ማን ይቀስቅሰን?

“አጥር መስራት የውሻ ተግባር ነው” ~ የገዳ ስርዓት — እንደ ማሕበረሰብ አንቀላፍተናል… ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነን… ለሞት የቀረበ እንቅልፍ… ችግሩ ማንቀላፋታችንን አናውቅም… ማንቀላፋታችንን ስላላወቅን የተኛንበትንም አናውቅም… ማንቀላፋታችን ደግሞ በሌባ አስደፍሮናል… ችግሩ መሰረቃችንን አናውቅም… ወይም ግድ የለንም… የተዘረፍነው ግን አማናዊነት ነው…ማንበብ ይቀጥሉ…

የዘውግ ፖለቲካ እንደ ሀገር?

ወደ 25 ሀገሮች ፌደራሊዝምን ይከተላሉ ይላል አሰፋ ፍስሃ ስለ ፌደራሊዝም በፃፈው መፅሐፍ። ያዋጣቸውን አዋጥቷቸው ይሆናል። የኛ ግን የቆመበት መሰረት በራሱ «ፀብ ለሚሹ የሜዳ ጠረጋ» ስለሆነ አልተሳካም ብንል አያኳርፍም። የዘውግ ፖለቲካ አያዋጣም ሲባል እንዲሁ ሳስበው ደስ አይለኝም ከሚል የሚሻገር ሰበብ አለው።ማንበብ ይቀጥሉ…

የኩባያ ወተት ወይስ የኩባያ ውሃ?

ስመጥሩ የእስልምና ታሪክ ተመራማሪና ፀሃፊ አህመዲን ጀበል ለ‹‹ከመጋቢት እስከ መጋቢት›› በተቀረፁት አጭር ቪዲዮ ላይ የተጠቀሟት ታሪክ ደስ አለችኝና አመጣሁላችሁ። ታሪኳ እንዲህ ትላለች። አንድ መሪ ህዝቡ ምን ያህል እንደሚወደው ለማውቅ ፈለገና አደባባይ ላይ ትልቅ በርሜል አስቀምጦ ህዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ። ‹‹የሚወደኝማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹የድሬ ሰው ነፍሴ››

  የሚያንገረግበውን የድሬ ሙቀት መብረድ ጠብቄ አመሻሹን ሻይ ልጠጣና በእግሬ ወዲህ ወዲያ ልል ከሆቴሌ ወጣሁ።  ለብ ባለው ንፋስ እየተደሰትኩ፣ ቱር ቱር በሚሉት ባጃጆች ካለጊዘዬ ላለመቀጨት እየተጠነቀቅኩ ከተዘዋወርኩ በኋላ ለሻይ አንዲት ትንሽ ቤት ቁጭ አልኩና ምን ይምጣልሽ ስባል ‹‹ቀጭን ሻይ›› ብዬማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹በሃገር ነው››

ጎረቤቴ ካለው ቤተክርስትያን የሚመጣው የቅዳሴ ዜማ እና የወፎች ዝማሬ አነቃኝ። እንዴት ውብ አነቃቅ ነው! በሰላም አሳድሮ ይሄንን አዲስ ቀን ስላሳየኝ ምንኛ የታደልኩ ነኝ? ዛሬን ከማያዩት ስላልደባለቀኝ ምንኛ አድለኛ ነኝ? አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ተንጠራራሁ። ሌላ ጊዜ ቅዳሜ እንደማደርገው አልጋ ውስጥ ስንደባለልማንበብ ይቀጥሉ…

የምንችለውን ወይስ የሚገባንን?

የሚቻለውን መሥራት የዐቅም ጉዳይ ነው። የሚገባውን መሥራት ግን የሕግና የሞራል ጉዳይ ነው። ኃይልን ለመጠቀም የሚያስችል ትምህርት ለሚማሩ ሰዎች በጥብቅ የሚነገራቸው ነገር ቢኖር የተገቢነት ጉዳይ ነው። ካራቴ፣ ጂዶ፣ ቦክስ፣ ውትድርና፣ ፖሊስነት የተማሩ ሰዎች ኃይልን ለመጠቀም ቅርብ ናቸው። በእጃቸው ማጠናፈር፣ በእግራቸው መዘረር፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ስለፍቅር በስምአብ ይቅር!!

በዙረት ካገኘሗቸው እውቀቶች አንዱን በማካፈል ወጌን ልጀምር። ያፍሪካ ስደተኞች ያንዱን ያውሮፓ አገር ድንበር አቋርጠው ይገቡና አንድ ከተማ ውስጥ አድፍጠው ይቀመጣሉ። በከተማው ባንድ ስፍራ ላይ መንግስት ገንብቶ ያልጨረሰው ባዶ ህንፃ ይኖራል። ስደተኞች ከለታት አንድ ቀን ተደራጅተው ህንፃውን ወርረው ይይዙታል። የህንፃውን አፓርታማማንበብ ይቀጥሉ…

“የሚያጀግነውን የሚያውቅ ህዝብ የተባረከ ነው”

ባገራችን የነገስታት መታሰቢያ ሀውልት ማቆም: በጀግና ተዋጊዎች ስም ጎዳናዎችንና ትምርትቤቶችን መሰየም የተለመደ ነው። አገሩ በሙሉ በጦርና ጋሻ ምልክት የተሞላ ቢሆንም አሁንም በወታደሮች: በጌቶችና በእመቤቶች ስም ሀውልት የማቆም ግፊቶች ቀጥለዋል ። በፖለቲካው ግርግር መሀል: ለህዝብ መንፈሳዊ እና አእምሮአዊ እድገት መዋጮ ያደረጉማንበብ ይቀጥሉ…

ግርምሽ ሲታወሱ

ግርማ ወልደጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሁኑው የተመረጡ እለት ብዙ ሰዎች ተገርመዋል ። ከእስክንድር ነጋ ጋዜጦች አንዱ ዜናውን የዘገበችው ” ወያኔ አበደች ” በሚል ርእስ እንደነበር ትዝ ይለኛል። አንድ አሙስ የቀረው ሽማግሌ እንዴት ለዚህ ሚና ይታጫል በሚል እብሪት የተቹ አልጠፉም ። ብዙዎቻችን “ሽማግሌማንበብ ይቀጥሉ…

ትናንት ዛሬ አደለም

ይገርማል!! ያገራችን ገበሬ የሚያርስበት በሬና ማረሻ ጥንታዊ ሰው ከአራት ሺህ አመት በፊት ይገለገልበት የነበረውን ነው። ይሁን እንጂ ቢቀናው ክላሺንኮቭ ይታጠቃል። ደሞ ገበሬውን ዘመናዊ ጠመንጃ እንጂ ዘመናዊ ማረሻ ለማስታጠቅ የሚያልም አክቲቪስት አይተን አናውቅም። ዘመናይ የብሄር አክትቪስት ጦርነት በናፈቀ ቁጥር ያባቶቹን ጀብድማንበብ ይቀጥሉ…