ድል ምርኮና ምህረት

በአጼ ዮሀንስ አራተኛ ዘመነ መንግስት የጎጃሙ ንጉስ ተክለሀይማኖት እና የሸዋው ንጉስ ምኒልክ በመሬትና በንብረት ተጣልተው ሰራዊት አስከትተው እምባቦ በሚባለው ስፍራ ተገናኝተው ተሸካሸኩ፤ በጦርነቱ ምኒልክ እና አጋሮቻቸው በለስ ቀናቸው፤ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብዙ ቦታ ቆስለው ተማረኩ፤ ምኒልክ በጦርነቱ ማግስት የግል ሀኪማቸውን በማዘዝማንበብ ይቀጥሉ…

ከሞተላት በላይ የወደዳት ማነው?

ትንሽ ልጅ ሳለሁ… ይህች …ከልጅነት እስከ ጉልምስና የትም፣ መቼም ሳያት እምባ በአይኔ የምትሞላውን ሰንደቅ ዓላማ ትምህርት ቤት በተጠንቀቅ ቆሜ ሳሰቅል፣ ሳላሳልስ ‹‹ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ ቅደሚ…አብቢ ለምልሚ›› እያልኩ በስሜት ሳዜም… ‹‹ይህች ሰንደቅ ዓላማ ተከፍሎባታል›› እያሉ ሲነግሩኝ፣ ‹‹ባንዲራችን ብዙ ታሪክ አላት›› እያሉ ሲያስተምሩኝ…. ‹‹ወድቆማንበብ ይቀጥሉ…

መጠናናት

አንድ በድሜና በምጣኔ ሀብት የሚበልጠኝ ወዳጅ ነበረኝ ፤ አንዳንዴ በግድግዳ ስልክ ደውየ “ ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልግህ እንገናኝ” ስለው ” ጋብዘኝ፥ ሊፍት ስጠኝ፥ ገንዘብ አበድረኝ፥ ዋስ ሁነኝ፥ ሽማግሌ ሆነኝ አትበለኝ እንጂ ለጥብቅም ሆነ ለላላ ጉዳይ ልታገኘኝ ትችላለህ ” ብሎ ይመልስልኝ ነበርማንበብ ይቀጥሉ…

መጠያየቅ

በቀደም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ አንድ ለየት ያለ ፕሮግራም አየሁ፤ ሁለት አርቲስቶች መድረክ ላይ ይቀርቡና ርስበርስ ቃለ መጠይቅ ይደራረጋሉ፤ ይካካባሉ ፤ ይሸነጋገላሉ ማለት ይሻላል። ቃለ መጠይቁ በገሀዱ አለም ያለውን እውነታ አያንጸባርቅም! በገሀዱ አለም፤ አርቲስት አርቲስትን ይቦጭቃል፤ አርቲስት ባርቲስት ላይ ይሸምቃል፤ አርቲስትማንበብ ይቀጥሉ…

( ግብዣው ፤ ቅጽ 2)

ጓደኛየ ዘፈን መስራት ካቆመ አስር አመታት ያለፈው ድምጻዊ ነው። ዋና ስሙ ፋኑኤል ሲሆን ለደህንነቱ ሲባል ” ዘነመ” እያልሁ እጠራዋለሁ፤ ከቀናት ባንዱ ሰንበት “ወለላ “ ምግብ ቤት በረንዳ ተቀምጠን አስተናጋጅ እንጠብቃለን፤ አንዲት እንዲያው በደፈናው የአፈወርቅ ተክሌን ስእል የመሰለች ሴት ከፊታችን ብቅማንበብ ይቀጥሉ…

ለከፋ ችግር የማይዳርግ ለከፋ

ከጥቂት አመታት በፊት” የምነው ሸዋ “ ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና፥ ለእህቱ ልደት፥ ዲሲ በሚገኝ ክለብ ውስጥ የእራት ግብዣ አዘጋጀ፤ በእሱ መጥርያ ወደ አሜሪካ የመጡ ዘፋኞች አንደኛው ጥግ ላይ ተከማችተው ተቀምጠዋል ፤ ፋሲል ደሞዝ ፥ አጫሉ ሁንዴሳ ፥ ሃይሉ ፈረጃ ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ስለአወዳመት

አሜሪካን አገር፥ አበሻና ላቲኖ የሚበዛበት ሰፈር ውስጥ ቤት ስከራይ ለደላላው እማቀርበው የመጀመርያው ጥያቄ “ ሽንት ቤቱ የብቻ ነው የጋራ ?” ሚል ነው። ወድጄ አይደለም፤ ደባል አበሻ ነህ እንበል! ዶሮ ወጥ ትወዳለህ! አሜሪካን አገር ያለው “ችክን” ደግሞ ችክ ያለ ነው ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ጎባጣው ትዳሬ

በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ መርህ አለኝ ፤ ያገርቤትም ሆነ የውጭ አገር ፖለቲካ ዜና እጦማለሁ፤ ኪነጥበብና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እጣድና ነፍሴን አለመልማታለሁ፤ በዚህ መሰረት ፥ ቅድም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ ቆየሁ። በቀደም አንድ የሞሮኮ ዜጋ የሆነ ዘፋኝ “ ሊጋባው በየነ” የሚለውን ዘፈን በራሱማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ኢምፔርያሊዝም፥ አልልም ዝም

(በእውቀቱ ስዩም ፤ የውስጥ አርበኛ) ያንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ Bully የሚያደርገኝ ልጅ ነበር ፤ ስሙ ራሱ ሙሉጌታ ቡሊ መሰለኝ ካልተሳሳትኩ ፤ እና አንድ ቀን ሄጄ ኮሌታውን ጨምድጄ ያዝኩት፤ እሱም እጁን ወደ አንገቴ በመስደድ አጻፋውን ለመመለስ ኮሌታየን ይፈልግ ጀመር ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

[ዛሬ ቀን 11/12/13]

ዛሬ ቀኑ 11 ወሩ 12 ዘመኑ ሁለት ሺ 13 (11/12/13) ነው። በዘመን ቀመር ቀን፣ ወር፣ ዓመት በአጻጻፍ 11/12/13 ሲደረደር ለዘመን ቀመር ተመራማሪ እጅግ ያስደስታል። ዛሬ በ11/12/13 ከጓደኞቼ መካከል ልደታቸውን የሚያከብሩ ነበሩና 11/12/13 ብለው ጽፈው በመመልከቴ ለእነርሱ የመልካም ልደት መታሰቢያ እንዲሆንማንበብ ይቀጥሉ…