መጋቢት 17/1988 (መጋቢት 9/ 1980) እኩለ ሌሊት። በዚያች ደረቅ ሌሊት ሕዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ (ሻዕቢያ) ሳይጠበቅ የናደውን እዝ ወረረ። የህዝባዊት ኢትዮጵያ አብዮታዊ ሰራዊትም ይዞታውን ለማስጠበቅ ተከላከለ። ይሁንና በለስ ሊቀናው አልቻለም። ሻዕቢያ ቀደም ብሎ ያገኘውን መረጃ በሚገባ ሊጠቀምበት ስለቻለ የአብዮታዊ ሰራዊትንማንበብ ይቀጥሉ…
አቶ ሀዲስ አለማየሁ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች
አቶ ሀዲስ አለማየሁ በልቦለድ ፀሀፊነታቸው የተጋረደ የፖለቲካ ሰብእና ነበራቸው። በተለያየ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች እንደ ደረቅ ትንቢት የሚቆጠሩ ነበሩ። ለዛሬ: መጋቢት 19: 1985 አመተ ምህረት ባዲሳባ ዩንቨርሲቲ ካቀረቡት ንግግር የሚከተለውን ለመቀንጨብ ወደድሁ። በጥሞና አንብበን በሰከነ መንፈስ እንወያይበት። የንግግሩማንበብ ይቀጥሉ…
ምንሽን
የሰው አገር ሙጥኝ ብየ-በወጣሁበት እንዳልቀር ሀገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ -ግና ምንድር ነው ማፍቀር? እንዳስመሳይ አዝማሪ -ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስተዛሬ ከጣትሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መች ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላ ስለቅምማንበብ ይቀጥሉ…
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
ጥቂት ስለ “አዳል”
በመካከለኛው የታሪክ ዘመን (Medieval Era) ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን፣ ጅቡቲን፣ ሶማሊላንድን እና ሶማሊያን በሚያቅፈው የአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና የተለያየ ቅርጽና አወቃቀር የነበራቸው መንግሥታት ተመሥርተዋል። ከነዚያ መንግሥታት መካከል ከአስር የማያንሱት የሙስሊም ሱልጣኔቶች ነበሩ። ከሱልጣኔቶቹ መካከል ስሙ በጣም ገንኖ የነበረውና በአፍሪቃ ቀንድ ሕዝቦች ታሪክ፣ ጂኦ-ፖለቲካማንበብ ይቀጥሉ…
“ሁ ኢዝ ባድ?!”
ይህቺ ጭዌ ከዚህ ቀደም ተፖስታ የነበረ ሲሆን ሰሞኑን ከሚከበረው የአጼ ሚኒሊክ ልደትና የጠ/ሚ መለስ ሙት አመት አንጻር ለሁለቱም ቀደምት መሪዎች ወዳጅም ሆነ ጠላት ሚዛናዊ ነው በሚል በአድማጭ ጥያቄ በድጋሚ የቀረበች ነች።ጽሁፉ ትንሽ ረዘም ይላል ያው የምታነቡት ካጣችሁ ብቻ ተደበሩበት። መቼቱማንበብ ይቀጥሉ…
የአርሲ ዐጃኢባት
እኛ (እደግመዋለሁ “እኛ”፣ “ኑቲ”፣ “ናህኑ”) የኢትኖግራፊ ፈረሳችንን ተሳፍረን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከመሀል እስከ ሰሜን መጋለብ ሱስ የሆነብን ጸሐፊ ከሀረር መሆናችንን ታውቃላችሁ አይደል? ታዲያ እኛ (አሁንም እደግመዋለሁ “እኛ”) ወደ ሌሎቹ ስፍራዎች ስንጋልብ የነበረው ከሌሎች አካባቢዎች ሁሉ የሚቀርበንን አንድ ጎረቤታችንን እያለፍን ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…
እድሜዬ እና የኢትዮጲያ እርምጃ!
ሰላም ነው ጋይስ! እንግዲህ ቅዳሜ እለት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ያለፈውን የ 35ኛ አመት የልደት በአሌን በማስመልከት ብዙዎች ” እድሜህ ስንት ነው?” በማለት በጠየቃችሁት መሰረት ስለ እድሜዬ የሚከተለውን መግለጫ ለመስጠት ተገድጃለሁ። ግና ለአንባቢ የተወለድኩበትን ዓመተ ምህረት በቀጥታ ከመናገር ይልቅ እስከዛሬዋ እለትማንበብ ይቀጥሉ…
ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጅማ (ክፍል ሁለት)
እነሆ ከተሚማ ጋር የጂማን ምድር “ሽርርርር” እያልንበት ነው። ሆኖም “ተሚማ” የትናንትናው ሙገሳ አንሶኛል ብላለች። “የነየታችሁት ሐጃ ሞልቶላችሁ በደስታ እንድትፍለቀለቁ ካሻችሁ ሙገሳውን ጨመርመር አድርጉልኝ” ትላለች። ታዲያ እኛም አላንገራገርንም። “ምን ገዶን! አንቺ ሰኚ ሞቲ! ሙገሳ በየዓይነቱ ይኸውልሽ” ብለን በድጋሚ መወድሳችንን ልንደረድርላት ተዘጋጅተናል።ማንበብ ይቀጥሉ…
መረራ ጉዲናን ሳስታውስ
በ1988 የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ESLCE) እንደወሰድኩ ነው። ዕለቱ ከሚያዚያ ወር መአልት አንዱ መሆኑ ይታወሰኛል። በዚያች ዕለት የጀርመን ድምጽ ራድዮ ከቀደሙት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለየ ዓላማን ያነገበ ድርጅት መቋቋሙን ዘገበ። የድርጅቱ መስራች የሆኑት ግለሰብ የተናገሩትንም ቀንጨብ አድርጎ አስደመጠን። በጉዳዩ ዙሪያማንበብ ይቀጥሉ…