ሃይማኖት ወይስ ፖለቲካ

ያለፈውን አመት ለውጥ ተከትሎ ለአገራችን አንድነት፣ ለሕዝባችን ሰላም አደገኛ የሆኑ አጀንዳዎች በድፍረት ሲነሱ አይተን ደንግጠናል። ሰሞኑን ከኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ጋር ተያይዞ እየጮኸ ያለው መንፈሳዊነት የነጠፈበት አጀንዳ ዋነኛው ነው። የትላንት ታሪክ እንደሚነግረን አትዬጵያ-ጠል የሆኑ ኃይሎች ቤተክርስትያኗ ላይ አደጋ ሲጥሉ ቆይተዋል። ከጉዲትማንበብ ይቀጥሉ…

የሚጠይቁና ለጥያቄያቸው መልስ የሚሹ ሰዎች በደንብ የሚያስቡ ናቸው!

አባቶቻችን የመጠየቅን አስፈላጊነት ሲያሰምሩበት ‹‹ካለመጠየቅ ደጅ አዝማችነት ይቀራል›› ይሉናል። ፈረንጆቹም ‹‹ካልጠየቅክ አታገኝም! (If you do not ask, you will never get)›› ይላሉ። ሊቃውንቱም ‹‹መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ›› በማለት መጠየቅ የሕይወት በርን፣ የአዕምሮ ደጃፍን፣ የልቦና መስኮትን ወለል አድርጎ ከፍቶ ከጥበብ ማማ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

የስነፅሁፍ ምሽት ከየት ወዴት?

  ድሮ በሃይለስላሴ ዘመን ያዲሳባ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች፤ ባህል ማእከል ውስጥ፤ የስነፅሁፍ ምሽት አዘጋጅተው፤ጃንሆይን በንግድነት ይጠሩዋቸዋል። ጃንሆይ የተማሪዎችን ጥሪ አክብረው፤ካባቸውን ደርበው ፤ ከች ይላሉ:: ከዛ ኮከብ ተማሪዎች ተራ በተራ እየተነሱ ረጅጅምምም ግጥም ያቀርባሉ። በጊዜው ስለፍቅር፤ ስለውበት መግጠም እንደ ቅንጦት ይቆጠራልማንበብ ይቀጥሉ…

እይታና ምዘና

በዚህ አለም ላይ ፤እንደ ወንድ ልጅ ጨካኝ ፍጡር አለ? ወንድ ልጅ በወንድ ልጅ ሲጨክን ለከት የለውም፤ባለፈው ከስንት ጊዜ በሗላ ፎቶ ለመለጠፍ ወሰንኩ። የሃይሌ ገብረስላሴን ያክል እንኳ ያክል ባይሆን፤ የሃይሌ ገሪማን ያክል ሮጨ፤ እምብርቴን የወጠረውን የጮማ አሎሎ አቅልጨ፤ ሰው ፊት የሚቀርብማንበብ ይቀጥሉ…

የሚቀጥለው ፋሲካ

(የሚያስተክዝ ትዝታ) ያኔ ልጅ እያለሁ ፤ የፍልሰታ ጦምን እስከዘጠኝ ሰአት እፆም ነበር። የፆም አላማ ፤ወደ እግዚያብሄር ለመቅረብ፤ በረከት ለማግኘት እና ሀጢአትን ለማስተረይ እንደሆነ ይታወቃል ። እኔ ግን የምጦመው በፆም ወቅት ቤት ውስጥ ምግብ ስለማይሰራ ነው፤ ጦሙ ሊገባ ሁለት ቀን ሲቀረውማንበብ ይቀጥሉ…

አንጀት የመብላት ጥበብ

የሆነ ጊዜ ላይ የሚሰራበት መስርያ ቤት፤ ለዓለምአቀፍ ስብሰባ ወደ ውጭ ሀገር ላከው:፤ በተላከበት የፈረንጅ ከተማ ሆቴል ውስጥ ፤ አንድ ሳምንት በስብሰባ ዛገ፤ እናም፤ ያንቀላፋ ልቡን የሚቀሰቅስለት አንድ ነገር ፈለገ፤ አንድ ቀን ሆቴሉ አጠገብ የሚገኝ ቡና መጠጫ ቤት ውስጥ ገባ። ካፌውማንበብ ይቀጥሉ…

ማፍረስ እንደ ባህል

(የመትከል ባህል የሌለው ሕዝብ እንትከል ስትለው አወዳደቁን እየተለመ ይስቃል) — ስሜነህ አያለሁ እና ቢኒያም ሲሳይ የፃፉት፣ «what is in a term? A historical and linguistic examination of the revolutionary terminology:yiwdem, “let it be demolished, down with,” 1974-1977» የሚል ወረቀት አለ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ሆሆ

“ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ። እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል። ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባትማንበብ ይቀጥሉ…

ሕሩይ ሚናስ

በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ታላቅ ቦታ ከያዙ ሰዎች አንዱ ነው። እስካሁን ካነበብኳቸው የአማርኛ መጽሐፍት በልዩ ኹኔታ ከማስታውሳቸው ጥቂት ሥራዎች አንዱ የሕሩይ ሚናስ “እብዱ” የሚለው ሥራ ነው። የራሱን devastating experience በመጽሐፍ መልክ በመሰነድ ለአጥኚ ባለሙያዎች ራሱ እጅግ እንቆቅልሽ የኾነውን የአእምሮ መታውክማንበብ ይቀጥሉ…

የማብራትና ማጥፋት ወግ

(የመጨረሻው ክፍል) ባገራችን፤ በባላባት ስርአት ወግ “ፈናወጊ “ የተባሉ አገልጋዮች ነበሩ፤የስራ ድርሻቸው ፋኖስ፤ አንዳንዴም ጡዋፍ ይዞ መቆም ነበር፤ራት ላይ ከጌቶች እና ከእመቤቶች ማእድ ትንሽ ፈንጠር ብለው ቆመው ያበራሉ፤ በቤተመንግስት ውስጥ መብራት ተሸክመው የሚያነጉም ነበሩ፤የመጀመሪያዎቹ የመብራት ምስሶዎች ነበሩ ማለት ይቻላል፤ ታድያማንበብ ይቀጥሉ…