የቀሰቀሰኝ የሙልጭታ ድምጽ ነው –የማዳለጥ። ማታ ራት በልተን፥ እዚያው የተውነውን ሳህን በዕንቅፍ ልቧ ሳትረግጠው አልቀረችም። አስታውሳለሁ በዕንቅልፍ ልቧ የመሔድ ችግር እንዳለባት የነገረችኝ እንደቀልድ ነበር። –ደግሞ እንዳትደነግጥ በዘረመላችን ያለ ነው። እናቴም ስሊፕ ዋከር ነበረች ሂሂሂ… ብላ ስትነግረኝ የምሯን አልመሰለኝም ነበር። (ዐምደኛማንበብ ይቀጥሉ…
የተሻለ ሃሳብም ጀግና አሳቢም አጣን!
ማሰብ መቻል ልዩ ፀጋ ነው። ሃሳብን መርጦ መተግበር ደግሞ ሰው በራሱ ላይ የሚያመጣው በረከት ነው። ማንም ለሆዱ የሚስማማውን ምግብ እንደሚመርጠው ሁሉ ለአዕምሮውም የሚመጥን ሃሳብን መመገብ ራስን መጥቀም ነው። ንፁህ ምግብ ሰውን ከበሽታ እንደሚከላከለው ሁሉ ንጹህና መልካም ሃሳብም ሰውን አፍራሽ ተልዕኮማንበብ ይቀጥሉ…
መርታት፤ መረታት፤ መገገም
የሆነ ጊዜ ላይ ረከቦት ጎዳና፤ ባንዱ ካፌ ውስጥ፤ ቡና ስጠጣ፤አንድ ጎረምሳ ወደ ተቀመጥኩበት መጣ፤ልጁ ግድንግድ ነው፤ጎልያድ ዳዊትን አዝሎ ያክላል፤ እኔ ደሞ እንደምታውቁኝ ነኝ፤ከፊቴ ሲቀመጥ የሚጥሚጣ ብልቃጥ አከልኩ፤ ግብዳው ብዙ ሳይቆይ የምነት ክርክር ጀመረ፤በተቻለኝ መጠን ወደ ክርክሩ ላለመግባት ተግደረደርኩ፤ ሰውየው ግንማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ስቀና….››
የታሪክ ሃሳብ፡ ዶርቲ ፓርከር ‹‹The Sexes› (1926) አኩርፌዋለሁ። ሳሎኔ እንደገባ ‹‹ተቀመጥ›› ብለውም ሶፋዬ ላይ አኩርፌ በተቀመጥኩበት ቁልቁል ያየኛል።ፈራ ተባ ይላል፣ አይኑ አይኔን ይሸሻል። ከገባ ከሁለት ቃል በላይ ደፍሮ ማውጣት ተስኖታል። ፈርቶኛል። ይሄንን ታላቅ የኩርፊያ ደመና በምን እንደሚበትነው ስለጨነቀው ፈርቶኛል። የልብማንበብ ይቀጥሉ…
የማብራትና ማጥፋት ወግ
(የመጨረሻው ክፍል) ባገራችን፤ በባላባት ስርአት ወግ “ፈናወጊ “ የተባሉ አገልጋዮች ነበሩ፤የስራ ድርሻቸው ፋኖስ፤ አንዳንዴም ጡዋፍ ይዞ መቆም ነበር፤ራት ላይ ከጌቶች እና ከእመቤቶች ማእድ ትንሽ ፈንጠር ብለው ቆመው ያበራሉ፤ በቤተመንግስት ውስጥ መብራት ተሸክመው የሚያነጉም ነበሩ፤የመጀመሪያዎቹ የመብራት ምስሶዎች ነበሩ ማለት ይቻላል፤ ታድያማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹አፍሪካዊነት በጎነት››
እዚህ ኮንዶሞኒየማችን አራተኛ ፎቅ ላይ አንዲት ቆንጆ ልጅ አለች….ቁንጅናን ሳይሰስት የሰጣት እሷም ሳትሰስት ውበቷንና ሽቶዋን ለብሎኩ ነዋሪዎች በቸርነት የምታሳይ ቆንጆ ! እውነቴን ነው …አንዴ ስታልፍ ከአንደኛ ፎቅ እስከአራተኛ ፎቅ ደረጃው ሁሉ የሷን ውድ ሽቶ ይታጠንና ባለአራት ፎቅ ገነት ይመስላል ….በአካልማንበብ ይቀጥሉ…
የየመኒዎች ጨዋታ
በዚህ ወቅት የቅርብ ጓደኛዬ የመኒው ኮሎኔል ሙሐመድ አል ሐይደሪ ነው። ረመዳንን በአብዛኛው አንድ ቤት ነበር ያሳለፍነው። አሁንም አብረን ነው የምንውለው። በተለይ ከሰዓት አብረን ስንጫወት ነው የምናሳልፈው። በርካታ ቁም ነገሮችንም ከእርሱ እየተማርኩ ነው። —- ጦርነትን ሸሽቶ ከሀገሩ የወጣው ሙሐመድ አል ሐይደሪማንበብ ይቀጥሉ…
ሲጨልም
የመብራት የመጥፋት ትዝታ፤ከባለፈው የቀጠለ
ከጥቂት አመት በፊት የረር በር እኖር ነበር፤አንድ ቀን መብራት በጊዜ ጠፋ፤እስከ እኩሌሊት ድረስ ስላልመጣ ተስፋቆርጠን ተኛን፤ ዘጠኝ ሰአት ላይ ሚስቴ ቀሰቀሰችኝና ወደ ምኝታቤቱ መስኮት ጠቆመችኝ፤ የሆነ ግዙፍ እጅ ጥላ መስኮቱን ሲዳብስ ይታየኛል፤ “ሌባ ነው?” አልኩዋት፤ ራሱዋን ባዎንታ ወዘወዘች፤ “መስኮቱን ምንማንበብ ይቀጥሉ…
እምዬ ያልታደለች
እምዬ ያልታደለች ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች እምዬ ሰከረች ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች! የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋትማንበብ ይቀጥሉ…