ስለ ያ ቡዳ

“እንጫወት እንጂ የምን ማፈር ማፈር ያ ቡዳ ሳይመጣ ሳይጫነን አፈር ‘ -(የማንኩሳ ዘፈን )- ስለሞት ሁለት አይነት አመለካከት አውቃለሁ ፤ የመጀመርያው ከሃይማኖታዊ መገለጥ የመነጨና ብዙ ህዝብ የሚያምንበት ነው፤ ሰው የእግዚያብሔር አምሳያ ፍጡር ነው፤ ሲሞት ነፍሱ ወደ ሰማይ ትሄዳለች፤ ምግባረ ሰናዮችማንበብ ይቀጥሉ…

የሆነ ምሽት

ይሄ ንፍጣም ቫይረስ ወደ አገራችን ከመግባቱ ሁለት ወር አስቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደ ጉድ ጨፈርኩበት! ዛሬ እንዲህ ተጨማድጄ ልቀመጥ ያኔ እየዞርኩ የክለብ ምንጣፍ በዳንስ ሳጨማድድ አመሽ ነበር! የዚያን ቀን ምሽት ከጊድዮን ጋር ነበርሁ፤ ባለትዳር ነው፤ የሚስቱና (ዛዮን) የሶስት ልጆቹ ፎቶ በስልኩማንበብ ይቀጥሉ…

ከታጋቹ ማስታወሻ የተቀነጨበ

ብዙ ያሜሪካ ላጤዎች ውሻ አላቸው። እኔ ውሻ የማሳድርበት አቅም የለኝም፤ ቢሆንም በቅርቡ ቤት ውስጥ ከሚርመሰመሱት ጉንዳኖች መካከል የሰልፍ መሪውን መርጨ አለመድኩት፤ ምሳ ስበላ አንድ ሩዝ ፍሬ ጣል አደርግለታለሁ፤ ወደ ዘመዶቹ ይዞ ሊሄድ ሲል አንገቱን ይዤ አስቀረዋለሁ፤ እኔ የስዊድን ቮድካየን ስቀመቅም፤ማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ይሄ ቀሳ ግን ስንቱን አሳበደ? ቲክቶክ ምስክሬ ነው፤ የድሮ እብድ ሙዚቃ ቤት በር ላይ ይደንስ ነበር ፤ የዘንድሮ ዲጅታል እብድ ደሞ ሞባይሉ ካሜራ ፊት ይደንሳል ፤ እኔ ራሴን እየታዘብኩት ነው፤ አሁን“ ዘፈን ሃጢአት ነው አይደለም?” በሚል ክርክር ላይ በስካይፒ መሳተፌማንበብ ይቀጥሉ…

አመፅ!!

በለው! በለው! ዛሬ ታሪክ ተሰራ! ከተማውን ባንድ እግሩ አቆምነው!! “ሽጉጥ መትረይሱን አንግቶታል ያ ጥቁር ግስላ ደም ሽቶታል” የሚለውን የአለማየሁ እሼቴን ዘፈን በአለማየሁ ፋንታ ድምፅ እያንጎራጎርሁ ከቤቴ ወጣሁ ፤ ፓርኩ ላይ ስደርስ አንዲት ደርባባ ኤሽያዊት ሰልፈኛ ተዋወቅሁ፤ ከኢትዮጵያ እንደሆንኩ ስነግራት አይኗማንበብ ይቀጥሉ…

ትዝታየ በፎቶ ዙርያ

በልጅነቴ ትዝ ከሚሉኝ መፈክሮች አንዱ “ያልሰራ አይብላ” የሚል ነው። ስራ ብሄራዊ ሀይማኖት ሆኖ ነበር። ይሄ ደግሞ በጊዜው ፎቶ አነሳስ ላይ ሳይቀር ይንፀባረቃል ፤ አንድ ሰው ፎቶ ሲነሳ የሆነ ሰርቶ ማሳያ ነገር ፎቶው ውስጥ ማካተት ነበረበት፤ የቤት እመቤት ከሆነች ጥጥ እየፈተለችማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ፎቶ (ክፍል አንድ)

ልጅ እያለሁ ፎቶ ብርቅ ነበር ፤ ከእናቴ ጋራ የሆነ ግብዣ እሄዳለሁ፤ የቤት እመቤቲቱ ቡናው እስኪፈላ ከግድግዳው ላይ መስኮት የሚያህል ባለፍሬም ፎቶ መስቀያ አውርዳ በዳንቴል ወልወል አድርጋ ትጋብዘናለች። በፎቶው ውስጥ ሚስት ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ፤ገብረክርስቶስ ጫማ አድርጋ ቁጢጥ ብላ ትታያለች ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ ከመረጥሽ በኋላ (ክፍል ሶስት)

አጭር ገመድ ማነኝ ብለሽ ትሄጃለሽ? ስለዚህ የሚስቱን ለቅሶ አትሄጅም ። ቀብሯ ላይ አትገኚም። አቶ ይሄይስ የጠበቀው ቢሆንም ከባድ ሃዘን ላይ ስለሆነ ከሳምንት በላይ አይደውልልሽም። የገባልሽን ቃል ሳያጓድል – ግን ደግሞ ምንም ሳይጨምር መንፈቅ ያልፋል። የመንጃ ፈቃድ አውጥተሸ ኒሳን ጁክ መያዝማንበብ ይቀጥሉ…

ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ ከመረጥሽ በኋላ (ክፍል ሁለት)

ያለ ተጨማሪ ጥቅማጥቅም ለተከታታይ ቀናት በግብዣ ያጣድፍሻል። በስጦታ ያንበሸብሽሻል። ምንም ነገር ውድ ነው ከማይል ወንድ ጋር መሆን ምንኛ ያስደስታል? ያየሽውን ሁሉ በሁለትና በሶስት አባዝቶ፣ ያማረሽን ሁሉ በጅምላ ገዝቶ የሚሰጥ ወዳጅ እንዴት ያረካል? ብለሽ ታስቢያለሽ። የቁርስ-ብረንች-ምሳ- እራት ግብዣዎቹ ያልለመድሻቸው አይነት ናቸው።ማንበብ ይቀጥሉ…

የፖለቲካ ቋንቋችን

እጄን በሳሙና ከመታጠብ በተረፈኝ ጊዜ ለንጀራ የሚሆን ስራ እሰራለሁ፤ ማታ ማታ ደግሞ አፌ ላይ ነጭ ሽንኩርት፤ ትከሻየ ላይ ነጭ ጋቢ ጣል አድርጌ ዩቲውብ ላይ እጣዳለሁ፤ ከፊልሙም ከዘፈኑም ቀማምሼ ያገሬን ቃለመጠይቅ ወይም ውይይት መመልከት እጀምራለሁ:: አልናደድም፤ አላዝንም፤ እንቅልፍ ደርሶ ከነዚህ ስሜቶችማንበብ ይቀጥሉ…