የጥንቲቱ ፋርስ ካፈራቻቸው ባለቅኔዎች መካከል ኣንዱ ኦመር ካያም ነው፡፡ ፈላስፋ ሳይንቲስት እና የተዋጣለት የሂሳብ ሊቅ ነው፡፡ሩባኣያት የሚል የግጥም ዘይቤ ፈልስፏል፡፡ሩባያት ኣራት መሥመር ያለው ሲሆን ከሦስተኛው መሥመር በቀር ሌሎች ቤት ይመታሉ ፡፡ ኦመር ካያም መናፍቅ ነበር፡፡ ትንሳኤ ሙታን መኖሩን ይጠራጠራል፡፡ህይወት ከስንዝሮማንበብ ይቀጥሉ…
ሸሌ ነኝ
‹‹ነይ እዚህ ጋር ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ…ብርድልብሱ ላይ ተኚ›› ሲለኝ፤ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር፡፡ ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ጊዜ መሽኮርመም፡፡ ሰው እንጂ ሴት ያልሆንኩ መስሎኝ፡፡ ስጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ፡፡ ገንዘብ ተቀብዬ ደስታን ልሰጥ ያልመጣሁ መስሎኝ፡፡ አንገቴን እንደሰበርኩ ወደማንበብ ይቀጥሉ…
ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና
ልጁ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡ ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣ ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ተቃርኖ
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ጆርጅ ኦርዌል “1984” በተባለ ልብወለዱ ውስጥ የጠቀሰውን፣ double think( ሁለት ተቃራኒ ሃሳቦችን በተመሳሳይ ሰዐት እውነት ናቸው ብሎ መቀበል) የሚከተል ይመስለኛል። ተቃርኖ #1 ወጣት በድሉ እጩ ዘፋኝ ነው (እጩ ካድሬ ብቻ ነው ያለው፣ ያለው ማነው? ) በቴሌቭዥን ከሚታዮ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
“የኛ ሰፈር ፌሚንስቶች”
( በማርች 8 ሰበብ ወዲህ የተሳበ።ሃሃሃ፣ ይሄን ሰፈር ባሰብኩት ጊዜ ለራሴ እድቃለሁ። አንዳዶች ይህ ፖስት ብልግና አለበት ይላሉ።ጭብጡ ብልግና አይደለምና አቋቋማችሁን አስተካክሉ። ከዛ ወደ ፅሁፉ…) **** የኟ ሰፈር “እናት ፌሚኒስቶ” አመፁ። የሚገርመው ማመፃቸው አይደለም፣ እሱን ሰፈሩ ለምዶታል። ድንገት ተነስተው ሁሉምማንበብ ይቀጥሉ…
ነገር ቶሎ አይገባኝም
ደም መላሽ እባላለሁ… ከደም ውጪ ታሪክ መዘገብ የሚከብደው ዓለም ላይ እኖራለሁ… አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንቸውን ከስክሰው… ሲባል፣ ክርስቶስ በደሙ አዳነን( በደሙ ሃጢያታችንን አጠበልን) ሲባል፣ ያለምንም ደም፣ ኢትዮጵያ ትቅ”ደም” ሲባል ( ትቅደም የሚለው ቃል፣ አፈፃፀሙም ቃሉም “ደም” እንዳለበት ሳይ)… አይገባኝም። ዓለምማንበብ ይቀጥሉ…
አራት ነጥብ (።)
አራት ነጥብ (።) ከቤት ስወጣ የሰፈሬ ሰዎች ሁላ ከዚህ በፊት አይቼው በማላቅ አግድም ወንበር ላይ በብዛት ተደርድረው ፀሀይ ይሞቃሉ። ፊታቸው ላይ ደስታ ባራት እግሩ ቆሟል። የወንበሩ ቁመት ከዚህ በፊት አይቼ የማላውቀው አይነት ነው። ምቾቱም ሳይቀመጡ የሚገምቱት ነው። አንድ ቀን ቁጭማንበብ ይቀጥሉ…
ለምን አትተኛም።
እሰከመቼ በአሳቻ ለሊት፣ በሀሰተኛ ዶሮ ጩኸት እየነቃህ!? አርፈህ አተኛም? አርፈህ አገሩን አትመስልም? ይልቅ እንካ ምክር፣ ሀሰተኛ ዶሮ በኳኮለ ቁጥር፣ የሚናድ፣ የሚጣስ የእንቅልፍህ አጥር መኖርህን አብዛ ከመተኛት ቅጥር። ** ተኛ። ብትችል አውቀህ ተኛ። “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ” ይላል የተኚዎች ተረት።ማንበብ ይቀጥሉ…
ውልደትህን ከማይሻ…
ብዙዎች በሚወዱት ቀን፣ ብዙዎች የማይወዱትን ግጥም ብንለጥፍ… የሚወደን አምላክ ምን ይለናል? እሱ ምንም አይልም፣ የሱ ነን የሚሉት እንጂ… አዳም፣ በብዙ ምግብ መካከል አንዲቱን ቢከለከል እሷኑ አንክቶ በላ፣ ከእግዜር ጋር ፍቅራቸው ላላ። እኔ፣ በብዙ ምግብ መካከል፣ አንዲት ጉርሻ ተነፍጌ፣ በማይላላ የጠኔማንበብ ይቀጥሉ…
ሰጎች
ሰዎች ይመስሉኛል። በጎችም ይመስሉኛል። ሰዎች ብዬ ስጠራቸው አቤት ይላሉ። በጎች ብዬ ስጠራቸውም አቤት ይላሉ። ሰዎች ናቸው በጎች? በቡድን ነው የሚኖሩት። በቡድንን ይንቀሳቀሳሉ።እንደማንነታቸው ሁሉ አንዳቸውን ከአንዳቸው ለመለየት ከባድ ነው። ጠጋ ብዬ እረኛቸውን ጠየኩት። “አልገባኝም በጎች ናቸው ሰዎች? ” ፈገግ ብሎ መለሰልኝ፣ማንበብ ይቀጥሉ…