የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አንድ ጽሑፍ እናበረክታለን ባልነው መሰረት ይህንን ኢትኖግራፊ ቀመስ ወግ ጀባ ልንላችሁ ነው። ታዲያ እኛ ባደግንበት አካባቢ በሚነገረው ትውፊት በዓሉ “ኢሬሳ” እየተባለ ስለሚጠራ በዚህ ጽሑፍ ውስጥም “ኢሬሳ” የሚለውን ስም መጠቀሙን መርጠናል። ወደ ነገራችን ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ የሚወሱትማንበብ ይቀጥሉ…
ኢህአፓ፣ መኢሶን እና የሃይሌ ፊዳ የፖለቲካ ህይወት
የመኢሶን መስራች የነበረው ሀይሌ ፊዳ በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ፋኖዎች አንዱ ነው። ይህ ሰው በ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ሰፊ አሻራ ጥለው ካለፉት ግለሰቦችም አንዱ ነው። አንዳንዶች የግለሰቡን ሚናና ስራውን እያዳነቁ ጽፈውታል። እንደ ሰማእትም ያዩታል።ማንበብ ይቀጥሉ…
የመታወቂያው ጉዳይ (አራተኛው ሙከራ)
“ሚስተር ኤክስን ያያችሁ” መታወቂያዬ ላይ በግድ የተፃፈብኝን የብሔር ማንነት ዜግነት ኢትዮጵያዊ ለማስባል ጥረት ያደረግኩበትን የባለፈውን ሳምንት የሦስተኛ ቀን ሙከራዬን ትረካ ያበቃሁት ከክፍለ ከተማው (በዘልማድ እንደሚባለው አውራጃ) ፍርድ ቤት ወደ ፌደራል ፍርድ ቤት ጉዳዬን እንዳቀርብ መላኬን ገልጬ ነበር። የዛሬውን ሙከራዬን እነሆ፡-ማንበብ ይቀጥሉ…
የመታወቂያው ጉዳይ
“ግራጁዬት ሎየር ነኝ” ድንቄም በግድ የተፃፈብኝን የመታወቂያዬን ብሔር ስያሜ ወደ ኢትዮጵያዊ ለማስቀየር ዛሬ ሶስተኛ ቀን ሙከራዬን ቀጥዬ ውያለሁ። ባለፈው ሳምንት የክፍለ ከተማውን ኃላፊ ሰኞ ወይ ማክሰኞ መጥቼ እንዳነጋግር ተቀጥሬ ነበር ትረካዬን ያቆምኩት። እነሆ የዛሬ ውሎዬ፡- የክፍለ ከተማው የወሳኝ ኩነቶች ሀላፊማንበብ ይቀጥሉ…
ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
አሪፍ የፍቅር ግጥም ጽፌ ለመለጠፍ አስቤ ነበር። ግን ብለው ብሠራው “ እኔ እምልሽ ውዴ” ከሚለው ቃል ውጭ ጠብ ሊልኝ አልቻለም። እኔ እምልሽ ውዴ! ብለው ሳይጀምሩ- ስለፍቅር መጻፍ አይቻልም እንዴ? አንዳንድ ባለንጀሮቼ በውስጥ መሥመር ይሄን ድብርታም ዘመን እንዴት እያሳለፍከው ነው ምናምንማንበብ ይቀጥሉ…
የመታወቂያው ጉዳይ
የቀድሞው ቀበሌያችን አሁን አድጎ ወረዳ ሆኗል። ከጠዋት ጀምሮ እስከ አሁን መብራት የለም ስለተባለ የመታወቂያ እድሳት ጉዳይ ለዛሬ አይሳካም ተብሎ ተመልሻለሁ። ጥያቄዬን ግን ለተረኛው ሹም “ብሔር – ኢትዮጵያዊ የሚል መታወቂያ ይሰጠኝ” ስል አቅርቤ በፈገግታ እና በአግራሞት ሳቅ “ቅፁ ላይ ካለው ወይማንበብ ይቀጥሉ…
ተጠየቅ መስከረም
አዲሱ ዓመት በእውነት አዲስ ይሁንላችሁ! ለሁላችንም የነጻነት፣የሰላም፣ የፍቅር፣ የሥራና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን ተጠየቅ መስከረም! ተጠየቅ መስከረም፤ ዛሬስ ዋዛ የለም አንተን ለመቀበል እንቁጣጣሽ እያልን፤ ከርስ እንሞላለን፤ እንሳከራለን፤ እንጨፍራለን፡፡ አልገባኝም እኔን አንተ መወደድህ፤ ስትገባ ስትወጣ ድግስ መቀበልህ፤ ዶሮው፤ በጉ፤ ሰንጋው ይታረድልሃል፤ ርጥብማንበብ ይቀጥሉ…
ተ ላ ቀ ቅ
ከሕላዌው ጽንፍ አልባ እውነት ራስን የመነጠል ግብግብ። ከሆኑት መሆን ሌላ መሆንታን መሻት። ከአማናዊው እውነት ተናጥሎ በሃሳብ ደሴት መገለል። የኔ/ኛ፣ የእነርሱ፣ የነዚያ ባይነት ፍረጃ። ነኝነት ከሌላው የተለየ መሆንን ሲሰብክ መሆን /Being/ ቅዠት ውስጥ ይቧችራል። ነኝነት ጥግ ሲያሻትት የመሆን ቀለም ይደበዝዛል። የሆንከውንማንበብ ይቀጥሉ…
“ሦስተኛው ይባስ”
1. ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ስመ ጥር መኮንን ነበሩ። ከፍተኛ ዲፕሎማት በመሆን ለዓድዋ ጦርነት የሩሲያ መንግስትን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እና የህክምና እርዳታ እንድናገኝ ያደረጉ ስኬታማ ሰው ናቸው። እኝህ ሰው ታዲያ ከሩሲያ በዲፕሎማሲያዊ ስኬት ተመልሰው እረፍት እንኳንማንበብ ይቀጥሉ…
ሰው ሳይቀና ሀገር አይቀናም
አንድ ሰው ራሱን በዘር መግለፁ ችግር ያለው አይመስለኝም። ችግሩ ዘረኛ መሆን ላይ ነው።ዘረኛ መሆንም ሃሳብ እንጂ ተግባር እስካልሆነ የከፋ ችግር አይሆን ይሆናል። ግን፣ዘረኝነት በልብ ይዘው የሚቆዩት ብቻ አይደለም። ካልወጣ፣ ሌሎች ካልጠላ፣ አጋጣሚውን ሲያገኝም ካልደቆሰ አስችሎት አርፎ መቀመጡን እንጃ! አንዳንድ አስተሳሰቦችማንበብ ይቀጥሉ…