«ወንድ ልጅ አይደለህ እንዴ? እንዴት ፖለቲካ አትወድም?» ብላኝ አረፈችው። እሰይ! «እዚህ ሀገር ከፖለቲካ ጋር ያልተነካካ ብቸኛ ገለልተኛ አካል የኔ አክሱም ነው። ተያ!…… የፓርላማ ጭብጨባ ካልሰማሁ አልቆምም ብሎ አያውቅም። አያደርገውም! እዝህች ሀገር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በረደ ብሎ ለግሞብኝም አያውቅም። ሽለላ ቀረርቶማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹የድሬ ሰው ነፍሴ››
የሚያንገረግበውን የድሬ ሙቀት መብረድ ጠብቄ አመሻሹን ሻይ ልጠጣና በእግሬ ወዲህ ወዲያ ልል ከሆቴሌ ወጣሁ። ለብ ባለው ንፋስ እየተደሰትኩ፣ ቱር ቱር በሚሉት ባጃጆች ካለጊዘዬ ላለመቀጨት እየተጠነቀቅኩ ከተዘዋወርኩ በኋላ ለሻይ አንዲት ትንሽ ቤት ቁጭ አልኩና ምን ይምጣልሽ ስባል ‹‹ቀጭን ሻይ›› ብዬማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹እታባዬ…እታባዬ!››
ባለፈው ሰሞን አንድ ቀብር ሄጄ ነው። ሟች፣ እታባ ጠና ያሉ ሴት ነበሩ። የእኛ ሰው ቀጠሮ የሚያከብረው ቀብር ሲሆን ብቻ አይደል? ምን ማክበር ብቻ? ቀድሞ ይጀምራል እንጂ! ያጣድፈዋል..ያዋክበዋል እንጂ! ስለዚህ ለስድስት ሰአት ቀብር መንገድ ተዘጋግቶብኝ እንዳላረፍድ ሰግቼ ከአምስት ሰአት በፊት ከቢሮማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹በሃገር ነው››
ጎረቤቴ ካለው ቤተክርስትያን የሚመጣው የቅዳሴ ዜማ እና የወፎች ዝማሬ አነቃኝ። እንዴት ውብ አነቃቅ ነው! በሰላም አሳድሮ ይሄንን አዲስ ቀን ስላሳየኝ ምንኛ የታደልኩ ነኝ? ዛሬን ከማያዩት ስላልደባለቀኝ ምንኛ አድለኛ ነኝ? አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ተንጠራራሁ። ሌላ ጊዜ ቅዳሜ እንደማደርገው አልጋ ውስጥ ስንደባለልማንበብ ይቀጥሉ…
የምንችለውን ወይስ የሚገባንን?
የሚቻለውን መሥራት የዐቅም ጉዳይ ነው። የሚገባውን መሥራት ግን የሕግና የሞራል ጉዳይ ነው። ኃይልን ለመጠቀም የሚያስችል ትምህርት ለሚማሩ ሰዎች በጥብቅ የሚነገራቸው ነገር ቢኖር የተገቢነት ጉዳይ ነው። ካራቴ፣ ጂዶ፣ ቦክስ፣ ውትድርና፣ ፖሊስነት የተማሩ ሰዎች ኃይልን ለመጠቀም ቅርብ ናቸው። በእጃቸው ማጠናፈር፣ በእግራቸው መዘረር፣ማንበብ ይቀጥሉ…
የማርች 8 የስልክ ጥሪዎች…
ማርች 8 መጣሁ መጣሁ ሲል ፤ መቶ እና ከመቶ ሰው በላይ የሚያውቃቸው ሴቶች ስልክ በጥሪ የሚጨናነቅበት ወቅት ነው። እኔም እዚህ ፌስቡክ ላይ መቶ ምናምን ሰው ያውቀኝ የለ? አንድ እሽግ ስሜንም እኔንም የማያውቁ ሰዎች የሚያውቁኝ ሰዎች ፈቃዴን እንኳን ሳይጠይቁ ቁጥሬን ስለሰጡዋቸውማንበብ ይቀጥሉ…
ስለፍቅር በስምአብ ይቅር!!
በዙረት ካገኘሗቸው እውቀቶች አንዱን በማካፈል ወጌን ልጀምር። ያፍሪካ ስደተኞች ያንዱን ያውሮፓ አገር ድንበር አቋርጠው ይገቡና አንድ ከተማ ውስጥ አድፍጠው ይቀመጣሉ። በከተማው ባንድ ስፍራ ላይ መንግስት ገንብቶ ያልጨረሰው ባዶ ህንፃ ይኖራል። ስደተኞች ከለታት አንድ ቀን ተደራጅተው ህንፃውን ወርረው ይይዙታል። የህንፃውን አፓርታማማንበብ ይቀጥሉ…
ሰው በሰውነቱ
የምግብ ቤት ባለቤት የሆነ ሰውየ :በደንበኞቹ መሀል ሲዘዋወር አንድ ዝነኛ ጋዜጠኛ ይመለከታል። ወድያው ባለቤትየው አስተናጋጂቱን ጠርቶ ” እዛ ጥግ ላይ የተቀመጠው ጋዜጠኛ ይታይሻል? ሂጅና የሚፈልገውን እየጠየቅሽ ተንከባከቢው!! ወጥ ካነሰው ጨምሪለት!! እንዲያውም ለኔ ራት ከተሰራው ዶሮ አንድ ቅልጥም ብትሰጪው ደስ ይለኛል።ማንበብ ይቀጥሉ…
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ
የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ ልቤን ክንዴን እያዛለ ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ። እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ። አሰታወሰኝ አስታወሰኝ። ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ ያለም ዘፋኝ የማያውቀውማንበብ ይቀጥሉ…
ጉደኛ ስንኞች
እንዳለመታደል ሁኖ የጎጃሙ ጌታ የራስ አዳል ልጆች አሪፍ ያገር አስተዳዳሪ አልነበሩም። እንደመታደል ሆኖ ደሞ የተዋጣላቸው ባለቅኔዎች ነበሩ። ግጥሞቻቸው ከኑሯችን ጋር በጣም የተቆራኙ ናቸው። ለምሳሌ የግፍ ዘገባ በሰማን ቁጥር የምንቀባበለው። “የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል” የሚለውን ገራሚ ግጥምማንበብ ይቀጥሉ…