ፀጥታ ነጋሲ

ይኼ አብኛዛውን የምንኖርበት አለም ፀጥታ ነው፡፡ ያልተነገረለት ነው፡፡ ሆሄ፣ ቃል፣ አንቀፅ፣ ምዕራፎች፣ ቅዳሴና ዘፈን፣ እንጉርጉሮና ምንትስ አልተነዳበትም የሚባል፡፡ ምድር ላይ ከተሰሩና ከተደረጉ ከታሰቡና ከታለሙ ነገሮች የተመዘገበው ስንቱ ነው? የአዳም የመጀመሪያ ሳቁ ተመዝግቧል? የመጀመሪያው የአዳም ወይ የሄዋን እንጉርጉሮ ይታወሳል? የሐጢያት መጀመሪያማንበብ ይቀጥሉ…

ኩልና ተኮላ

ተኮላ የተባለ ሰው አፍቅሬ በትዳር መኖር ከጀመርኩ አሁን ሰማንያ ሰባት ነው አይደል? አዎ አንድ አመት ተኩል አለፈኝ፡፡ በዚህ …. ማለት በቃ ከእሱ ጋር አንድ ቤት ውስጥ ሚስቱ ሆኜ በመኖሬ ደስተኛ ነኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በማያገባቸው መግባት የሚወዱ ወይም የማናቀፍ ጉጉታቸው ወሰንማንበብ ይቀጥሉ…

ቡቡ ዘተበሃለ ስንዝሮ (ከ “የስንብት ቀለማት” የተወሰደ)

ተረት ተራች ነኝ፡፡ ድሮ ድሮ እንደ እኔ አይነቱ ተራች፣ ጉዳይ ቀማሚ ፣ የታሪክ ጉድፍ ነቃሽ ‹ሐዳሚ› ይባል ነበር፡፡ በጥንት አፍ እንግዲህ ሐዳሚ ነኝ፡፡ ህይወት ተወሳስባ፣ ተተረማምሳና ተሸፋፍና ልታልፍ ስትል ለአፍታ ጆሮዎ ስር አቆማትና በአንደበቴ (በልሳነ ጥንት፣ በልሳነ ድንጋይ ዘመን ቀባጢሶ)ማንበብ ይቀጥሉ…

…ቸል ያደርገኛል

‹‹ከጠዋት እስከማታ እለፋለሁ፡፡ የምለፋውም በቸልታ፡፡ ነገሥታቶቹ ምቹ ላይ ይተኛሉ፡፡ የሚንቀጠቀጥ ማለፊያ እንጀራ ሰሀኖቻቸው ላይ ዘርግተው የእኔ የደንባራው ነገር ገርሟቸው በሳቅ ይፈርሳሉ፡፡ በንቀት የመጣ አለመግባባት እንጂ ሌላ ምንድን ነው? ይሄ ቸል ያደርገኝ ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ በቆዳ ቦት የታሰሩትን እግሮቼን ማታ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን (1928-1998)

ጸጋዬ ገብረ መድህን (1928-1998) ባዳ ተብላ በምትታውቅ አምቦ ካተማ አካባቢ በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት ቀኃሥ ትምህርት ቤት ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ ትምህርታችውን ከገፉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952 እንደማንበብ ይቀጥሉ…

የመጀመሪያው የአማርኛ ልቦለድ

በ1908 ዓ.ም. በሮም ባሳተሟት ልቦለድ ታሪክ የፈጠራ ሥራቸው-በኢትዮዽያ የአማርኛ ዘመናዊ ሥነጽሑፍ መሥራች ካሰኛቸው ማእረግ ባሻገር በአፍሪካ ቋንቋዎችም ታሪክ- በሀገርኛ ቋንቋ በመጻፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ የሚል ምስክርነት አግኝተዋል። ደራሲው ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ሲሆኑ የልብወለድ ድረሰታቸው ‘ጦቢያ’ ትባላለች። አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በ1860 ዓ.ምማንበብ ይቀጥሉ…

ከአዳም ረታ ቃለ መጠይቅ

. . . አብዮት ሲመጣ (እንዲመጣ ሲደረግ) ልብ ወለድ መጽሃፍት ቢረባም ባይረባም በፓምፍሌት ተተኩ፡፡ ለመጀመሪያ ሰሞን ደስ የሚል ነገር ነበረው፡፡ ምክኒያቱም አዲስ ነው፡፡ (እዚህ ዘመን ላይ ቦታ ስለማይበቃን ልዝለለው እንጂ በሰፊው የምለው ኑዛዜያዊ ግለ ሂስ ነበር) ብዙ ሳልቆይ ሲጀመር መሰላቸቴንማንበብ ይቀጥሉ…

የበላይ ዘለቀ እና የፋሺስት ኢጣሊያ ድርድር ታሪከ

በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ከባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አስኔ በወሎ ክፍለ ሐገር በቦረና ሳይንት አውራጃ በጫቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሩ ጉጣ ከተባለው ቀበሌ በ1904 ዓ.ም ተወለዱ። ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ሲወር በላይ ዘለቀ የ24 ዓመት ወጣት ነበር።ማንበብ ይቀጥሉ…