‹‹ባይተዋር›› (ክፍል አንድ)

( በቢኮዙሉ ‹‹ኦቨር ናይት ስትሬንጀር›› ላይ ተመስርቶ የተፃፈ) ሰናይ እና ሜላት በስንት ጊዜያቸው ፣ ስንት ጊዜ ለምኗት፣ ስንት ጊዜ ተለማምጧት፣ ስንት ‹‹በናትሽ›› አባክኖባት፣ ስንት ‹‹የኔ ቆንጆ ስወድሽ››፣ ‹‹እስቲ አንዳንዴ እንኳን ያለልጆቹ እንደ ድሮው ወጣ ብለን እንዝናና›› አዝንቦባት እየጠጡ ሊያመሹ ቦሌማንበብ ይቀጥሉ…

የማርች 8 የስልክ ጥሪዎች…

ማርች 8 መጣሁ መጣሁ ሲል ፤ መቶ እና ከመቶ ሰው በላይ የሚያውቃቸው ሴቶች ስልክ በጥሪ የሚጨናነቅበት ወቅት ነው። እኔም እዚህ ፌስቡክ ላይ መቶ ምናምን ሰው ያውቀኝ የለ? አንድ እሽግ ስሜንም እኔንም የማያውቁ ሰዎች የሚያውቁኝ ሰዎች ፈቃዴን እንኳን ሳይጠይቁ ቁጥሬን ስለሰጡዋቸውማንበብ ይቀጥሉ…

ስለፍቅር በስምአብ ይቅር!!

በዙረት ካገኘሗቸው እውቀቶች አንዱን በማካፈል ወጌን ልጀምር። ያፍሪካ ስደተኞች ያንዱን ያውሮፓ አገር ድንበር አቋርጠው ይገቡና አንድ ከተማ ውስጥ አድፍጠው ይቀመጣሉ። በከተማው ባንድ ስፍራ ላይ መንግስት ገንብቶ ያልጨረሰው ባዶ ህንፃ ይኖራል። ስደተኞች ከለታት አንድ ቀን ተደራጅተው ህንፃውን ወርረው ይይዙታል። የህንፃውን አፓርታማማንበብ ይቀጥሉ…

ሰው በሰውነቱ

የምግብ ቤት ባለቤት የሆነ ሰውየ :በደንበኞቹ መሀል ሲዘዋወር አንድ ዝነኛ ጋዜጠኛ ይመለከታል። ወድያው ባለቤትየው አስተናጋጂቱን ጠርቶ ” እዛ ጥግ ላይ የተቀመጠው ጋዜጠኛ ይታይሻል? ሂጅና የሚፈልገውን እየጠየቅሽ ተንከባከቢው!! ወጥ ካነሰው ጨምሪለት!! እንዲያውም ለኔ ራት ከተሰራው ዶሮ አንድ ቅልጥም ብትሰጪው ደስ ይለኛል።ማንበብ ይቀጥሉ…

“የሚያጀግነውን የሚያውቅ ህዝብ የተባረከ ነው”

ባገራችን የነገስታት መታሰቢያ ሀውልት ማቆም: በጀግና ተዋጊዎች ስም ጎዳናዎችንና ትምርትቤቶችን መሰየም የተለመደ ነው። አገሩ በሙሉ በጦርና ጋሻ ምልክት የተሞላ ቢሆንም አሁንም በወታደሮች: በጌቶችና በእመቤቶች ስም ሀውልት የማቆም ግፊቶች ቀጥለዋል ። በፖለቲካው ግርግር መሀል: ለህዝብ መንፈሳዊ እና አእምሮአዊ እድገት መዋጮ ያደረጉማንበብ ይቀጥሉ…

ወዲህ በዳዊት ወዲህ በጋሻ!!!

ትላንትና ከባልንጀራየ ምኡዝ ጋር ተገናኝተን ቢራ ወይንና የመሳሰሉትን አልኮሎች ስንጠጣ:-አገርን በፍቅር ስለማስተዳደር አሰፈላጊነት ” በሰፊው ሰበክሁለት። እሱ እያዛጋና እየተቅበጠበጠ ሲሰማኝ ቆይቶ ሳያስጨርሰኝ የሚከተለውን ቀደዳ ቀደደ። “ማኪያቬሊ ስለተባለ ዝነኛ ደራሲ ሰምተህ ይሆን? ስለስልጣን ባህርይ እንደ ሌሎች ሳያለባብስ እቅጯን ፅፏል!! ይህ ሀቀኛማንበብ ይቀጥሉ…

ግርምሽ ሲታወሱ

ግርማ ወልደጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሁኑው የተመረጡ እለት ብዙ ሰዎች ተገርመዋል ። ከእስክንድር ነጋ ጋዜጦች አንዱ ዜናውን የዘገበችው ” ወያኔ አበደች ” በሚል ርእስ እንደነበር ትዝ ይለኛል። አንድ አሙስ የቀረው ሽማግሌ እንዴት ለዚህ ሚና ይታጫል በሚል እብሪት የተቹ አልጠፉም ። ብዙዎቻችን “ሽማግሌማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ስንኞች

እንዳለመታደል ሁኖ የጎጃሙ ጌታ የራስ አዳል ልጆች አሪፍ ያገር አስተዳዳሪ አልነበሩም። እንደመታደል ሆኖ ደሞ የተዋጣላቸው ባለቅኔዎች ነበሩ። ግጥሞቻቸው ከኑሯችን ጋር በጣም የተቆራኙ ናቸው። ለምሳሌ የግፍ ዘገባ በሰማን ቁጥር የምንቀባበለው። “የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል” የሚለውን ገራሚ ግጥምማንበብ ይቀጥሉ…

ኖረሽ እይው በቃ

(ለoptimistቶች) ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ ዘልለሽ አትጠግቢ ስቀሽ አትሰለቺ ወርሃ- ፅጌ ነው አመት ሙሉ ላንቺ። ደሞ በየቀኑ ፋሲካ ነው ኑሮሽ ያለም ሰቀቀኑ ሩቅ ነው ለጆሮሽ (የፍጥረት ሰቆቃ) ለጋ ነው አእምሮሽ ገላሽም ነው ጮርቃ ሌላም አልልሽም ኖረሽ እይው በቃ። በየጎዳናሽማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

ባለፈው ከውጭ ወዳገር ቤት ስመጣ አንዱ ደውሎ:- ” ጀለስካ ወዳገር ቤት ለመግባት ኤርፖርት ታይተሃል የሚባል ነገር ሰማሁ ልበል” ” ልክ ነው!” “በሩ ላይ ጠብቀኝ ታክሲ ይዤ መጣሁ” “እቃ ውሰድልኝ ልትለኝ ባልሆነ?” “ምናለበት ብትቸገርልኝ” ” አዝናለሁ ሻንጣየ ውስጥ ላየር ማስገብያ የሚሆንማንበብ ይቀጥሉ…