ሸምበቆ እና ሸንኮሬ

አመት ከማይሞላው ጊዜ በፊት ለመስክ ስራ ወጣ ስል እግረ መንገዴን ‹‹የአባቴን ሀገር እና ዘመዶች ልይ›› ብዬ ከተወለደበት የገጠር መንደር ጎራ ብዬ ነበር። በቅጡ ያልወጠንኩት የእግረ መንገድ ጉዞዬ ወሬ አባቴ ዘመዶች ዘንድ ከብርሃን ፈጥኖ ደረሰና እኔን ለማስተናገድ ወጥነው ሲንገላቱብኝ ሰነበቱ። በተለይማንበብ ይቀጥሉ…

ለሊዮ ቶሎይስቶይ የተጻፈ ደብዳቤ

 (እውነተኛ የሰሙኑ ገጠመኝ) አንድ ወዳጄ ከሳምንታት በፊት አንድ ቴአትር ይጽፍና በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት ቴአትር ቤቶች ወደ አንዱ ይሄዳል፡፡ ድርሰቱን ለግምገማ እንዲያስገባ ይነገረዋል፡፡ አስገባ፡፡ በቀደም ዕለት የግምገማውን ውጤት ለማየት ወደ ቤተ ተውኔቱ ያመራል፡፡ መዝገብ ቤቶቹም ‹የግምገማው ውጤት ደርሷል፡፡ መታወቂያዎትን አሳይተውማንበብ ይቀጥሉ…

ገነት ይቅርብኝ

“እንለያይ?” ስላት አስቀድማ ውብ ከንፈሮቿን ገለጥ አድርጋ የሲኦል መቀመቅ ውስጥ ሰምጬ እንኳን ቢሆን ንዳዱን የሚያዘነጋኝን ጥርሶቿን አሳየችኝ። ቀጥሎ ግን የእውነቴን መሆኑን ስታውቅ ሳሳዝናት ደፍሬ ማየት የሚከብደኝ ውብ ዓይኗ ደፈራረሰ። “ማለት?” አለችኝ በተሰበረ እና የአፏን በር ለቆ ለመውጣት በሚቅለሰለስ ድምፅ “እንድንለያይማንበብ ይቀጥሉ…

“የፖለቲካ ትልቁ ጥቅም ሽፋን መስጠቱ ነው”

ታውቃላችሁ ፖለቲከኞቻችን ትልልቅ ነገር እየተናገሩ ይማርኩናል። ጋዜጣ፣ ሬዲዮና ቲቪ አስደግፈው ያማልሉናል። አንድ ዛፍ ይተክሉና ስለዚህ ስለተከሉት ዛፍ አስር ሰአት ያወራሉ። ይሄን የሚሰሙ የዋሃን እና ቂሎች፣ ዛፍ ብቻ ሳይሆን በቃ ደን ያደገ ይመስላቸዋል። ድርጊቱ ደቃቃ ቢሆንም ከጥዝጠዛው ብዛት የእውነት ትልቅ ይመስላቸዋል።ማንበብ ይቀጥሉ…

ከአሸናፊዎች መዳፍ ወደ የተሸናፊዎች ወገብ

‹ሰላም ከተሸናፊዎች ወገብ እንጂ ከአሸናፊዎች መዳፍ አትገኝም› የሚል ወርቃማ አባባል አላቸው የካናዳ ጥንታውያን ሕዝቦች (First Nations)። አደን ልዩ ችሎታቸው የነበረውና በዚህች ሀገር ከሺ ዓመታት በፊት ሠፍረው መኖር የጀመሩት እነዚህ ሕዝቦች አያሌ የእርስ በርስ ጦርነቶችንና ችግሮችን ለመፍታት የቻሉት በዚህ ምክንያት እንደነበረማንበብ ይቀጥሉ…

ረከቦት ጎዳና

ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ አዲሳበባ ድምጻዊት ከተማ ናት ። አዱ ገነት ውስጥ ፤ ከመኪና የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በብዛት፤ በሥራ ላይ የሚውለው ክላክሱ ነው። እንዲያው ሸገር ውስጥ መኪና- ነፊ እንጂ መኪና- ነጂ ያለ አይመስለኝም ። አንድ አሽከርካሪ ቆንጆ እግረኛ ሲመለከት ምሥራቅማንበብ ይቀጥሉ…

የመታወቂያው ጉዳይ (አራተኛው ሙከራ)

“ሚስተር ኤክስን ያያችሁ” መታወቂያዬ ላይ በግድ የተፃፈብኝን የብሔር ማንነት ዜግነት ኢትዮጵያዊ ለማስባል ጥረት ያደረግኩበትን የባለፈውን ሳምንት የሦስተኛ ቀን ሙከራዬን ትረካ ያበቃሁት ከክፍለ ከተማው (በዘልማድ እንደሚባለው አውራጃ) ፍርድ ቤት ወደ ፌደራል ፍርድ ቤት ጉዳዬን እንዳቀርብ መላኬን ገልጬ ነበር። የዛሬውን ሙከራዬን እነሆ፡-ማንበብ ይቀጥሉ…

ዳግማዊ ስቅላት

የመሲሁ ስቅየት ግርፊያ ስቅላቱ አምላክ ነኝ ስላለ በድምቀት ተሳለ የኛንስ ስቅላት ማነው ያስተዋለ? ተመልካች ጠፍቶ እንጂ ዐይን የሚቸረን እኛም መስቀል ላይ ነን፣ ቄሳራዊ ሚስማር ዘልቆ የቸነከረን ዘውትር ዱላ እና አሳር ዘውትር ችንካር ሚስማር የሚገዘግዘን የሚጠዘጥዘን እኛም ክርስቶስ ነን! ሺ ዱላማንበብ ይቀጥሉ…

መዳፍና ዓይን

“እጅ እድፉን ያየበትን አይን ጉድፍ ያፀዳል” ተቆራኝተው የኖሩት የአካል ክፍሎቻችን በእድሜ ብዛት ሲወራረሱ “እጅ አይንን ተክቶ፥ አይን ግን እጅን ይተካ ዘንድ አይቻለውም” ስል ያሰብኩት ዛሬ በምተርክላችሁ ገጠመኜ ነው። ለፊልም ስራ ባህርዳር ከተማ ዙሪያ በነበርኩበት ወቅት እንዲህም ሆነ። ፊልሙ – የገጠርማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

አሪፍ የፍቅር ግጥም ጽፌ ለመለጠፍ አስቤ ነበር። ግን ብለው ብሠራው “ እኔ እምልሽ ውዴ” ከሚለው ቃል ውጭ ጠብ ሊልኝ አልቻለም። እኔ እምልሽ ውዴ! ብለው ሳይጀምሩ- ስለፍቅር መጻፍ አይቻልም እንዴ? አንዳንድ ባለንጀሮቼ በውስጥ መሥመር ይሄን ድብርታም ዘመን እንዴት እያሳለፍከው ነው ምናምንማንበብ ይቀጥሉ…