መረራ ጉዲናን ሳስታውስ

በ1988 የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ESLCE) እንደወሰድኩ ነው። ዕለቱ ከሚያዚያ ወር መአልት አንዱ መሆኑ ይታወሰኛል። በዚያች ዕለት የጀርመን ድምጽ ራድዮ ከቀደሙት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለየ ዓላማን ያነገበ ድርጅት መቋቋሙን ዘገበ። የድርጅቱ መስራች የሆኑት ግለሰብ የተናገሩትንም ቀንጨብ አድርጎ አስደመጠን። በጉዳዩ ዙሪያማንበብ ይቀጥሉ…

የኢትኖግራፊ ጉዞ ወደ ጎጃም (ክፍል ሁለት)

ጎጃምን ከሌሎች የቀድሞ ክፍለ ሀገሮቻችን ለየት የሚያደርገው ዙሪያውን በዐባይ ወንዝ የታጠረ መሆኑ ነው። ከጣና ሐይቅ በስተምዕራብ ራቅ ብሎ ካለው የግልገል ዐባይ መነሻና በሱዳን ድንበር መካከል ከሚገኘው ክፍት መሬት በስተቀር ክፍለ ሀገሩ በሙሉ በዐባይ የተከበበ ነው። እርግጥ በወንዝ የታጠሩ ሌሎች ክፍለማንበብ ይቀጥሉ…

ተመራቂዉ ልጅ

ከተመረቅኩኝ አንድ ወር አለፈኝ።(በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ዉሸት) ……የሆነ ልጅ እንደጻፈዉ እስካሁን ስራ ለምን አልያዝኩም ብዬ አላማርርም። እንኳንስ እኔ መካከለኛ ግሬድ ካላቸዉ ተማሪዎች ተርታ የምመደበዉ ይቅርና ሰቃያችንም ስራ አልያዘም! ይልቁንስ የሚያስጨንቀኝ ሰፈራችን ከእኔ ጋር በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የተመረቀዉ የአንድ አመትማንበብ ይቀጥሉ…

የኢትኖግራፊ ጉዞ ወደ ጎጃም

ያ በእውቀቱ ስዩም የሚሉት ጎጃሜ ብላቴና አምናና ዘንድሮ የኛዋን ኦሮሚያን በብዕር መነካካቱን አብዝቷል። እስከ ዛሬ ድረስ “ይሄ ልጅ ለምን አያርፍልንም? እኛም እርሱን ስላፈራችው ጎጃም መጻፍ የማንችል መሰለው እንዴ” እያልን ከራሳችን ጋር ስንነጋገር ቆይተናል (“እኛ” ወልደ-ገለምሶ ዘብሔረ ሀረርጌ በመሆናችን ባሰኘኝ ጊዜማንበብ ይቀጥሉ…

ባይተዋሩ ግመል

አንዳንድ ድምጻውያን አዲስ አልበም ሊያወጡ ሲሉ ነጠላ ዜማቸውን ቀደም ብለው እንደሚለቁት፣ከአዲሱ ‹ያልተቀበልናቸው› ከተሰኘው መጽሐፌ ከአንዱ ወግ ቀንጭቤ ጀባ ልላችሁ ወደድኩ።  ባይተዋሩ ግመል (….) ግመሉ የተገለለ ነው – ከወንዙ ተነጥሎ፣ ከወገኑ ተለይቶ፣ ለተሻለ ኑሮ፣ ወይም ለተሻለ የመንፈስ ፀጥታ፣ ወይም ለተሻለ ዕውቀትማንበብ ይቀጥሉ…

ሰርፕራይዝ

(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ትናንትና የልደት በአሌን በማስመልከት ከወዳጆቼ አንዱ ወይም አንዲቱ ሰርፕራይዝ ያደርገኛል/ታረገኛለች ብየ ብጠብቅ ብጠብቅ ወፍ የለም። ግን ተስፋ አልቆረጥኩም። ባካባቢየ ወደሚገኝ አንድ ያበሻ ሬስቶራንት ሂጄ ተቀመጥሁ። ያዘዝኩት ሰላጣ እስኪመጣ ፌስ ቡኬን ለኮስኩ። አንዱ በቀጥታ ካዲሳባ online ላይ ጠመደኝ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ግጥሎት

ቀጥሎ የምታነቡት ነገር በግጥምና በፀሎት ማሃል ያለ ነገር ነው። ግጥሎት ብየዋለሁ😉ትናንት በእንቅልፍና በንቃት ማሃል ሆኘ የመጣልኝ ነው። ወፍ እንዳገሩዋ ትጮሃለች! ነፍስ እንደዘመኑዋ ትፀልያለች! የፅሁፌ አላማ ራሴን እና ብጤዎቼን ለማዝናናት ብቻ እንደሆነ ይታወቅ! አባት ሆይ ! እንሆ ዛሬ ተወለድሁ! ካለመኖር ወደማንበብ ይቀጥሉ…

እኔና አንቺ

“አንተ ሴሰኛ አይደለህም።” ትዪኛለሽ። ሴሰኝነት ‘ስሜ’ መሆኑን አንቺም፣ እኔም፣ ከጎኔ የሚሻጡት ሴቶችም፣ እኔን የሚያውቁኝም ሁሉ እናውቃለን። ለራሴ ‘ያለማወቅሽን እና የዋህነትሽን’ ነገርኩት። ላንቺ ግን ዓይኖቼንም ልቤንም የጠለፈውን ህልም የመሰለ ውበት ያለው አካልሽን እያየሁ ጥርሴን ለመግለጥ ከንፈሬን አሸሸሁልሽ …….. ሚስጥር አዘል ወጋገንማንበብ ይቀጥሉ…

የገቢዎች ነገር እና 40/60

በጥዋት አልጋዬ ውስጥ ሆኜ እየተብሰከሰኩ ነው። የቤት ኪራይ መክፈያዬ ደርሷል……ኤዲያ! ” መቼ ነው ግን የራሴ ቤት የሚኖረኝ?” ።ትላንት በጉጉት ስጠብቀው የነበረው የ40/60 እጣ እንደወጣ በዜና አይቻለሁ…እጣ ውስጥ የተካተቱት መጀመሪያውኑም መቶ ፐርሰንት የከፈሉ ብቻ እንደሆነም ተነግሯል……የወጣው እጣ አንድ ሺ እንኳን አይሞላም።ማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

(ታሪካዊ ልቦለድ) To be honest with you ሲያትል በተደረገው የዲያስፖራ የግርኳስ ውድድር ወደ ሚደረበት ስቴዲየም የሄድኩት ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳልነካካ መፅሃፌን ሸጬ አገሬ ለመግባት ነበር፤ (ከመፅሃፍ ሻጭ የሚገኘው ገቢ አስር በመቶ ለእኔ ሲሆን ፤ ቀሪው ለቤት አከራየ ለጋሽ ጣሰውማንበብ ይቀጥሉ…