“ባቦ፤ በማርያም…”

አመት በአል ሲቃረብ ብዙ ነገር ይናፍቀኛል። ከሁሉም በላይ፤ እንደ አፍላ ጉም የሚሳብ የሉባንጃ እጣን – ብረት ምጣድ ላይ የሚጤስ ቡና -የጥላሁን ገሠሠ ዘፈን -ብዙ ፍቅር- ብዙ ፈገግታ ውልውል ይለኛል። ከመከረኛ ህይወታችን ማህል ብልጭ ብሎ የሚጠፋ አመት በአል የተባለ አብሪ ኮከብማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው ቀላውጦ ማስመለስ ( የመጨረሻ ክፍል)

“ታውቃለህ? ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም። ትክክል መሆኑንም እንጃ!” አለችኝ እቤት እንደገባን “ምኑ?” “የሚሰማኝ ስሜት” “ምንድነው የሚሰማሽ?” ከአፏ የሚወጣው ዓረፍተ ነገር ምንም ቢሆን እኔ ጆሮጋ ሲደርስ ‘ላንተ ፍቅር‘ የሚል ቢሆን እየተመኘሁ “በደለኝነት፣ ሀጢያተኝነት፣ ጥፋተኝነት……ከዳተኝነት… ክምር ወቀሳ!” ጭንቅላቷን ይዛ ጫማዋን እያንቋቋች ተረማመደች።ማንበብ ይቀጥሉ…

አል-ዑመሪ እና ሪቻርድ ፓንክረስት

በ1330ዎቹ ነበር። በዘመኑ የምሥራቅ አፍሪቃ ታላላቅ መንግሥታት በነበሩት የኢትዮጵያ ሰለሞናዊ አፄዎች እና የኢፋት ወላስማ ሱልጣኖች መካከል ታላቅ ጦርነት ይካሄድ ነበር። በጦርነቱ ከተሸነፉት የኢፋት መንግሥት ባለሟሎች መካከል ጥቂቱ ወደ ግብጽ ሸሹ። እዚያም ለግብጹ ሱልጣን የደረሰባቸውን ሽንፈት ሲያወሱ አንድ ጸሐፊ ያስተውላቸዋል። ይህማንበብ ይቀጥሉ…

ሕይወት- ሌስተርና ቼልሲ

ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም። አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል። አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል። ለሚወጣ ሰው ግን መውረድማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው (ክፍል ሰባት)

በጀርባዬ ተኝቼ አላውቅም። በደረቴ ካልተኛሁ እንቅልፍ አይወስደኝም። … ዛሬ እንቅልፍ ስለመተኛት አይደለም ግዴ…… አይኔን ብከድን ስነቃ አጠገቤ የማጣት ነው የመሰለኝ ፒጃማ ለብሼ ተኝቼ አላውቅም። ይጨንቀኛል። ዛሬ እሷ ምቾት እንድታጣ አልፈለግኩም። …… እቤቴ ማንም ሴት መጥታ አታውቅም። ዛሬ ስምሪትን አቅፊያት ለወትሮዬማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው (ክፍል ስድስት)

ስምሪት ያስደነገጣት የኔ መምጣት ይሆን ወይም የመጣሁበት ሰዓት አላውቅም። …… ደነገጠች። “እንዴ? ኪሩቤል?” ተንተባተበች። …… ጨበጠችኝ። ሰውየው ለኔ ማሳወቅ የፈለገው ነገር ያለ መሰለኝ አቅፎ ወደ ራሱ አስጠግቶ ፀጉሯን ሳመ። …… እሷ በድርጊቱ ያፈረች መሰለኝ። አይኔን ሸሸችው። ” ማሬ የስራ ባልደረባዬማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው (ክፍል አምስት)

“ልክ አይሆንም። እኔና አንተ ከዚህ ቀደም ከነበረን የዘለለ ግንኙነት ሊኖረን አይችልም።” አለችኝ …… “ቅድም ‘ከአዕምሮ ይልቅ ልብ ይማርከኛል‘ አልሺኝ አይደል?” ” እም… ” የምቀጥለውን ለመስማት እየሰገገች “ሲገባኝ ሌላ ፍቺው ከስሌት ይልቅ ለስሜት ቅርብ ነኝ ማለትሽ መሰለኝ። …… ልክና ስህተቱን በስሌትማንበብ ይቀጥሉ…

ልጄ -ባዶ ወረቀቴ

ማን ማን ውስጥ እንደገባ፣ የቱ ገላ የማን እንደሆነ መለየት እስኪያስቸግረን ድረስ ተቆላልፈን ከመዋሰብ ያለፈ ነገር አላውቅም ነበር። የወጣትነት ትኩሳትን ከማዳፈን፣ የቆመን ከማጠውለግ፣ ከግብት- ውጥት እና ግብት- ትፍት ጨዋታ በላይ ደስታ ይሰጠኝ የነበረ ነገር አላስታውስም። ….እንዲህ እንዲህ በየአልጋው ስንወድቅ እና ስንነሳማንበብ ይቀጥሉ…

የዝምድና ታሪክ

በታሪካችን የብሔረሰብ ማንነት በተዋልዶ ብቻ ሳይሆን በተለምዶም የሚገኝ ነበር። በቅርብ ርቀት ከማውቀው ከጎጃምና ከወለጋ ታሪክ ምሳሌ ላምጣ። አንድ ኦሮሞ ከወለጋ በዘመቻ በንግድ ወይም በምርኮ አባይን ተሻግሮ ወደ ጎጃም ይዘልቅና በዛው ቀልጦ ይቀራል እንበል። ክርስትና ተነሥቶ የጥምቀት ስም ይዞ ዳዊት እየደገመማንበብ ይቀጥሉ…

ሠርገኛ መጥቶም በርበሬ ቀንጣሽ ጠፋ

ስንቱ መከረኛ ወገኔ ዛሬም ፤ ‹‹አዬ ክፉ ዘመን ይቅር አይነሳ፣ አርጉዝ ላሜን ሸጥኳት- ለሁለት ቀን ምሳ›› እያለ አጣዳፊ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ሲገልፅ፤ ‹‹ድርቁን ረሃብ ከመሆኑ በፊት ተቆጣጥረነዋል!›› ‹‹የውጪ እርዳታ አንፈልግም!›› ሲባል ተከርሞ፤ በዚህ ሳምንት ከወራት በፊት በጓሮ በር ቤተመንግስት ይመላለሱማንበብ ይቀጥሉ…