ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ

የሚከተለው ግጥም በሚታየው ታሪካዊ ፎቶግራፍ ንሸጣ የተፃፈ ነው፤ በፎቶው ላይ ሻምበል አበበ ቢቂላ የልምምድ ሩጫ ሲሮጥ ይታያል፤ ከሁዋላው አህያ እየነዳ የሚያልፍ አላፊ ጠፊ ገበሬ አለ፤ ግጥሙን የጣፍኩት ለዚህ አህያ ነጂ ገበሬ ነው፤ ) ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ ባሮጌው ጎዳና፤ በጮርቃውማንበብ ይቀጥሉ…

የመውሊድ ትዝታዎቼ

የመውሊድ በዓልን እያከበርነው ነው። በዚህ ጽሑፌ ስለበዓሉ አከባበር የማወጋችሁ ነገር የለም። ከዚያ ይልቅ ያኔ በልጅ ወኔአችን ከሰራናቸው “አድቬንቸሮች” አንዳንዶቹን አጋራችኋለሁ። ***** በህዳር ወር 1980 ነው። በወቅቱ እኔ (አፈንዲ)፣ መሐመድ አብደላ (ማመኔ)፣ ጆሀር ሀጂ ዩሱፍ (ጀዌ)፣ አድናን ዑመሬ (አግሽ)፣ እና አሕመዶማንበብ ይቀጥሉ…

ባዩ ቀብሩም ገሰሲ አለቁም!

‹‹ አብርሃም ›› ‹‹አቤት አባባ ›› አልኳቸው አከራየ ሻለቃ በላቸው ነበሩ በር ላይ ቁመው የጠሩኝ ‹‹ እየውልህ . . . ይሄ የሸምሱ ሱቅ ጋር መታጠፊያው ታውቀው የለም ? ›› አሉኝ በከዘራቸው ወደሸምሱ ሱቅ አየጠቆሙ ‹‹አዎ ወደ ኢንተርኔት ቤቱ መታጠፊያ አይደልማንበብ ይቀጥሉ…

ወደ እሷው ጉዞ

“ስሟ ግን ማነው?” አልኩት አቡሽን “እብድ ደግሞ ስም አለው? አንተ ልጅ ዛሬ ምን ሆነሃል? ልታብድ ነው እንዴ?” መለሰልኝ። ላብድ መሆኔን እኔም ጠርጥሪያለሁ። ማታ ሰክሬ ነው ብዬ ያባበልኩት ቅዠቴ አድሮ ከህሊናዬ ካልጠፋ ለማበድ እየተቃረብኩ መሆን አለበት።ባለፈ ለሊት ሰማይ ተቀዶ በሚወርደው ዶፍማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

(የሚያስተክዝ ወግ) ከየረር በር እስከ ቦሌ የሚሄድ ምኒባስ የመሳፈር እድል ያልገጠመው ሰው ስለ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ልተንትን ቢል ማን ይሰማዋል? እና ትናንት የተሳፈርኩበት ምኒባስ ካፍ እስከ ሰደፍ ሞልቶ ነበር፤ የምኒባሱ ነባር ወንበር የተሳፋሪውን ብዛት ባገናዘበ መልኩ ሽግሽግ ተደርግጎበታል፤ ወደ ሁዋለኛውማንበብ ይቀጥሉ…

አንዳንድ አሟሟቶች

ሀበሻ አሟሟቴን አሳምረው ይላል። አሟሟት ትልቅ የክብር ሞት ላይ የተንጠለጠለች አላቂ እቃ ነች። የሚደነቅ አሟሟት እንዳለ ሁሉ ግራ የሆነ አሟሟት አለ። ላልቃሽ ቤተሰብ የሚቸግር የሚመስል። ከሞተ የገዘፈ የሚመስል ሰውን ሞት ተኩነስንሶ እና ተልከስክሶ አንሸራቶ ይጥለዋል። ከሞቱ አሟሟቱ አስብሎ ያሳዝናል። ጊዜውማንበብ ይቀጥሉ…

ቂም የሸፈነው እውነት (ክፍል ሁለት)

“እሙዬ ነይ እስኪ……” “ምን ፈለግክ?” “አንቺን” “ሸርሙጣ አይደለሁም።” “ታዲያ እዚህ ምን ይገትርሻል?” “ቤቴ ነዋ…..” ብዬ የላስቲክ ቤቴን በእጄ ጠቆምኩት። “ስንት ዓመትሽ ነው?” “አስራ አራት” ከመኪናው ወርዶ እየተንገዳገደ ተጠጋኝ። “300 ብር እሰጥሻለሁ።” “ሸርሙጣ አይደለሁም አልኩህ እኮ……” “ሸርሙጣ ነሽ ማን አለሽ? ጎዳናማንበብ ይቀጥሉ…

ታስፈሩኛላችሁ

ታስፈሩኛላችሁ አለ አስኮ ጌታሁን ታስፈሩኛላችሁ! ሳያድግ ያስረጃችሁት የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ገብታችሁ «የበለው በለው» ቅኝታችሁን ጥኡም ሙዚቃ ነው ስትሉ ታስፈሩኛላችሁ። «ሀገር ተዘረፈ ሲባል» ሆ ብላችሁ ስትተሙ ሳይ፣ለማስጣል የመሰለኝ መትመማችሁ አብሮ ለመዝረፍ መሆኑን ሳውቅ ታስፈሩኛላችሁ። በጥላቻ ጄሶ የታሸ የተበድለናል ለቅሶችሁ ውስጥ ያለውማንበብ ይቀጥሉ…

እንጀራ

የተሟላ አይነት ውክልና አለው። ይታያል (እንደ ስዕል)፣  ይነካል፣ ይቀመሳል፣ እናም ይበላል፡፡ የመጨረሻው ፀባዩ የተለየ ያደርገዋል። እንደ ብዙ ቁሳቁስ በሩቅ የሚታይ አይደለም። ከሳብጀክቱ (የሰው ልጅ) ጋር ይዋሃዳል (embodied)። የትውስታም ሰሌዳ ነው። አርኪዮሎጂስቶች በጥንት ጊዜ የተሰራ ቁስ አግኝተው በመሳሪያቸው መርምረው የእነዚህን ቁሶችማንበብ ይቀጥሉ…

ቂም የሸፈነው እውነት

“መለያየት እፈልጋለሁ። ፍታኝ?” አልኩት በመኪናው መስኮት አሻግሬ ዓይኖቹን እየሸሸሁ። “እሺ!!” ነበር መልሱ:: ቢያንስ ‘ለምን?’ ብሎ እንዴት አይጠይቀኝም? “መች ነው እንዲሆን የምትፈልጊው? አሁን? ነገ? ከሳምንት በኋላ? መቼ?” ቀለል አድርጎ ቀጠለ። ቀጥዬ የምለው ጠፋኝ። ለራሴ ምክንያት መስጠት እፈልጋለሁ። ተናዶ እንዲናገረኝ እሱ ላይማንበብ ይቀጥሉ…