ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 11)

እንዳልፈጠፈጥ ፈራሁ ቀና ብዬ እራሴን ለማረጋጋት  ሞከርሁ። ጥጉን ይዤ  እምዬ እሄን ጉዴን አላየሽ  እስተዛሬ ታውሬ ጋር አብሬ  ነው የኖርኩት አልሁ ለራሴ።  ትንሽ ተቀመጥሁና  ትንፋሽ ወስጄ መልሼ በሆዴ  ተኝቼ ቁልቁል ትመለከት  የበልሁ ሁኔታ አንጀቴን አላወሰው። እትዬ የ ባእድ  የአምልኮ ጠሎታቸውን ጨርሰውማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 10)

ሻወር ቤት ውስጥ ሆኜ ያለሁበት ክፍል ውስጥ ዘው ብለው ቲገቡ እኔኑ የተከተሉኝ መስሎኝ  ወደ ውስጥም ወደ ደጅም ትንፋሽ ማውጣት ተስኖኝ ፀጥ አልሁ። እሳቸው ግን እክፍሉ እንደገቡ ግድግዳዉ ላይ የተሰቀለውን  ትልቅ ስእል  ተግድግዳው ላይ አወረዱ። ደሞ ቀጠሉና ቀለሙ ተግድግዳው ጋር የሚመሳሰልማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 9)

ቀጥታ ወደ ክፍሌ ገባሁ የሰውየው አስተያየት እና አስፈሪ ገፅታ ተፊቴ አልጠፋ አለኝ።ትናንት ያንን ምስኪን ደሀ በልሁን አስሬ እስሩ እየሄድኩ ተፖሊሶቹ ጋር  ታልሄዱኩ እያልሁ ትጨቀጭቀው ሰውየው አይቶን ታይሆን አይቀርም እትዬ  በልሁ ሚስጥር ያወጣ መስሏቸው የጨከኑበት። አይ እትዬ ምን አይነት ጨኳኝ ሰውማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 8)

ሰሚ የለለው ጩኸት ምን ያህል ውስጥን እንደሚያቆስል የደረሰበት ብቻ ታልሆነ ማን ይረዳዋል?።ባይወጣልኝም እስቲደክመኝ እለቀስሁ አልጋዬ ላይ በደረቴ እንደተደፋሁ በልሁን ተከፋ ጉዳት እንዲጠብቀው አምላኬን እየለመንሁና እየተማፀንሁ ቆየሁና ምናልባት ተኔ በፊት እዚህ ቤት የቤት ሰራተኛ ተነበሩት ውስጥ ምናልባት ምናልባት እክፍሉ ውስጥ የደበቁትማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦7)

አድፍጬ  ትጠባበቅ የትዬ ቤት አንፖል ታይጠፋ  እኩለ ሊሊት ሆነ።ተትዬ ባህሪ የማውቀው መብራት ታይጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸው ነው።ግራ ገባኝ እስታሁን አልተኙም ወይስ ታያጠፉ እንቅልፍ ጥሏቸው ይሆን ?ጨነቀኝ። በጭንቀት ትወዛወዝ  ገርበብ ያለው የትዬ ምኝታ ቤት ቲከፈት ሰማሁ።ቆሌዬ ተላዬ ላይ ረገፈ። ተተቀመጥኩበት  ተበሩ ስርማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 6)

እራሴን መሆን ተስኖኝ ተዝለፍልፌ መሬት እንደደረስኩ እትዬ “አንቺ ምን ሆነሻል”  አሉና  አምባረቁብኝ ።  ተንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ሰመመን ውስጥ  ሆኜ ምድር ምድሪቱን ትመለከት በልሁ ተወደ ጀርባዬ እየሮጠ መጣና …”እይይ እቺ ሚስኪን ልጅ  እንዲሁ እትዬ ክፉ እንዳይገጥማቸው ብላ ትትጨነቅ ነው የዋለችው አይዞሽማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 5)

እሄን ግዜ በልሁ “እዚህ ቤት ሰራተኛች ሲገቡ እንጂ ሲወጡ  አይቼ አላውቅም” ያለኝ ነገር  ተትዬ መሰወር ጋር ተገናኝቶ በመላ ሰውነቴ ትኩሳት ከፍርሀት ጋር ለቀቀብኝ። ፓሊሶቹ ስራቸውን አገባደው ለምሄድ ሲሰናዱ አየሁና እየተጣደፍኩ ወደ በልሁ ጋር ሄጄ እኔ ይችን ቀን እዚህ ቤት ከማድርማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 4)

በልሁ ፈራ ተባ እያለ በሩን ቲከፍተው አንድ አማላይ ግርማ ሞገስ የተላበሰሰ ፓሊስ “ጤና ይስጥልኝ” አለና ወደ ውስጥ ዘለቀ ሶስት አምሳያዋቹ ተከተሉት ሁለት አምሳያዋቹ ደሞ ሳይገቡ እዛው ደጅ ላይ ቆመው ሰፈሩን መቃኘት ጀመሩ። “የቤቱ ባለቤት ይኖራሉ?” ማንም የለም ጌታዬ አልኩኝ ቀድሜማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር … (ክፍል፦3)

ሀሎ…ሀሎ…ሀሎ ማን ልበል…  ድምጥ የለም። እትዬ በጭንቀት  ጆሮዬ  ላይ ወደ  ለጠፍኩት  ስልክ  ጠጋ አሉና የደዋዩን  ድምጥ ለመስማት ሞከሩ …ሀሎ …..ማን ልበል ሀሎ….  አሁንም  ድምጥ  የለም  እትዬ ተፊቴ ቆመው  እንድዘጋው በምልክት አዘዙኝ ። እንደዘገሁት ስልኩን በሁለት እጃቸው ወደ ላይ አነሱና ተመሬትማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር … (ክፍል፦2)

ጋሼ  ከታሰሩ ቡሀላ የትዬ ነገረስራ ሁሉ  ያስፈራል  ያስጨንቃል አሁን ለታ ለስንት አመት ግድግዳው ላይ የተሰቀለው ሰአት የለመደውን ቆጠራ  ቀጥሏል  ቃ….ቃ……ቃ…. ቃ  ይላል  ወድያው እትየ ተፈዘዙበት አለም ተመለሱና  ” እሄ የግድግዳ ሰአት ድምፁ ሊያሳብደኝ ነው አውርጄ ሳልከሰክሰው  አውርጂና አጥፊልኝ!  አሉኝ የጆሮዬማንበብ ይቀጥሉ…