ለሙዚቃ የመነነው ኤሊያስ!

  በዓሉ ግርማ ከሀዲ ደራሲ መሆኑን የነገረኝ የቀድሞ መምህሬ ቴዎድሮስ ገብሬ ነበር።“ከአድማስ ባሻገርን” ካነበብኩ በኋላ እኔም የእሱ ጭፍራ ሆንኩኝ። ታላቁን ደራሲ በክህደት ወነጀልኩኝ። ተስፋ ያጣውን አበራ ወርቁ ለምን ሲል በልቦለዱ መቋጫ ላይ በጉልበት ብሩሽ አስጨብጦ ከብርሃን አገናኘው አልኩኝ። ፍርሃቱን እረገምኩኝ።ማንበብ ይቀጥሉ…