በውበት ሳሎኑ ውስጥ – 3

ውድ አንባብያን! <ያልተቀበልናቸው>የተሰኘው አዲሱ መጽሐፌን በየመጻሕፍት መደብሩና በየአዙዋሪዎቹ እጅ ታገኙታላችሁ።መጽሐፉ በእጃችሁ እስኪገባ፣አሁንም አንድ ቁንጽል ጻሪክ ከመሐፉ ልጋብዛችሁ።  በውበት ሳሎኑ ውስጥ – 3 ——- የተቀመጥኩት መግቢያው በር አጠገብ ነበር። የሆነ ሰው፣ እጀርባዬ እንደቆመ ትከሻዬ ነግሮኝ ቀና አልኩ። ቀና ስል፣ ከዚህ ቀደምማንበብ ይቀጥሉ…

መረራ ጉዲናን ሳስታውስ

በ1988 የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ESLCE) እንደወሰድኩ ነው። ዕለቱ ከሚያዚያ ወር መአልት አንዱ መሆኑ ይታወሰኛል። በዚያች ዕለት የጀርመን ድምጽ ራድዮ ከቀደሙት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለየ ዓላማን ያነገበ ድርጅት መቋቋሙን ዘገበ። የድርጅቱ መስራች የሆኑት ግለሰብ የተናገሩትንም ቀንጨብ አድርጎ አስደመጠን። በጉዳዩ ዙሪያማንበብ ይቀጥሉ…

ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጅማ!

በለምለሚቷ ምድራችን ላይ እየተሽከረከረ ዚያራ ማድረግ ወጉ የሆነው የኢትኖግራፊ ፈረሳችን ታሪካዊቷን ጅማንና ህዝቧን መጎብኘት አሰኘው። እኛም “አበጀህ! ጥሩ ሀገር መርጠሃል” በማለት መረቅነው። ፈረሳችንም የደቡብ ምዕራብ አቅጣጫን ይዞ ገሰገሰ። ከጊቤ ዉሃ ከተጎነጨ በኋላም ወደ ታሪካዊቷ ቀበሌ ሰተት ብሎ ገባ። ጅማ! የአባጅፋርማንበብ ይቀጥሉ…

ወለጋ እና ሌንሳ ጉዲና

ከዚህ በፊት ስለወለጋ የሚያትት አነስተኛ ጽሑፍ በዚህ ግድግዳ ላይ ለጥፌ ነበር። ይሁንና ያቺ ጽሑፍ ለወለጋ ክብር የምትመጥን አልመሰለኝም። ብዙ ድርሳናትን ለሚያስጽፈው ምድር ትንሹን ብቻ እንደ መወርወር ነው። በመሆኑም በዛሬው የኢትኖግራፊ ጉዞአችን ወለጋን ደግመን ልንዘይረው ተዘጋጅተናል። ጉዞ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ! ዳይ!ማንበብ ይቀጥሉ…

የኢትኖግራፊ ጉዞ ወደ ጎጃም (ክፍል ሁለት)

ጎጃምን ከሌሎች የቀድሞ ክፍለ ሀገሮቻችን ለየት የሚያደርገው ዙሪያውን በዐባይ ወንዝ የታጠረ መሆኑ ነው። ከጣና ሐይቅ በስተምዕራብ ራቅ ብሎ ካለው የግልገል ዐባይ መነሻና በሱዳን ድንበር መካከል ከሚገኘው ክፍት መሬት በስተቀር ክፍለ ሀገሩ በሙሉ በዐባይ የተከበበ ነው። እርግጥ በወንዝ የታጠሩ ሌሎች ክፍለማንበብ ይቀጥሉ…

ተመራቂዉ ልጅ

ከተመረቅኩኝ አንድ ወር አለፈኝ።(በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ዉሸት) ……የሆነ ልጅ እንደጻፈዉ እስካሁን ስራ ለምን አልያዝኩም ብዬ አላማርርም። እንኳንስ እኔ መካከለኛ ግሬድ ካላቸዉ ተማሪዎች ተርታ የምመደበዉ ይቅርና ሰቃያችንም ስራ አልያዘም! ይልቁንስ የሚያስጨንቀኝ ሰፈራችን ከእኔ ጋር በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የተመረቀዉ የአንድ አመትማንበብ ይቀጥሉ…

የኢትኖግራፊ ጉዞ ወደ ጎጃም

ያ በእውቀቱ ስዩም የሚሉት ጎጃሜ ብላቴና አምናና ዘንድሮ የኛዋን ኦሮሚያን በብዕር መነካካቱን አብዝቷል። እስከ ዛሬ ድረስ “ይሄ ልጅ ለምን አያርፍልንም? እኛም እርሱን ስላፈራችው ጎጃም መጻፍ የማንችል መሰለው እንዴ” እያልን ከራሳችን ጋር ስንነጋገር ቆይተናል (“እኛ” ወልደ-ገለምሶ ዘብሔረ ሀረርጌ በመሆናችን ባሰኘኝ ጊዜማንበብ ይቀጥሉ…

ባይተዋሩ ግመል

አንዳንድ ድምጻውያን አዲስ አልበም ሊያወጡ ሲሉ ነጠላ ዜማቸውን ቀደም ብለው እንደሚለቁት፣ከአዲሱ ‹ያልተቀበልናቸው› ከተሰኘው መጽሐፌ ከአንዱ ወግ ቀንጭቤ ጀባ ልላችሁ ወደድኩ።  ባይተዋሩ ግመል (….) ግመሉ የተገለለ ነው – ከወንዙ ተነጥሎ፣ ከወገኑ ተለይቶ፣ ለተሻለ ኑሮ፣ ወይም ለተሻለ የመንፈስ ፀጥታ፣ ወይም ለተሻለ ዕውቀትማንበብ ይቀጥሉ…

ሰርፕራይዝ

(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ትናንትና የልደት በአሌን በማስመልከት ከወዳጆቼ አንዱ ወይም አንዲቱ ሰርፕራይዝ ያደርገኛል/ታረገኛለች ብየ ብጠብቅ ብጠብቅ ወፍ የለም። ግን ተስፋ አልቆረጥኩም። ባካባቢየ ወደሚገኝ አንድ ያበሻ ሬስቶራንት ሂጄ ተቀመጥሁ። ያዘዝኩት ሰላጣ እስኪመጣ ፌስ ቡኬን ለኮስኩ። አንዱ በቀጥታ ካዲሳባ online ላይ ጠመደኝ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ዓሊ ቢራ፣ የሸዋሉል መንግሥቱ እና “ዮቢ ሐደሶ ሊባነታ”

ዛሬ ስለምን የማወጋችሁ ይመስላችኋል? ስለ“ፈስ” ነው የምንጨዋወተው። አዎን ስለ “ፈስ” ነው! ስለርሱ መጻፍ አይቻልም እንዴ? ስለርሱ ብንወያይ ነውረኛ እንሆናለን? የፈለጋችሁን በሉኝ! ስለ “ፈስ” ልጽፍ አሐዱ ብያለሁ። የጀመርኩትንም ሳልጨርስ አላቆመም። ደግነቱ ስለሚገማ “ፈስ” አይደለም የማወጋችሁ (ስለዚህ አፍንጫችሁን አትያዙ! ቂቂቂቂቂ….)። ስለማይገማ “ፈስ”ማንበብ ይቀጥሉ…