(የመትከል ባህል የሌለው ሕዝብ እንትከል ስትለው አወዳደቁን እየተለመ ይስቃል) — ስሜነህ አያለሁ እና ቢኒያም ሲሳይ የፃፉት፣ «what is in a term? A historical and linguistic examination of the revolutionary terminology:yiwdem, “let it be demolished, down with,” 1974-1977» የሚል ወረቀት አለ።ማንበብ ይቀጥሉ…
የ‹‹ፌዴራሊስቶቹ›› ኅፀፅ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰርክ የምትታይ፣ ከዚህ ቀደም ደግሞ እንዲሁ ችግር ሲፈጠር ተደጋግማ ብቅ የምትል ቅጥፈት/ዝንፈት አለች። እሷም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎችን ‹‹ፌዴራሊስት››ና ‹‹አሀዳዊያን›› አድርጎ የመክፈል ሙከራ ናት። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ‹‹ፌዴራሊስት›› ነኝ ማለት የተራማጅነትና የሞራል ልዕልና መገለጫ ተደርጎም ይቀርባል። እነዚህን ሁለትማንበብ ይቀጥሉ…
ለሌሎች መጮህ ለራስም መጮህ ነው!
ዝምታ ጥሩ የሚሆንበት ጊዜ አለ፤ ክፉም የሚሆንበት ጊዜ አለ። ዝምታን እንደየሁኔታው ማከናወን ከብልህ ሰው ይጠበቃል። ዝምታህ ለከት ይኖረው ዘንድ ማስተዋል ይፈልጋል። በሆነ ባልሆነው ከመዘባረቅ፣ በማይመለከትህ በሌሎች ሰዎች ግላዊ ጉዳይ ከመቀባጠር ዝም ማለት የተሻለ ነው። ዝምታን ወርቅ ማድረግ የሚችሉት የዝምታ ቅኔነትንማንበብ ይቀጥሉ…
እንደማመጥ
እድሜየ ላቅመ ምክር ስለደረሰ ልመክር ነው፤ ስልጣንህን ተጠቅመህ የተወዳዳሪህን የመናገር ነፃነት ስታፍን ፤ራስህንና አገርህን በሁለት መንገድ ትበድላለህ። አንደኛ ልክህን እንዳታውቅ ትሆናለህ! ዜጎች ባስተዳደርህ ላይ የሚያቀርቡትን ቅሬታ ካልሰማህ እንዴት ልክህን ታውቃለህ? ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው፤ብዙ አምባገነኖች የወዳጆቻቸውን ከንቱ ውዳሴ የህዝብ ድምፅማንበብ ይቀጥሉ…
እኛ ነን እኛ!
መግደልና መናድ እንጂ! ተስማምቶ መኖርና ማኖር ያቃተን፣ በሃሳብ መሸናነፍ እጅግ የከበደን፣ ከመካብ ይልቅ ማፍረስ የሚቀለን፣ የሃሳብ ልዩነት ሁሌም የሚገለን። በመጠፋፋት ታሪካችን! ዓለሙ የሚያውቀን፣ በዚህም የሚንቀን፤ የመገዳደል አዚም የተጋተን! ክፉ አዙሪት የሚነቀንቀን። የውጪ ጠላት ሲመጣ የምንስማማ፣ የውጪ ጠላት ሲጠፋ… እርስበርስ ተጠላልተን፣ማንበብ ይቀጥሉ…
የባህርዳሩ ክስተት – “የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” ወይስ ሌላ?
መንደርደሪያ ሰኔ 15 በባህርዳር የተከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ እያነጋግሩ ካሉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ክስተቱ ምን ተብሎ መጠራት አለበት የሚለው ነው። ሁኔታውን ‹‹መፈንቅለ-መንግሥት›› ብለው የጠሩትና ቃሉን ለመጀመሪያ ጊዜ በደምበኛ(ሜይንስተሪም) ሚዲያ የተጠቀሙት በመንግሥት ሚዲያ የመጀመሪውን መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አፈቀላጤ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።ማንበብ ይቀጥሉ…
በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር
“በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር፤ በዘመን ሂደት የችግር ካንሠር ይሆናል።” ለአንዲት ሐገር ዘመንን የሚዋጅ፣ ትውልድን አንደአዲስ የሚቀርፅ ጥበብ ያስፈልጋታል። ሐገርን ወደኋላ የሚጎትት የማይጠቅም አስተሳሰብ በአዲስና በተሻለ አስተሳሰብ መለወጥ ከዜጎች የሚጠበቅ ተግባር ነው። ያረጀውን ማደስ፣ የሌለውን ጥበብ መፍጠር፣ ያልነበረውን መልካም ተሞክሮ መቅሰምማንበብ ይቀጥሉ…
ትብልዬ
የማያልፉት የለም ፣ ያ ሁሉ ታለፈ ታጋይ የህዝብ ልጅ ፣ ምርጫ በሌለበት ፣ ምርጫ እያሸነፈ በደሙ በላቡ ፣ ትውልድ አከሸፈ🙄(ርዕሱ አይደለም😂) ።። መቸም የማያልፉት የለም ያ ሁሉ ታልፎ ያ ሁሉ መሥዋእት ተከፍሎበት የግንቦት 20 በዓል አከባበር በዚህ ደረጃ ቀዝቅዞ ማየትማንበብ ይቀጥሉ…
ፉት ሲሉት ጭልጥ
ግንቦት ሃያ ተመልሶ መጣ። ከሶስት አመታት በፊት የግንቦት ሃያ አረፋፈዴን እንደዚህ አውግቻችሁ ነበር ። ።።።።።።።።።።።። ዛሬ.. ግንቦት 20 ማለዳ 1.45 ከበራፌ ላይ ቀጭን እና ስለታም ድምፅ ‹‹ልዋጭ! ልዋጭ!›› እያለ ሲጮህ ነቃሁ። የዚህ ሰውዬ ድምፅ በዛሬ ቀን ከነገር ሁሉ ቀድሞማንበብ ይቀጥሉ…
“የቡዳ ፖለቲካ”
ሁሉም ችግር ያወራል። ሁሉም ወቃሽ ነው። ሁሉም ተጠቅቻለሁ ባይ – ሁሉም በደል ቆጣሪ ነው። እነከሌ ይራገማሉ። እነከሌም ያሳቅላሉ። ሁሉም ነገድ የተገፊነት ተረክ አለው። ሁሉም ጠላት እና ጨቋኝ አለው፤ ሁሉም በጋራ ይከሳል.. ሁሉም በጅምላ ይከሰሳል፤ ‘ጸረ ሰላም፣ ጨቋኝ፣ ሴረኛ፣ ለውጥ አደናቃፊ፣ማንበብ ይቀጥሉ…