ይህቺ ጭዌ ከዚህ ቀደም ተፖስታ የነበረ ሲሆን ሰሞኑን ከሚከበረው የአጼ ሚኒሊክ ልደትና የጠ/ሚ መለስ ሙት አመት አንጻር ለሁለቱም ቀደምት መሪዎች ወዳጅም ሆነ ጠላት ሚዛናዊ ነው በሚል በአድማጭ ጥያቄ በድጋሚ የቀረበች ነች።ጽሁፉ ትንሽ ረዘም ይላል ያው የምታነቡት ካጣችሁ ብቻ ተደበሩበት። መቼቱማንበብ ይቀጥሉ…
ጠፍታ አገኘችኝ
የደመናው ጽልማሞት በዝናብ ፍርሃትና በቀጠሮ አለማክበር ስጋት መሃል አዕምሮዬን እያላጋብኝ ወደ ታክሲ መያዣው የማደርገውን ግስጋሴ ትቼ ቅርቤ ወዳለ ካፌ ዘለቅሁ… ፒያሳ ነኝ… ከመቀመጤ ሸገር እሪ ብላ አነባች… በጣም ከባድ ዝናብ መውረድ ጀመረ… “ሸበሌ እንገናኝ” ነበር ያለችኝ… ፍቅረኛዬ ናት… ‘ጥብቅ ጉዳይ’ማንበብ ይቀጥሉ…
ብርሃን ፍለጋ
ወይንሸት የመጀመርያ ልጅ ነች። ዕድሜዋ አስር ሆኗል። እኩዮቿ ከክፍል ወደ ክፍል በተዘዋወሩ ቁጥር እሷ ግን ታናናሾቿን በመሸከም ነው ከዓመት ወደ ዓመት የምትሸጋገረው! ወላጆቿ ሞግዚት የመቅጠር አቅም የላቸውም፤ ለዚህም ነው ወይንሸትን ወደ ፊደል ገበታ ያልሰደዷት። አባቷ ‘ሰርቶ በይ!’ የሚል ድምፅ ወደሰማበትማንበብ ይቀጥሉ…
እድሜዬ እና የኢትዮጲያ እርምጃ!
ሰላም ነው ጋይስ! እንግዲህ ቅዳሜ እለት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ያለፈውን የ 35ኛ አመት የልደት በአሌን በማስመልከት ብዙዎች ” እድሜህ ስንት ነው?” በማለት በጠየቃችሁት መሰረት ስለ እድሜዬ የሚከተለውን መግለጫ ለመስጠት ተገድጃለሁ። ግና ለአንባቢ የተወለድኩበትን ዓመተ ምህረት በቀጥታ ከመናገር ይልቅ እስከዛሬዋ እለትማንበብ ይቀጥሉ…
ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጅማ (ክፍል ሁለት)
እነሆ ከተሚማ ጋር የጂማን ምድር “ሽርርርር” እያልንበት ነው። ሆኖም “ተሚማ” የትናንትናው ሙገሳ አንሶኛል ብላለች። “የነየታችሁት ሐጃ ሞልቶላችሁ በደስታ እንድትፍለቀለቁ ካሻችሁ ሙገሳውን ጨመርመር አድርጉልኝ” ትላለች። ታዲያ እኛም አላንገራገርንም። “ምን ገዶን! አንቺ ሰኚ ሞቲ! ሙገሳ በየዓይነቱ ይኸውልሽ” ብለን በድጋሚ መወድሳችንን ልንደረድርላት ተዘጋጅተናል።ማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል አራት)
“ልትነግሪኝ የምትፈልጊው ነገር አለሽ?” “ማለት? ስለምን?” “እኔ እንጃ ቦስ አባትሽ እዚህ ቢሮ እግራቸው ከረገጠ ቀን ጀምሮ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ፍፁም ልክ አይደለሽም። ያዘንሽ ያዘንሽ ፣ የተከፋሽ ፣ የሆነ ነገር ያደከመሽ አይነት ነው የምትመስዪው።” ሲለኝ ለቅፅበት ያደከመኝን ሁሉ ልነግረው ዳድቶኝ ነበር።ማንበብ ይቀጥሉ…
“ስለ ቅዳሜ ሲባል ስለ ‘ሁድ ካወራን ተሳስተናል!”
እኔን መምከርና መርገም አሪፍ የስተርጅና ጊዜ መደበርያ ከሆነለት ከፋዘር ጋር እንደተለመደው ሶስት ከባድ የምክር እና የተግሳፅ ሰኣታትን አሳለፍኩ።እንዳረዛዘሙ አመታትን ብል ይቀለኛል ለነገሩ።የማዘርን ጉሽ ጠላ በላይ በላይ እየነፋ፣የአተላውን ግርድፍ በላዬ ላይ እየተፋ መጠጥ እርም እንድል ካልተሳሳትኩ ለመቶ አስራ ሰባተኛ ጊዜ ዛሬምማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሦስት)
ከሀያ ዓመት በላይ የሆናቸው በወጣትነቷ ውዷ ከፃፈላት ደብዳቤዎች ዛሬም ድረስ አብረዋት ያሉ እያንዳንዱን በቃሏ የምታውቃቸው 23 የፍቅር ደብዳቤዎች አሏት። ሁሉንም ከነተፃፉበት ቀን ሳይቀር እኔም በቃሌ አውቃቸዋለሁ። እንደዚህ ከፍ ያለ ፍቅር መቋጫው እንዴት አስከፊ መለያየት እንደሆነ ሳስብ ይገርመኛል። እሷ ዛሬን ማሰብምማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሁለት)
“አቤት?” አልኩት ለሰላምታ የዘረጋውን እጁን ችላ ብዬ ወንበሬ ላይ እየተቀመጥኩ። ፀጉሩ አልፎ አልፎ ከመሸበቱ ውጪ ብዙም አልተለወጠም። “ደህና ነሽ ሚሚሾ?” “ምን ፈልገህ ነው የመጣኸው? ደህና መሆኔ አሳስቦህ አይሆንም መቼም!! የልጅህ ሰርግ ጥሪ ወረቀት እንደደረሰኝ ለማረጋገጥ ከሆነ ደርሶኛል። እማም ደርሷታል። ጨርቄንማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው
“ተሳፋሪዎቻችን ይህ የበረራ ቁጥር 206 ነው… … ” ጭንቅላቷ እየሸወዳት እንደሆነ የማውቀው እንዲህ ማለት ስትጀምር ነው። በግልቡ እብደቷ እየጀመራት ነው ማለት ነው። እናቴ ናት!! ይሄን ሀረግ ማለት ከጀመረች ትርጉሙ የዛሬ 20 ዓመት ወደ ኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆስተስ የነበረችበት ዘመንማንበብ ይቀጥሉ…