ልቤ ድው ድው። አይኔ ቦግ ቦግ። ጆሮዬ ቆም ቆም። ምላሴ ዝርክርክ አለብኝ፡- ሃብሉን ሲሰጠኝ። ልብ እና ቁልፍ አንድ ላይ ያንጠለጠለ ሃብል ነው። አቤት ማማሩ። አቤት ማብረቅረቁ። ከዚያ ሁሉ ደግሞ አቤት ትርጉሙ! ‹‹የልቤ ብቸኛ ቁልፍ ያለው አንቺ ጋር ብቻ ነው ለማለትማንበብ ይቀጥሉ…
ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት
ጥንታውያን የአብነት ሊቃውንት ‹ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት ነው› ይላሉ። መታመሙን ላወቀ፣ መድኃኒቱን ለፈለገ፣ መድኃኒቱንም በትክክል ለወሰደ፣ ወስዶም ለዳነ ሰው ሕመም ለትምህርት ይሆነዋል። ሦስት ነገር ይማርበታልና። አንድም ዳግመኛ እንዳይዘው ጥንቃቄን፣ አንድም ቢይዘው ሊትርፍ የሚችልበትን መፍትሔን፣ አንድም ደግሞ ለሌላው የሚመክረው ልምድንማንበብ ይቀጥሉ…
መጪው ትውልድ
እሱ ስለ እሷ – እነዳለጌታ ከበደ
የመጀመሪያዋ ግብዣ
ምድርም ሰማይም ባዶ እንደነበሩ ነው ድሮ ! …እና ባዶው ምድር ላይ …እግዚአብሔር ሳር ነሽ ቅጠል ነሽ ውሃ ነሽ ፀሃይ ነሽ እንደጉድ ፈጠረው …. በግ ነሽ ዶሮ ነሽ በሬ ነሽ ዳይኖሰር ነሽ …..ፈጠረ ፈጠረና ከዳር እስከዳር አየት አድርጎ ሲያበቃ ‹‹ፓ መልካምማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለት ስፍራ፣ ሁለት ዓለም!
አስፋልት ዳር ያለች አነስተኛ ዳስ! ሃይለኛ ዝናብ ይዘንባል። ሰማዩ የላስቲክ ቤቷ ውስጥ ያለው መከራ ያነሳት ይመስል፣ ተጨማሪ መከራ ያዘንባል። ውስጥ… አንዲት እናት ተኝተው ያቃስታሉ።ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ የገባው የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ አጠገባቸውቁጭ ብሏል።የደረቀ እንባ አሻራውን ጉንጮቹ ላይ ትቷል። ሴትየዋ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ሚስቴ ፓለቲከኛ ናት
ፓለቲካ አልወድም። የማልወደው፣ ሰዎች የሚያንቀሳቅሱት ሳይሆን ሰዎችን የሚያንቅሳቅሳቸው ስለሆነ ነው። ፓሊዮ እና ዚካ ተቀላቅለው የፈጠረቱ ይመስለኛል። የጠላሁት ቤቴ ገባ። አትግባ እንዳልለው፣ ይዛው የገባችው ባለቤቴ ናት። መች እንደጀመራት ሳላውቅ ፓለቲካ አተኮሳት። ቀጥሎ አነደዳት። ተቃጠለች። እሳቷ እሳቴ ሆነ። ፍቅር ከሰራን በኋላ ሁሉ፣የአደረግነውንማንበብ ይቀጥሉ…
ሌላ ፓለቲከኛ ሚስት አገባሁ
ይቅርታ! ፓለቲከኛ ያልኩት ተሳስቼ ነው። የአሁኗ ሚስቴ ሃይማኖተኛ ናት።ፓለቲካኛ ያልኩት በቀደመው ትዳሬ ተፅዕኖ ነውና ይቅር በሉኝ። የአሁኗ ሚስቴ ጴንጤ ናት። አንድ ሰው ታሞ እያጣጠረ ብታገኝ፣ ራበኝ እያለ አጠገቧ ቢያጣጥር አንድ ጉርሻ በመስጠት ፈንታ«ቆይ አንዴ ልፀልይለት ብላ እጇን በላዩ ላይ» የምትጭንማንበብ ይቀጥሉ…
ለቅምሻ የተቀነጨበ
…..ብዙው ኢትዮጲያዊ የራሱን ነፍስ ኑሯት አያውቅም … ከልጅነት እስከእውቀት ለሌሎች ይኖራል ! ወዶ ሳይሆን ተገዶ !! ሙሉ ደሞዙን ደስ ብሎት ተጠቅሞበት የሚያውቅ ማነው ? …. ለዛ ነው ኢትዮጲያ ውስጥ ኑሮ ‹‹መቀማት ›› የሆነው ……የምትረዳውን ሰው ወደድከውም አልወደድከውም መርዳት ግዴታህም ይሁንማንበብ ይቀጥሉ…
የጦርነት ነገር…
የጦርነት ነገር… (አ.አ) ስሜ ሲያጥር፣ የግለሰብ ሳይሆን የከተማ፣ሊያውም የመዲና ስም እንደሚሆን ካወኩ ሰንብቻለሁ። ይብላኝ እንደ «ብስራት ዳኛቸው» ዐይነት ስም ላላቸው።ምን ብለው ሊያሳጥሩት ነው ሃሃ ይሄ ስም ቢኖረኝ፣ ስሜን ከማሳጥር ቁመቴ ቢያጥር የምመርጥ ይመስለኛል ☺ ድህነትን በቀኝ፣ ፀረ ሰላም ሃይሎችን በግራማንበብ ይቀጥሉ…