ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

ባለፈው ከውጭ ወዳገር ቤት ስመጣ አንዱ ደውሎ:- ” ጀለስካ ወዳገር ቤት ለመግባት ኤርፖርት ታይተሃል የሚባል ነገር ሰማሁ ልበል” ” ልክ ነው!” “በሩ ላይ ጠብቀኝ ታክሲ ይዤ መጣሁ” “እቃ ውሰድልኝ ልትለኝ ባልሆነ?” “ምናለበት ብትቸገርልኝ” ” አዝናለሁ ሻንጣየ ውስጥ ላየር ማስገብያ የሚሆንማንበብ ይቀጥሉ…

እኔ እምፈልገው

እውነት ለመናገር፥እኔ እምፈልገው ካንቺ ጋር መጋባት ይህን ሐምሌ ፊቴን፥ ደጋግሞ ማራባት ከወፎች ጋር መንቃት፥ በጊዜ ቤት መግባት “ምንም ድሀ ቢሆን፥ ባይኖረውም ሀብት ከደጃፍ ሲቀመጥ፥ ደስ ይላል አባት” ለሚል መናኛ ጥቅስ ፥ ኑሮየን ማይመጥን ሲሻኝ በየባንኩ፥ ስፈልግ በሳጥን የተረፈኝ ገንዘብ ደጃፍማንበብ ይቀጥሉ…

ድንኩዋን ሰባሪው

  አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ነው። የቸሬ ድህነት ግን ወለል እንኩዋ የለውም። ከቸሬ ጋር ስትወዳደር ድህነት ራሷ ሀብታም ናት። እኔ ግን ምናለ መፈላሰፉን ትቼ ወደ ታሪኩ ብገባ ! በቀደምለት ቸሬ ተፈናቃይ ወገኖቻችንን በጉልበትና በፀሎት ለማገዝ ወደ ስፍራውማንበብ ይቀጥሉ…

ወፋ በፌስቡክ

በድሮ ጊዜ በኢትዮጵያ ባንዳንድ ገጠሮች ውስጥ “ወፋ” የሚባል ልማድ ነበር። ያንድ ቀበሌ ባላገሮች ከወንዝ ወዲህ ማዶ እና ወድያ ማዶ ተሰላልፈው በጩቤ በጦር በዱላ ይከሳከሳሉ። አንድ ባላገር ከገበያ ሲመለስ የወፋ ጦርነት ሲካሄድ ከተመለከተ ቆም ብሎ ቅርጫቱን ያስቀምጣል። ከዚያ በቅርብ ከሚያገኘው ጎራማንበብ ይቀጥሉ…

ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና የምፅዋ ወግ (ክፍል ሶስት)

አስመራ – ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ አዲስ አበባ እና አስመራ በብዙ ነገር የተለያዩ ከተሞች ይሁኑ እንጂ በተለይ የድሮዋን አዲስን ለሚያውቅ ሰው የአስመራን መልክ መገመት የሚከብድ አይመስለኝም። እስቲ ድፍን ፒያሳን አስቡ። ብሄራዊ ቲያትር አካባቢን፣ አምባሳደር፣ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢን ጨምሩ። ሜክሲኮ የድሮውንማንበብ ይቀጥሉ…

ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና ምፅዋ ወግ (ክፍል ሁለት)

አስመራ- ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ ለስድስት ቀን ቆይታዬ በፊልሞን አማካኝነት ወደተያዘልኝ አምባሳደር ሆቴል ገባሁ። የእንግዳ መቀበያውና በኋላ ያየሁት በስተግራ ያለው ሻይ ቤት ነገረ ስራው ሁሉ የፒያሳውን ቶሞካ አስታወሰኝ። ሞቅ ባለ ሁኔታ የተቀበለኝ አስተናባሪ ሻንጣዬን ይዞ ክፍሌን የሚያሳየኝ ጎልማሳ መድቦልኝ አሳንሰሩማንበብ ይቀጥሉ…

ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና ምፅዋ ወግ

አስመራ- ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ ‹‹እናት ብዙ ሻንጣ የለሽም አይደል? እባክሽ ይህቺን ስኳር ያዢልኝ? የእኔ እህት….ኪሎ በዝቶብን ነው…ይህችን ቡና ትይዥልኛለሽ?….እመቤት… ያንቺ አልሞላም አይደል…እባክሽ እነዚህን ጫማዎች ያዢልን…›› እያሉ ብዙ ሰዎች ያዋክቡኛል። ቦሌ አየር ማረፊያ አስመራ የሚወስደኝን አውሮፕላን ለመሳፈር ሻንጣ ማስረከቢያው ጋርማንበብ ይቀጥሉ…

ይበለኝ

በቀደምለት፤አልጄዚራ ያማርኛ ክፍል ጋዜጠኛ ከኔ ጋር አጭር ቃለመጠይቅ አድርጋ ነበር፤ በሁዋላ ግን ቃለ መጠይቁ ከባህላችን ጋር ስለማይጣጣም ልናቀርበው አንችልም የሚል ኢሜል ላከችልኝ፤ ለማንኛውም ሙሉ ቃለመጠይቁ ይህንን ይመስላል፤ “የት ነው የተወለድከው?” -ሆስፒታል “የትውልድ አገርህ ማለቴ ነው” -ማንኩሳ ሚካኤል “በልጅነትህ የሚያስደስትህ ነገርማንበብ ይቀጥሉ…

በውቄ እንዴት እንደተፈነከተ!

አባቴ በጣም ትግስተኛና ደመበራድ ስለሆነ ባመት አንድ ቀን ቢናደድ ነው፤ የተናደደ ቀን ግን ምድር አትበቃውም፤ ከደመኞቹ ጋር ሲደባደብ ጣልቃ የገቡ ገላጋዮች “እጁ ላይ ሰው አይበረክትም” እያሉ ያደንቁት ሰምቻለሁ፤ ዘጠነኛ ክፍል እያለሁ፤ በገና በዐል ዋዜማ፤አባየ ከባለንጀራው፤ ከጋሽ ፋኑኤል ጋር አንድ ሁለትማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ፀዲ››

(መነሻ ሃሳብ- የጁኖ ዲያዝ ‹ዘ ቺተርስ ጋይድ ቱ ላቭ›› አጭር ልቦለድ) ሰው ሁሉ ‹‹ፀዲና ሙሌማ ይጋባሉ። ተጋብተው አራት ልጅ ይወልዳሉ። አብረው ያረጃሉ። ተለያይተው መኖር ስለማይችሉ አንዳቸው ከሞቱ በነጋታው ሌላኛቸው ይከተላሉ›› የምንባል አይነት ነበርን። እኔና ፀዲ። ከተለያየን ሁለት ወራት ሞላን። መጀመሪያማንበብ ይቀጥሉ…