ላለፉት ጥቂት ቀናት ያገኘኋቸውን ወንዶች በሙሉ አንድ ጥያቄ ስጠይቅ ነበር፡፡ ‹‹የቤት እመቤት ምን ማለት ነው?›› ከአንድ ወይም ሁለት መልሶች ውጪ የተሰጡኝ ፍቺዎች በሚከተሉት ሀረጎች ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ‹‹የማትሰራ ሴት›› ‹‹ስራ የሌላት ሴት›› ‹‹ገቢ የሌላት ሴት›› ‹‹ስራ አጥ ሴት›› ‹‹ስራ ፈት ሴት››ማንበብ ይቀጥሉ…
ሥልጣኔ የኋልዮሽ
ቀደም ባለው ዘመን ደመቅ ብለው የጠቆሩ የዳር አገር ብሄረሰቦችን በባርነት መፈንገል የተለመደ ነበር። ብዙዎቹ የኦሮሞ የአማራና የትግራይ ጌቶች እልል ያሉ የባርያ ፈንጋይና አሳዳሪ ነበሩ።ተፈንጋዮቹን ለፍንገላ ያጋለጣቸው ከነሠንሠለታቸው ስለተወለዱ አልነበረም። ማስገበር ደንብ በነበረበት በዚያ ዘመን ራሳቸውን የሚመክቱበት ነፍጥ ወይም አደረጃጃት ስላልነበራቸውማንበብ ይቀጥሉ…
ያድዋ ስንኞች
የቅዱስ ቫላንታይንን በአል ምክንያት በማድረግ ስለ አድዋ ጦርነት እንጽፋለን፡፡ የቀድሞ ሰዎች የቃልና የዜማን ኃይል አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ሁሌም ወደ ጦርሜዳ ከመሄዳቸው በፊት አዝማሪ እና አረሆ ይመለምላሉ፡፡ ባድዋ ጦርነት ብዙ አዝማሪዎች ማሲንቆ ታጥቀው ዘምተዋል፡፡ አንዳንዶች ለውለታቸው ከድል በኋላ ማእረግና መታሰቢያ ተበርክቶላቸዋል፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
የፍቅረኞች ቀን
የፍቅረኞች ቀንን የማልወደው ፍቅርን ስለማልወድ አይደለም፡፡ ፍቅርን የሚዘክር ቀንን ስለምጠላም አይደለም፡፡ የፍቅረኞች ቀንን የማልወደው ከፍቅረኞች ቀን ይልቅ የጥቅመኞች ቀን እየሆነ ስለመጣ ነው፡፡ ‹‹ከወደድከኝ የፍቅረኞች ቀን እለት ግሎባል ሆቴል ውሰደኝ›› የሚል ማስታወቂያ በየቦታው ተለጥፎ ሳይ፣ ‹‹እኔ ዘንድሮ እንደአምናው በቸኮሌት አልሸወድልህም…ዘንድሮ የምፈልገው የኢቴልኮንማንበብ ይቀጥሉ…
የእቴጌ እና የሂትለር ፎቶ
ባየኋቸው ቁጥር ግርርም ከሚሉኝ ታሪካዊ ፎቶዎች አንዱን ላካፍልዎት፡፡ በ1935 የተነሣው ይህ ፎቶው የተገኘው ባሶሼትድ ፕሬስ መዝገብ ውስጥ ነው፡፡ በፎቶው ላይ ለጊዜው ስሙን ያልደረስኩበት ሠዓሊ የግርማዊት እቴጌ መነን እና የአዶልፍ ሂትለርን ሥዕል ሲሸጥ ይታያል፡፡ በፎቶው ጀርባ ላይ እንደ ተገለጸው ከሆነ፤የጀርመኑ አምባገነንማንበብ ይቀጥሉ…
ባለ መሰንቆውና ባለ ወለሎው
“ሮድ ደሴት” በተባለ አገር ውስጥ እንደ እንደምኖር የነገርኩት ጓደኛየ “እና ባሣ አጥማጅነት ነው የምትተዳደረው?” ብሎኛል፡፡ ሮድ ደሴት አበሻ እጥረት ክፉኛ ከሚያጠቃቸው ክልሎች አንዱ ነው ፡፡ አሁን ምድሩም ሰማዩም ሰውም ነጭ ነው፡፡ ያገር ሰው በጣም ይናፍቀኛል፡፡ የሆነ ያበሻ ዓይነ ውሃ ያለው አልፎማንበብ ይቀጥሉ…
“አልወለድም!” (ክፍል ሁለት)
እየተደናበረች በመሮጥ ላይ ሳለች እንቅፋት መትቷት በሙሉ ሰውነቷ ው-ድ-ቅ ስትል ሁለቱም ተናወጡ፡፡ ዘፈንኑን በድንገት አቆመ፡፡ ‹‹ራበኝ!›› አለች በእንቅፋት የተነደለ አውራጣት ጥፍሯን እያሻሸች፡፡ መድማት ጀምሯል፡፡ ‹‹እኔም ርቦኛል…እማ›› ብሎ መለሰላት፡፡ ዝም ብላ ቁስሏን እና ረሃብዋን ስታስታምም ትንሽ ጊዜ ጠበቀና፤ ‹‹እማ…ደሃ በመሆንሽ ታሳዝኚሻለሽ…ነገር ግን ለኔማንበብ ይቀጥሉ…
“አልወለድም!” (ክፍል አንድ)
‹‹አልወለድም!›› የደራሲ አቤ ጉበኛ እጅግ ታዋቂ ስራ ነው፡፡ የሚከተለው ድርሰት በአመዛኙ በአቤ ጉበኛ አልወለድም መፅሃፍ ጭብጥ፣ ገፀባህርያትና ምልልልሶች ላይ በደንብ ተመስርቼ የፃፍኩት የአልወለድም ዘመነኛ እና አዲስ ገፅ ነው፡፡ የትረካው አቅጣጫ፣ የገፀባህሪዎቹ ገለፃ እና ምልልሶች ግን በአመዛኙ ተለውጠዋል፡፡ ‹…ግን ከተመረጡ ሃብታሞችማንበብ ይቀጥሉ…
የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ
አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ በዘፈን አንደኛ ሙሉቀን መለሰ (እስከመቸ ድረስ ጥላሁን ገሰሰ) የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ? Lol የህዳሴውን ግድብ ወደ “ህዳሴው ገደል” ያሸጋገረውን ስምምነት የፈረመው ሰውየ“ እጁን ለቁርጥማት፤ ደረቱን ለውጋት“ እንዲዳርገው በመመረቅ ወደ ሰላምታየ እገባለሁ፡፡ እንዴት ናችሁ፤ ያልታደላችሁ? እኔ በህይወቴማንበብ ይቀጥሉ…
በአልጋው ትክክል (ክፍል 22 )
ውሃ በተሞላ ብርጭቆ ውስጥ ማንም ውሃ መጨመር አይችልም ….ፍቅር የተሞላ ልብም ማንንም ማፍቀር አይችልም … ሁለት ሰዎች ከተፋቀሩ ብቸኛው ምክንያት ሁለቱም ልብ ውስጥ ያለው ክፍተት ነው ሊሆን የሚችለው ! ልእልት እኔ እንዳፈቀርኳት ካፈቀረችኝ ሲጀመር የፍቅር ፅዋዋ ጎደሎ ነበር ማለት ነውማንበብ ይቀጥሉ…