ሰዎች ይመስሉኛል። በጎችም ይመስሉኛል። ሰዎች ብዬ ስጠራቸው አቤት ይላሉ። በጎች ብዬ ስጠራቸውም አቤት ይላሉ። ሰዎች ናቸው በጎች? በቡድን ነው የሚኖሩት። በቡድንን ይንቀሳቀሳሉ።እንደማንነታቸው ሁሉ አንዳቸውን ከአንዳቸው ለመለየት ከባድ ነው። ጠጋ ብዬ እረኛቸውን ጠየኩት። “አልገባኝም በጎች ናቸው ሰዎች? ” ፈገግ ብሎ መለሰልኝ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ስሚ!
ስሚ መስሚያ ካለሽ። ከሰማሽ ደሞ ተስማሚ፤ ወዲያ ሂጂልኝ እስቲ። ማነሽ እውነት ነኝ የምትይ፣ እስቲ ስሚን የስንቱን አለመስማት እንችላለን? መንግስት አይሰማን፣ ፈጣሪ አይሰማን፣ አንቺ አትሰሚን… ኸረ እስቲ አንቺ እንኳን?!! ማን ነበረ ስምሽ? “እውነት ” ነው አይደል? እውነቱን ልንገርሽ፣ በደረስኩበት ባትደርሺ ደስማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱ ካድሬዎቹ
ሁለቱ ካድሬዎች የማነ እና ዳንኤል ካድሬዎች ናቸው። ይሁኑዋ ታዲያ! ካድሬ በበዛበትሀገር እነገሌ ካድሬ ናቸው ማለት ምንድነው? የማነ እና ዳንኤል ጓደኛሞችም ናቸው፤ ውሏቸው አንድ ላይ ነው፣ ወሬያቸውም አንድ ዓይነት። ስለ ልማቱ ያወራሉ፣ ያደጉትም፣ ያላደጉትም ፣የማያድጉትም ከኢትዮጵያ መውሰድ ሰላለባቸው ተሞክሮ ያወራሉ፣ አዲስማንበብ ይቀጥሉ…
የዚህ ትውልድ አባል ነኝ!
በመውደድ ወይ በመጥላት አልፍቀውም። ያለፈው ትውልድ ውላጅ ነኝ። የመጪው ትውልድ ወላጅ ነኝ። ያለፈው ትውልድ “አዬ ልጅ” እያለ ያሾፍብኛል፤ መጪው ትውልድ ይኮርጅኛል( ወደፊት “አይ አባት” ብሎ ይስቅብኝ ይሆናል -ግድ አይሰጠኝም) ለሁሉ ፈጣን ነኝ። ሁሉን በፍጥነት አይቼ በፍጥነት አልፋለሁ። ችክ ማለት አልወድም።ማንበብ ይቀጥሉ…
መረቅ
(ስሜቴን ለመግለፅ እንጂ፣ እንዳይንዛዛ( እንዳልንዛዛ) ሁለት ወይ ሶስት ጊዜ ቆራርጬ ለመፖሰት እገደዳለሁ) ክብነት(ሙሉዕነት) በመረቅ የመፅሓፉ ሀይለኛ ጉልበት እዚህ ጋር አለ።አዳም የህይወትን ክብነት ለማሳየት ገፀባህሪያቱንና ታሪክን በመጠቀም እንጀራውን ይጋግራል። ሀ. በገፀባህሪቱ፡― መፅሐፉ አራት ዋና ገፀባህሪያት አሉት።አራት(ምናልባትም “ዐራት”) የምልዑነት መገለጫ ነው። በማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት እህትማማቾች ወግ
የዛሬ ወር ተኩል ገደማ ለሳምንታት ቆይታ ወደ አሜሪካ ሄጄ ነበር፡፡ የጉዞ ሃሳቤን የሰሙ እዚህም አዚያም ያሉ ዘመድና ወዳጆቼ እኔ ‹‹ልዋጭ ልዋጭ›› የምለውን የእቃ ውሰጂና አምጪልን ጥያቄያቸውን ጀመሩ፡፡ በርበሬና ሽሮን በጋላክሲ ስልክና በሌቫይስ ጅንስ የመለወጥ ጥያቄ፡፡ ቡላና ኮሰረትን በናይኪ ስኒከርና በሬይባንማንበብ ይቀጥሉ…
በመጨረሻም…
በመጨረሻም ራሴን ላጠፋ ነው። ቃሉ ራሱ ደስ ሲል! ራስን ማጥፋት!! ፓለቲከኞች “የራስን ዕድል በራስ መወሰን ” እንደሚሉት ነው። ከህይወት ምን ቀረኝ? ምንም! አንድ የቀረኝ ነገር ራሴን የማጥፋት ድርጊት ብቻ ነው። ከዛ በኋላ ሀገሬ ሞት ነው። ከሞት ግድግዳ ወዲህ ምንም የሚጎትተኝማንበብ ይቀጥሉ…
ላንቺ ግጥም እየፃፍኩ ነበር!
የሆነ የዓለም ጥግ ላይ ህፃናት በረሃብ ሲያልቁ እኔ ላንቺ ግጥም እየፃፍኩ ነበር። ሁሉም ሲያድጉ አንቺን ማግኘት እንደማይችሉ ስለገባችው እንደሚያለቅሱ ይሰማኝ ነበር። እንደዚህ እያሰብኩ ግጥም እየፃፍኩልሽ ነበር። ፈጣሪ ዓለም የሚያጠፋት በቁጣ ነው ሲሉኝ እገረማለሁ። ፈጣሪ ዓለምን ካጠፋ አንቺ ስትሞቺ በሚደርስበት ሀዘንማንበብ ይቀጥሉ…
ይሰለቻል
በመጀመሪያ እግዜር ብቻውን ነበር። ብቸኝ ት ሰለቸው። ብቸኝነት ሰለቸውና ዓለምን ፈጠረ። የፈጠረውን አይቶ ደስ አላለውም፣ ሰለቸው እንጂ። የሰለቸውን ዓለም ትቶ ሌላ አዲስ ነገር ፍለጋ ሄደ። ዓለምም ከዛን ወዲህ መሰልቸት ወለል ላይ ሆና የአምላኳን መምጣት በጥፍሯ ቆማ ትጠብቃለች። እኔ የዓለም አካልማንበብ ይቀጥሉ…
ባትሄጂ ኖሮ…!
ባትሄጂ ኖሮ፣ ብትሆኝ ከኔ እቅፍ እዚህ ከፃፍኩት ላይ፣አንድም መስመር አልፅፍ፡፡ አቤት ባትሄጂ! ግን አንቺ አልቆምሽም መጓዝ አልደከምሽም፡፡ ይሄዋ፡- ከሄድሽ በኋላ ዐይኔም አይታየው፣ ጆሮዬም አይሰማ ልቤም ደም የሚረጭ፣ ባንቺ ስለደማ፡፡ አንቺ በመሄድሽ፤ ያለህይወት በህይወት ተነጥላኝ ነብሴ፣ ያው አለሁ ሙት ሆኜ፣ ለሰዉምማንበብ ይቀጥሉ…