ፒያሳ ነኝ… ከመቀመጤ ሸገር እሪ ብላ አነባች… በጣም ከባድ ዝናብ መውረድ ጀመረ… “ሸበሌ እንገናኝ” ነበር ያለችኝ… ፍቅረኛዬ ናት… ‘ጥብቅ ጉዳይ’ማንበብ ይቀጥሉ…
ተ ላ ቀ ቅ
ከሕላዌው ጽንፍ አልባ እውነት ራስን የመነጠል ግብግብ። ከሆኑት መሆን ሌላ መሆንታን መሻት። ከአማናዊው እውነት ተናጥሎ በሃሳብ ደሴት መገለል። የኔ/ኛ፣ የእነርሱ፣ የነዚያ ባይነት ፍረጃ። ነኝነት ከሌላው የተለየ መሆንን ሲሰብክ መሆን /Being/ ቅዠት ውስጥ ይቧችራል። ነኝነት ጥግ ሲያሻትት የመሆን ቀለም ይደበዝዛል። የሆንከውንማንበብ ይቀጥሉ…
የሱፍ አበባ ነኝ
የብርሃን ጥገኛ ነኝ… እኔዬ ከብርሃን ውጭ ውበት የላትም… ብርሃን ሳጣ ይጨንቀኛል… ቅጠሎቼ ይጠነዝላሉ… ቅርንጫፎቼ ይኮሰምናሉ… የሱፍ አበባ ነኝ… በሕላዌ ገመድ ለተንጠለጠለችው ኑረት ጨለማና ብርሃን የማይዘለሉ ሃቆች ቢሆኑም እኔ ግን በብርሃን ፍቅር እንደተለከፍኩ አለሁ… ልክፍቱ “..መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ ስላልኩ የሚለቅማንበብ ይቀጥሉ…