‹‹ጨዋታው ፈረሠ…›› (ክፍል ሁለት)

  ይሄ ኑሮ ነው? ከዚህ ኑሮ ለመነጠል የምፈራው ለምንድነው? ይሄን መፈራረስ የጀመረ ጎጆ ፈፅሜ መደርመስ የምሰጋበት ምክንያት ምንድነው? በትዳሬ የደስታ ቅንጣት፣ የእርካታ ፍንጣሪ ሳይኖረኝ፣ ይሄ ምሶሶው የተንጋደደ ቤቴ ቢፈርስ አለም እላዬ ላይ የምትፈርስ የሚመስለኝ ስለምን ነው? ለውሳኔ ምን አውሸለሸለኝ? ሌሊቱንማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ጨዋታው ፈረሠ…›› (ክፍል አንድ)

ሄኖክን ከተዋወቅኩ ጀምሮ ልቤን በደስታ ያዘለለ የፍቅር ጊዜ ትዝ አይለኝም። በሴት ወግ ፍቅሩ ይዞኝ የተጃጃልኩበት፣ ነጋ ጠባ ስለእሱ ያሰብኩበት፣ እንቅልፍ ነስቶኝ የተቸገርኩበት ወቅት ትዝ አይለኝም። ትውውቃችን ተራ እና ቀላል፣ ለሰው ቢነግሩት አፍ የማያስከፍት- አ-ላስደናቂ ነበር። በምኖርበት ህንፃ ላይ ለወራት ክፍትማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ልቤ››

አዲስ ፀባይ ካመጣች ሰነባበተች። ስሙን ለመጥራት ሰበብ መፈለግ እስክታቆም ወዳዋለች። ይሉኝታዋን እንደ ቆሸሸ ልብስ እስክታወልቅ ልቧን ሰጥታዋለች። ፍቅር ይሉኝታ ያስጥል የለ? ምን ይሉኝ ፍርሃትን ይገፍ የለ? እህ…እንደሱ። የጀማመራት ሰሞን ፣ ‹‹በረከት እኮ…ሂ ኢዝ ሶ ስማርት…እኛ ቢሮ የሚቆይ አይመስለኝም…ማስተርሱን ይጨርስ እንጂማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ሚያው››

አብረን ያየን ሰው ሁሉ ‹‹አፈስሽ አፈስሽ›› እያለ ያወራል። ቆንጆ፣ ሎጋ፣ ረጋ ያለ እና ዝምተኛ ነው። የወንድ ልጅ አማላይነት የተሰራው ከእነዚህ ተንኮለኛ ንጥረ ነገሮች አይደል? በፍቅር መውደቅ ከገደል እንደመውደቅ ያማል? በፍቅር መያዝ እንደ ተስቦ ያማቅቃል? አዎ። ቢሆንም እያመመኝ እወደዋለሁ። እየማቀቅኩ አፈቅረዋለሁ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ዋግህምራ እና ትግራይ – የረጅም ጉዞ አጭር ማስታወሻ

ሰሞኑን ለስራ ወደ ሰቆጣ ተጉዤ ነበር። ‹‹ካልተቀጠቀጠ አይበላም ቋንጣ፣ የዋግሹሞች ሃገር እንዴት ነው ሰቆጣ›› ተብሎ የተዘፈነላት ሰቆጣ ትንሽ ግን ደማቅ ከተማ ነች። ሃሙስ እለት ገብቼ ስውልባት ለቅዳሜ የድጋፍ ሰልፍ ጠብ- እርግፍ ትል ነበር። ሰንደቅ አላማ ታከፋፍል፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ ምስሎች ያሉባቸውንማንበብ ይቀጥሉ…

የአልጋ ላይ ዱካ

ትላንት ማታ ክፉ ነገር ተፈጠረ። መልከ መልካሙ እና ገራገሩ እጮኛዬ ላይ ማገጥኩበት። ያች በልጣጣ ጓደኛዬ ትዕግስት ናት እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የከተተችኝ። ሁሌም ለሰኔ ሚካኤል ቤቷ ድል ያለ ድግስ ታዘጋጃለች። የምታውቀውን ሰው ሁሉ ትጋብዛለች። ከልክ በላይ ታበላለች። ከመጠን በላይ ታጠጣለች።ማንበብ ይቀጥሉ…

በህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰጠው መግለጫ ላይ የተሰጠ መግለጫ

ከአንዲ ፈጌሳ በህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰጠው መግለጫ ላይ የተሰጠ መግለጫ ፡ ህወሃት ማምሻውን የሰጠችውን መግለጫ ተከትሎ የተፈጠረውን ግራ መጋባት አስመልክቶ በውስጥ መስመር እየቀረቡ ያሉ የበርካታ(3 ሰዎች) ጠያቂዎችን ሃሳብ በማክበር የሚከተለውን የመግለጫውን ተዛማች ትርጉም ሰጥተናል። ፡ መግለጫውን በአጭሩ “አንፈርስም! አንታደስም!” የሚለውማንበብ ይቀጥሉ…

ስንት ጊዜ ሆናችሁ?

መሃል አዲስአባ…ሸገር ላይ እያላችሁ.. የእንቁራሪቶች ድምፅ በደንብ ከሰማችሁ በክር የታሰረ ጢንዚዛ ካያችሁ የማርያም ፈረስን መንገድ ካገኛችሁ በእፉዬ ገላ ‹‹ያዘኝ አትያዘኝ›› ከተጃጃላችሁ… ስንት ጊዜ ሆናችሁ? ሱዚ የሚዘሉ ፔፕሲ የሚራገጡ ሸክላ እየፈጩ በርበሬ ነው የሚሉ ሙሽራ ሙሽራ – እቃ እቃ እቃ እቃማንበብ ይቀጥሉ…

አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል…

ትላንት ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ምሳ ለመብላት አንዱ ምግብ ቤት ቁጭ ብለናል። ምግቡን እየጠበቅን የተገናኘንበትን ብርቱ ጉዳይ ስንወያይ፣ አራት አለባበሳቸውና ነገረ ስራቸው ሁሉ ሃያዎቹን ከጀመሩ እንዳልቆዩ የሚያሳብቅባቸው ወጣቶች መጡና አጠገባችን ያለውን ጠረጰዛ ከበው ተቀመጡ። በእነሱና በእኛ መሃከል ያለው ርቀት በጣም ቅርብማንበብ ይቀጥሉ…

“የዘር በቆሎ” እና ሌሎች ነጥቦች

ሰሞኑን ኑሮ ተወዱዋል። ትንታኔና ትንቢት ጥንቡን ጥሉዋል። እኔም አይኔን አጥቤ ድርሻየን ልተነትን ነው። ቀልዱን እዚህ ላይ ላቆየውና ውደ ቁምነገሩ። ባጭር ጊዜ እንደ ዶፍ የወረዱት ክስተቶች እንኩዋን ለመተንተን ለመቆጠር እንኩዋ እንደሚያቸግሩ አላጣሁትም። በሁለት ጉዳዮች ላይ ብቻ ባገር ልጅነት የሚታየኝን ለማካፈል እወዳለሁ። አብይማንበብ ይቀጥሉ…