“ባቦ፤ በማርያም…”

አመት በአል ሲቃረብ ብዙ ነገር ይናፍቀኛል። ከሁሉም በላይ፤ እንደ አፍላ ጉም የሚሳብ የሉባንጃ እጣን – ብረት ምጣድ ላይ የሚጤስ ቡና -የጥላሁን ገሠሠ ዘፈን -ብዙ ፍቅር- ብዙ ፈገግታ ውልውል ይለኛል። ከመከረኛ ህይወታችን ማህል ብልጭ ብሎ የሚጠፋ አመት በአል የተባለ አብሪ ኮከብማንበብ ይቀጥሉ…

አል-ዑመሪ እና ሪቻርድ ፓንክረስት

በ1330ዎቹ ነበር። በዘመኑ የምሥራቅ አፍሪቃ ታላላቅ መንግሥታት በነበሩት የኢትዮጵያ ሰለሞናዊ አፄዎች እና የኢፋት ወላስማ ሱልጣኖች መካከል ታላቅ ጦርነት ይካሄድ ነበር። በጦርነቱ ከተሸነፉት የኢፋት መንግሥት ባለሟሎች መካከል ጥቂቱ ወደ ግብጽ ሸሹ። እዚያም ለግብጹ ሱልጣን የደረሰባቸውን ሽንፈት ሲያወሱ አንድ ጸሐፊ ያስተውላቸዋል። ይህማንበብ ይቀጥሉ…

ሕይወት- ሌስተርና ቼልሲ

ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም። አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል። አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል። ለሚወጣ ሰው ግን መውረድማንበብ ይቀጥሉ…

ልጄ -ባዶ ወረቀቴ

ማን ማን ውስጥ እንደገባ፣ የቱ ገላ የማን እንደሆነ መለየት እስኪያስቸግረን ድረስ ተቆላልፈን ከመዋሰብ ያለፈ ነገር አላውቅም ነበር። የወጣትነት ትኩሳትን ከማዳፈን፣ የቆመን ከማጠውለግ፣ ከግብት- ውጥት እና ግብት- ትፍት ጨዋታ በላይ ደስታ ይሰጠኝ የነበረ ነገር አላስታውስም። ….እንዲህ እንዲህ በየአልጋው ስንወድቅ እና ስንነሳማንበብ ይቀጥሉ…

ሠርገኛ መጥቶም በርበሬ ቀንጣሽ ጠፋ

ስንቱ መከረኛ ወገኔ ዛሬም ፤ ‹‹አዬ ክፉ ዘመን ይቅር አይነሳ፣ አርጉዝ ላሜን ሸጥኳት- ለሁለት ቀን ምሳ›› እያለ አጣዳፊ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ሲገልፅ፤ ‹‹ድርቁን ረሃብ ከመሆኑ በፊት ተቆጣጥረነዋል!›› ‹‹የውጪ እርዳታ አንፈልግም!›› ሲባል ተከርሞ፤ በዚህ ሳምንት ከወራት በፊት በጓሮ በር ቤተመንግስት ይመላለሱማንበብ ይቀጥሉ…

እምቢ እሺ አይደለም…እሺ ብቻ ነው እሺ

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከጓደኞቼ አንዱ የሚያሰቅቅ ነገር ላከልኝ። አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ በመቶ የሚቆጠሩ ወንድም ሴትም ተማሪዎችን ያሳተፈ ጥናት ውጤት ነው። ጥናቱ ስለ አስገድዶ መድፈር ነው። የመጠይቁ ብቸኛ ጥያቄ ይሄ ነው፤ ‹‹አስገድዶ መድፈር ተቀባይነት ሊኖረውማንበብ ይቀጥሉ…

ደስታን በብልቃጥ

‹‹ላግባሽ›› ብሎ ሲጠይቀኝ… አይኖቼ እንደ ስልሳ ሻማ አምፖል እየተንቦገቦጉ፣ የሰራ አከላቴ እየፋመ፣ ከንፈሬ መርበትበቴን ለማሳበቅ እየተንቀጠቀጠ፣ ሰውነቴ ያለ አግባብ እየተናወጠ… ይሄ ሁሉ አይሰሙ ደስታ እየተሰማኝ ፤ ቃላቶቼን መጥኜ፣ መፈንደቄን ደብቄ ቀዝቀዝ አልኩና፣ ረጋ አልኩና፣ በሴት ልጅ ወግ፤ ‹‹እሺ…›› አልኩት። ይወደኝማንበብ ይቀጥሉ…

የቤት እመቤት በመሆን ውስጥ እመቤትነት አለ?

ላለፉት ጥቂት ቀናት ያገኘኋቸውን ወንዶች በሙሉ አንድ ጥያቄ ስጠይቅ ነበር፡፡ ‹‹የቤት እመቤት ምን ማለት ነው?›› ከአንድ ወይም ሁለት መልሶች ውጪ የተሰጡኝ ፍቺዎች በሚከተሉት ሀረጎች ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ‹‹የማትሰራ ሴት›› ‹‹ስራ የሌላት ሴት›› ‹‹ገቢ የሌላት ሴት›› ‹‹ስራ አጥ ሴት›› ‹‹ስራ ፈት ሴት››ማንበብ ይቀጥሉ…

የእቴጌ እና የሂትለር ፎቶ

ባየኋቸው ቁጥር ግርርም ከሚሉኝ ታሪካዊ ፎቶዎች አንዱን ላካፍልዎት፡፡ በ1935 የተነሣው ይህ ፎቶው የተገኘው ባሶሼትድ ፕሬስ መዝገብ ውስጥ ነው፡፡ በፎቶው ላይ ለጊዜው ስሙን ያልደረስኩበት ሠዓሊ የግርማዊት እቴጌ መነን እና የአዶልፍ ሂትለርን ሥዕል ሲሸጥ ይታያል፡፡ በፎቶው ጀርባ ላይ እንደ ተገለጸው ከሆነ፤የጀርመኑ አምባገነንማንበብ ይቀጥሉ…

ሀገሬ

‹‹ሀገሬ…›› (መነሻ ሀሳብ ፤ ‹‹ ዘ ሬቬናንት›› ፊልም) በከባድ ንፋስና ዝናብ ሰአት ትልልቅ ዛፎችን አይታችሁ ታውቃላችሁ? የቅጠሎቹን ሳያቋርጡ መርገፍገፍ፣ የቅርንጫፎቹን መንቀጥቀጥ ስታዩ ‹‹ይሄ ዛፍ ካሁን ካሁን ወደቀ፣ ካሁን ካሁን ተገነደሰ ››ብላችሁ ሰግታችሁ ይሆናል፡፡ ቅርንጫፎቹ ቅንጥስ እያሉ ቢወድቁም፣ ቅጠሎቹ ባንድነት ቢረግፉም፣ ግንዱንማንበብ ይቀጥሉ…