የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል አራት)

ክፍል አራት፡ ትግሉን ለዓለም ማኅበረሰብ ማስተዋወቅ  በጆርጅ ሐበሽ የሚመራው PFLP እስራኤልን በትጥቅ ትግል ብቻ ለመፋለም የወሰነ ድርጅት ነበር። በመሆኑም በወቅቱ ከስድስት መቶ ያልበለጡ ተዋጊዎቹን በማሰማራት በፍልስጥኤም ግዛቶች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያደርግ ጀመር። በሊባኖስ፣ በዮርዳኖስ፣ በሶሪያ እና በሌሎች የዐረብ ሀገራት የተበተኑት ፍልስጥኤማዊያንማንበብ ይቀጥሉ…

ሶማሊ እና ኦሮሞ ወንድማማቾች ናቸው!

ታሪካችን የመረዳዳት እንጂ የግጭት አልነበረም። ታሪካችን የአብሮ መኖር እንጂ የመበላላት አልነበረም። ታሪካችን የመፋቀር እንጂ የመናቆር አልነበረም። እጅግ በሚገርም ሁኔታ አንዳችን ለሌላው መብትና ጥቅም መከበር ስንል አብረን ተዋግተናል። ህይወታችንን ሰውተናል። ለምሳሌ ታዋቂ የኦሮሞ አርበኞች የሆኑት ኤሌሞ ቂልጡ (ሐሰን ኢብራሂም)፣ እና ሁንዴማንበብ ይቀጥሉ…

የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ሶስት)

ክፍል ሶስት፡ የአዲስ ግንባር ምሥረታ  ጆርጅ ሐበሽ እና ዋዲ ሀዳድ ሶሪያን እንደ ዋነኛ ቤዝ በመጠቀም ትግላቸውን በማካሄድ ላይ ሳሉ በ1962 የባዝ ፓርቲ አፍቃሪ የሆኑ መኮንኖች በሳላህ አል-ቢጣር መሪነት የሀገሪቱን መንግሥት ገለበጡ። ይህም የሶሪያ መንግስት ይከተለው በነበረው ፖሊሲ ላይ ትልቅ ለውጥማንበብ ይቀጥሉ…

የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ሁለት)

ቀዳሚው የትግል ምዕራፍ ዶ/ር ጆርጅ ሐበሽ እና ዶ/ር ዋዲ ሀዳድ በቀዳሚዎቹ ዓመታት አዲሱን ድርጅታቸውን በማስተዋወቅና አባላትን በመመልመል ላይ ነበር ያተኮሩት። በዚህ መሠረት በተለያዩ ሀገራት ወደሚገኙት የፍልስጥኤም ኮሚኒቲዎች ወኪሎቻቸውን እየላኩ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን አስተዋውቀዋል። አባላትን እየመለመሉ በድርጅቱ ህዋሳት ስር አዋቅረዋል። ከተለያዩ መንግሥታትማንበብ ይቀጥሉ…

የሁለት ዶክተሮች ወግ

ክፍል አንድ፡ የትግል ጅማሮ ይህ ተከታታይ ትረካ የሁለት ግለሰቦችን የትግል ጉዞ በአጭሩ ለማስተዋወቅ ታስቦ የተሰናዳ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ፍልስጥኤማዊያን ናቸው። ሁለቱም ክርስቲያን ዐረቦች ነበሩ። ሁለቱም ከሀብታም ቤተሰቦች ነበር የተገኙት። ሁለቱም በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ አጥንተው በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል። ሁለቱም በዩኒቨርሲቲውማንበብ ይቀጥሉ…

ዜግነት እውነት ነው፤ ብሄረሰብነት እምነት ነው

ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ፤ ጥንታዊ ወታደር በባላገር ላይ ሲያደርስ የኖረውን በደል ፅፎ አይጠግብም፤ ባንድ ቦታ ስለ አንድ ገበሬ የሚከተለውን ይተርካል፤ •….“ከነዚህ መከረኞች አንዱ(ገበሬ) መልከ ቅን ምሽት ነበረችው፤ አንድ ቀን በቴዎድሮስ ጊዜ አንድ ቅማጫም ነፍጠኛ ተቤቱ ተመርቶ ገባና ባለቤቲቱ መልከ ቅንማንበብ ይቀጥሉ…

ስንቴ ገረዝኩት (ክፍል አራት)

(የመጨረሻ ክፍል) “ዶክተር ሰው ይፈልግሻል?” “ሲሳይ ነው? ትንሽ ታገሰኝ በይውና ተረኛ ታካሚ አስገቢልኝ።” “ዶክተር ……… ባለቤትሽ ነው።” “ባለቤትሽ? ኢሳያስ?…………” “ቢሮዬ ድረስ እየመጣህ ለምን ትረብሸኛለህ ኢሳ?” “ናፈቅሽኝ!! ከዚህ በላይ ሳላይሽ መቆየት አልችልም።” ከዩንቨርስቲ ጀምሮ የማውቀው ሰው ነው ኢሳያስ ። ለ6 ዓመትማንበብ ይቀጥሉ…

ስንቴ ገረዝኩት (ክፍል ሦስት)

እግሬና ሀሳቤ ሳይስማሙ እግሬ ቀድሞ ሬስቶራንቱ ውስጥ ተገኘ። ሲሳይ ቀድሞኝ ተገኝቷል። ልጨብጠው የዘረጋሁትን እጄን ሳብ አድርጎ አቀፈኝ። የምቀመጥበትን ወንበር ሳበልኝ። እራትና ወይን አዘዝን። ከእርሱ ጋር መጨቃጨቁ ትርፉ የሌላ ሰው ትኩረት ከመሳብ ያለፈ ስለማይሆን ዝም ብዬ የሚያደርገውን ከማየት ውጪ ተቃውሞም መስማማትምማንበብ ይቀጥሉ…

ስንቴ ገረዝኩት (ክፍል ሁለት)

“ዶክተር? ያው ሰውዬ ነው የላከልሽ………” ሲስተር ቀለም በፈገግታ በደመቀ ፊት ጠረጴዛዬ ላይ በፎይል የተጠቀለለውን ምሳ አስቀምጣው ወደ በሩ ተመለሰች “ሲስተር ከዛሬ በኋላ የሚያመጣውን ምሳ እንዳትቀበሉት።” አልኳት ለሁለተኛ ጊዜ ታክሞ ከሄደ ጀምሮ ሶስት ቀኑ ነው። የምሳ ሰዓት እየጠበቀ ምሳ ይልካል። ጠዋትማንበብ ይቀጥሉ…

ስንቴ ገረዝኩት?

“አንቺማ አትገርዢኝም። በስመአብ! ” አለ እያማተበ ለመቀመጥም ለመነሳትም በቀረበ አኳኋን አየሩ ላይ ተንጠልጥሎ። “አየር ላይ ነህ፣ አረፍ ትል?” አልኩት አኳኋኑ ሳቄን እያመጣው “የታለ ዶክተሩ ከምር? ” አለኝ ወንበሩ ላይ ተስተካክሎ እየተቀመጠ “እኔ ነኝ!!” አልኩት ምን እንደሚያስብ ለመገመት እየሞከርኩ ካርዱ ላይማንበብ ይቀጥሉ…