እውነት ለመናገር፥እኔ እምፈልገው ካንቺ ጋር መጋባት ይህን ሐምሌ ፊቴን፥ ደጋግሞ ማራባት ከወፎች ጋር መንቃት፥ በጊዜ ቤት መግባት “ምንም ድሀ ቢሆን፥ ባይኖረውም ሀብት ከደጃፍ ሲቀመጥ፥ ደስ ይላል አባት” ለሚል መናኛ ጥቅስ ፥ ኑሮየን ማይመጥን ሲሻኝ በየባንኩ፥ ስፈልግ በሳጥን የተረፈኝ ገንዘብ ደጃፍማንበብ ይቀጥሉ…
ድንኩዋን ሰባሪው
አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ነው። የቸሬ ድህነት ግን ወለል እንኩዋ የለውም። ከቸሬ ጋር ስትወዳደር ድህነት ራሷ ሀብታም ናት። እኔ ግን ምናለ መፈላሰፉን ትቼ ወደ ታሪኩ ብገባ ! በቀደምለት ቸሬ ተፈናቃይ ወገኖቻችንን በጉልበትና በፀሎት ለማገዝ ወደ ስፍራውማንበብ ይቀጥሉ…
ወፋ በፌስቡክ
በድሮ ጊዜ በኢትዮጵያ ባንዳንድ ገጠሮች ውስጥ “ወፋ” የሚባል ልማድ ነበር። ያንድ ቀበሌ ባላገሮች ከወንዝ ወዲህ ማዶ እና ወድያ ማዶ ተሰላልፈው በጩቤ በጦር በዱላ ይከሳከሳሉ። አንድ ባላገር ከገበያ ሲመለስ የወፋ ጦርነት ሲካሄድ ከተመለከተ ቆም ብሎ ቅርጫቱን ያስቀምጣል። ከዚያ በቅርብ ከሚያገኘው ጎራማንበብ ይቀጥሉ…
ቅንጣቢ የምፅዋ ወግ
‹‹የት ነው የሚሄደው? ›› ይሉኛል መአት ሰዎች እየተፈራረቁ። በትግርኛ ነው የሚጠይቁኝ። በግምት ነው የምመለሰው። ከንጋቱ 11.45 ላይ አስመራ አውቶብስ ተራ ላይ ያረጀ ኮሰተር አውቶብስ ውስጥ ብቻዬን ተቀምጬ ሲያገኙኝ ሌላ ምን ሊጠይቁኝ ይችላሉ? ከአዲስ አበባ አውቶቢስ ተራ ጋር ሲነፃፀር በውክቢያም በስፋትምማንበብ ይቀጥሉ…
ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና የምፅዋ ወግ (ክፍል ሶስት)
አስመራ – ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ አዲስ አበባ እና አስመራ በብዙ ነገር የተለያዩ ከተሞች ይሁኑ እንጂ በተለይ የድሮዋን አዲስን ለሚያውቅ ሰው የአስመራን መልክ መገመት የሚከብድ አይመስለኝም። እስቲ ድፍን ፒያሳን አስቡ። ብሄራዊ ቲያትር አካባቢን፣ አምባሳደር፣ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢን ጨምሩ። ሜክሲኮ የድሮውንማንበብ ይቀጥሉ…
ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና ምፅዋ ወግ (ክፍል ሁለት)
አስመራ- ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ ለስድስት ቀን ቆይታዬ በፊልሞን አማካኝነት ወደተያዘልኝ አምባሳደር ሆቴል ገባሁ። የእንግዳ መቀበያውና በኋላ ያየሁት በስተግራ ያለው ሻይ ቤት ነገረ ስራው ሁሉ የፒያሳውን ቶሞካ አስታወሰኝ። ሞቅ ባለ ሁኔታ የተቀበለኝ አስተናባሪ ሻንጣዬን ይዞ ክፍሌን የሚያሳየኝ ጎልማሳ መድቦልኝ አሳንሰሩማንበብ ይቀጥሉ…
ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና ምፅዋ ወግ
አስመራ- ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ ‹‹እናት ብዙ ሻንጣ የለሽም አይደል? እባክሽ ይህቺን ስኳር ያዢልኝ? የእኔ እህት….ኪሎ በዝቶብን ነው…ይህችን ቡና ትይዥልኛለሽ?….እመቤት… ያንቺ አልሞላም አይደል…እባክሽ እነዚህን ጫማዎች ያዢልን…›› እያሉ ብዙ ሰዎች ያዋክቡኛል። ቦሌ አየር ማረፊያ አስመራ የሚወስደኝን አውሮፕላን ለመሳፈር ሻንጣ ማስረከቢያው ጋርማንበብ ይቀጥሉ…
የትርፍ ጊዜ ሥራ ( ክፍል ሁለት)
– ቀሚስሽ በጣም ያምራል አለች ገነት ምግብ ቤቱ ውስጥ ገብተን እንደተቀመጥን። – ይሄ? አልኩ በመገረም ቀሚሴን እያየሁ። ተራና ረዘም ያለ ነጭ ቀሚስ ነው የለበስኩት። – አዎ…ቅልል ያለ ነው…ለነገሩ ከመስቀያው ነው…አለች አተኩራ እያየችኝ። (በተሰቀልኩ። እዚሁ እንዳለሁ ተሰቅዬ በሞትኩ!) ፈገግ ብዬ አቀረቀርኩናማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹የትርፍ ጊዜ ስራ››
( የታሪክ መዋቅር እና ሃሳብ- የቼታን ባጋት ‹‹ዋን ኢንዲያን ገርል›› አንዲት ዘለላ ታሪክ) ቅዳሜ ስምንት ሰአት ተኩል። አዲሱን ቤቴን ለማደራጀት የቤት እቃዎች መገዛዛት ከጀመርኩ አንድ አመት ሞላኝ። የቀረኝን የመፅሃፍ መደርደሪያ ለመግዛት በባልደረቦቼ ጥቆማ መሰረት ‹‹ፍሎውለስ ፈርኒቸርስ›› የሚባል ቤት መጥቻለሁ። የሱቁማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ቆንጅዬ›› (ክፍል ሶስት)
አንዳንድ ሴቶች በቁርጥ ስጋ እና ቱርቦ ተደልለው ወደ አልጋ ይሄዳሉ። አንዳንዶች ውድ ሽቶ ሲሰጣቸው ገና ሳይቀቡት ልብሳቸውን ለሰጪያቸው ያወልቃሉ። አንዳንዶች ለቪትዝ የውስጥ ሱሪያቸውን ያስወልቃሉ። አንዳንዶች ጂ ፕላስ ምናምን ቤት ሲያዩ ጭኖቻቸው ይከፈታሉ። አንዳንዶች ላሳቃቸው ወንድ ገላቸውን ይቸራሉ። የእኔ ምስ ግንማንበብ ይቀጥሉ…