እዚህ ኮንዶሞኒየማችን አራተኛ ፎቅ ላይ አንዲት ቆንጆ ልጅ አለች….ቁንጅናን ሳይሰስት የሰጣት እሷም ሳትሰስት ውበቷንና ሽቶዋን ለብሎኩ ነዋሪዎች በቸርነት የምታሳይ ቆንጆ ! እውነቴን ነው …አንዴ ስታልፍ ከአንደኛ ፎቅ እስከአራተኛ ፎቅ ደረጃው ሁሉ የሷን ውድ ሽቶ ይታጠንና ባለአራት ፎቅ ገነት ይመስላል ….በአካልማንበብ ይቀጥሉ…
የየመኒዎች ጨዋታ
በዚህ ወቅት የቅርብ ጓደኛዬ የመኒው ኮሎኔል ሙሐመድ አል ሐይደሪ ነው። ረመዳንን በአብዛኛው አንድ ቤት ነበር ያሳለፍነው። አሁንም አብረን ነው የምንውለው። በተለይ ከሰዓት አብረን ስንጫወት ነው የምናሳልፈው። በርካታ ቁም ነገሮችንም ከእርሱ እየተማርኩ ነው። —- ጦርነትን ሸሽቶ ከሀገሩ የወጣው ሙሐመድ አል ሐይደሪማንበብ ይቀጥሉ…
ሲጨልም
አድናቆት እና ሞት
ላልጀመርከው ስኬት —የማይቆም ጭብጨባ ማያቋርጥ ፉጨት እያደር ሚገልህ — ቀን ያጣፈጠውን መርዝ እንደመጎንጨት እንደ ሱፍ አበባ ጭለማን ተኳርፎ ፀሀይ ከሚመስል መብራት ስር መሰጣት ለምትወደው ስትል ሚያፈቅሩህን ማጣት አንዳንዴ ጥሩ በጣም ጥሩ እጅግ በጣም ጥሩ እንደ ፃ‘ፊው ሳይሆን እንደ አነባበብ ነው ሚገለጥ ሚስጥሩ ወደ ላይማንበብ ይቀጥሉ…
በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር
“በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር፤ በዘመን ሂደት የችግር ካንሠር ይሆናል።” ለአንዲት ሐገር ዘመንን የሚዋጅ፣ ትውልድን አንደአዲስ የሚቀርፅ ጥበብ ያስፈልጋታል። ሐገርን ወደኋላ የሚጎትት የማይጠቅም አስተሳሰብ በአዲስና በተሻለ አስተሳሰብ መለወጥ ከዜጎች የሚጠበቅ ተግባር ነው። ያረጀውን ማደስ፣ የሌለውን ጥበብ መፍጠር፣ ያልነበረውን መልካም ተሞክሮ መቅሰምማንበብ ይቀጥሉ…
የመብራት የመጥፋት ትዝታ፤ከባለፈው የቀጠለ
ከጥቂት አመት በፊት የረር በር እኖር ነበር፤አንድ ቀን መብራት በጊዜ ጠፋ፤እስከ እኩሌሊት ድረስ ስላልመጣ ተስፋቆርጠን ተኛን፤ ዘጠኝ ሰአት ላይ ሚስቴ ቀሰቀሰችኝና ወደ ምኝታቤቱ መስኮት ጠቆመችኝ፤ የሆነ ግዙፍ እጅ ጥላ መስኮቱን ሲዳብስ ይታየኛል፤ “ሌባ ነው?” አልኩዋት፤ ራሱዋን ባዎንታ ወዘወዘች፤ “መስኮቱን ምንማንበብ ይቀጥሉ…
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የተቀሰቀሰ ትዝታ
ወደዚች ምድር ስመጣ ማንኩሳ በጭላጭ ኩራዝ ተቀበለችኝ፤ ኩራዙ ያራት ነገሮች ጥምረት ነው፤ የኮኮስ ቅባት ጠርሙስ፤ በምስማር ተበሳ ቆርኪ፤ የዝሃ ክር እና ላምባ። በጊዜው የኩራዝ ማብሪያ መቅረዝ አይታወቅም፤ ከያንዳንዱ ጎጆ የውስጥ ግድግዳ ማእዘን ላይ በጭቃ የተሰራ የኩራዝ ማስቀመጫ ይኖራል፤ስሙ ባማርኛ መዝገበቃላትማንበብ ይቀጥሉ…
ትንንሽ ቅመሞች
ቅዳሜ ቅዳሜ ማታ በዙረቴ የማልደርስበት የከተማችን ክፍል የለም። ሳምንት ወይ አስራ አምስት ቀን በሙሉ ከቤት ሳልወጣ እቆይና፣ እመሽግና አንድ ቅዳሜ መርጬ ከወጣሁ ግን የምመለሰው ተበለሻሽቼ ነው። በደንቤ ሳምንት፣ ሁለት ሳምንት ሙሉ ከቤት አልወጣም…… ከእሁድ እስከ ዓርብ። ብዙ ጊዜ ቅዳሜ ግንማንበብ ይቀጥሉ…
ጥቂት ቁንጣሪ ሃሳብ ከ “Born a Crime” መፅሐፍ!
የዚህ መፅሐፍ ፀሐፊ ትሬቨር ኖህ (Trevor Noah) በሙያው አዘጋጅ፣ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ተዋንያን እና ኮሜዲ ነው። ይሄ ፀሐፊ የኮሜዲ ስራውን ማቅረብ የጀመረው በሐገሩ በደቡብ አፍሪካ ነበር። ይሄንንም ስራውን በመቀጠል አሁን በሚገኝባት አሜሪካም በተፅዕኖ ፈጣሪነት በሚታወቀው ፕሮግራም ላይ ምፀታዊ ዜናዎችን የሚያቀርብ (Theማንበብ ይቀጥሉ…
መርፌ
አብዬ መንግስቱ ለማ እጅግ ሲበዛ አስተዋይ ነበሩ። አማሪካን ሀገር ሄደው ተምረው ሲመለሱ ከሀሳብ ሁሉ ገዝፎ ሀሳብ የሆነባቸው ከአንድ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ጋር ድንገት ቢገናኙ ሊጠይቃቸው የሚችለው ጥያቄ ነበር። ውጪ ተምረው እንደመጡ ሲያወሩ ድንገት የሰማ ገበሬ ጠጋ ብሎ “መርፌ ትሠራለህ? ” ብሎማንበብ ይቀጥሉ…