ትላንት ዘ ጋርዲያን ላይ ከወጣ የከረመ አንድ ፅሁፍ ሳነብ ሁሌም የሚያስቀኝ፣ የሚያሳዝነኝ እና የሚያስገርመኝ ነገር ስለሆነ እሱን ተመርኩዤ በዚህ ጉዳይ ለምን አላወራም ብዬ አሰብኩ። ጌሪ ኦውን የጻፈው የጋርዲያኑ ፅሁፍ ርእስ 10 tricks to appear intelligent during development meetings ይሰኛል።ማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ጨዋታው ፈረሠ…›› (ክፍል ሁለት)
ይሄ ኑሮ ነው? ከዚህ ኑሮ ለመነጠል የምፈራው ለምንድነው? ይሄን መፈራረስ የጀመረ ጎጆ ፈፅሜ መደርመስ የምሰጋበት ምክንያት ምንድነው? በትዳሬ የደስታ ቅንጣት፣ የእርካታ ፍንጣሪ ሳይኖረኝ፣ ይሄ ምሶሶው የተንጋደደ ቤቴ ቢፈርስ አለም እላዬ ላይ የምትፈርስ የሚመስለኝ ስለምን ነው? ለውሳኔ ምን አውሸለሸለኝ? ሌሊቱንማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ጨዋታው ፈረሠ…›› (ክፍል አንድ)
ሄኖክን ከተዋወቅኩ ጀምሮ ልቤን በደስታ ያዘለለ የፍቅር ጊዜ ትዝ አይለኝም። በሴት ወግ ፍቅሩ ይዞኝ የተጃጃልኩበት፣ ነጋ ጠባ ስለእሱ ያሰብኩበት፣ እንቅልፍ ነስቶኝ የተቸገርኩበት ወቅት ትዝ አይለኝም። ትውውቃችን ተራ እና ቀላል፣ ለሰው ቢነግሩት አፍ የማያስከፍት- አ-ላስደናቂ ነበር። በምኖርበት ህንፃ ላይ ለወራት ክፍትማንበብ ይቀጥሉ…
ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል እብሪት ግን ለውድቀት ይዳርጋል
ጎሽ! ጎሽ! እሰይ —- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን በየእለቱ እየወደድኩት ነው። ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ያለኝ አድናቆትም እየናረብኝ ነው። ታዲያ አቶ ኢሳያስ ዛሬ ያደረገውን አስገራሚ ነገር ልብ ብላችኋልን? ፊርማውን ሲፈርም እኮ የባድመ ጉዳይ ከቁም ነገር ተቆጥሮ አልተነሳም። ድሮስ? ድሮማ “ባድመን ካላስረከባችሁን ድርድርማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ልቤ››
አዲስ ፀባይ ካመጣች ሰነባበተች። ስሙን ለመጥራት ሰበብ መፈለግ እስክታቆም ወዳዋለች። ይሉኝታዋን እንደ ቆሸሸ ልብስ እስክታወልቅ ልቧን ሰጥታዋለች። ፍቅር ይሉኝታ ያስጥል የለ? ምን ይሉኝ ፍርሃትን ይገፍ የለ? እህ…እንደሱ። የጀማመራት ሰሞን ፣ ‹‹በረከት እኮ…ሂ ኢዝ ሶ ስማርት…እኛ ቢሮ የሚቆይ አይመስለኝም…ማስተርሱን ይጨርስ እንጂማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ሚያው››
አብረን ያየን ሰው ሁሉ ‹‹አፈስሽ አፈስሽ›› እያለ ያወራል። ቆንጆ፣ ሎጋ፣ ረጋ ያለ እና ዝምተኛ ነው። የወንድ ልጅ አማላይነት የተሰራው ከእነዚህ ተንኮለኛ ንጥረ ነገሮች አይደል? በፍቅር መውደቅ ከገደል እንደመውደቅ ያማል? በፍቅር መያዝ እንደ ተስቦ ያማቅቃል? አዎ። ቢሆንም እያመመኝ እወደዋለሁ። እየማቀቅኩ አፈቅረዋለሁ።ማንበብ ይቀጥሉ…
ዋግህምራ እና ትግራይ – የረጅም ጉዞ አጭር ማስታወሻ
ሰሞኑን ለስራ ወደ ሰቆጣ ተጉዤ ነበር። ‹‹ካልተቀጠቀጠ አይበላም ቋንጣ፣ የዋግሹሞች ሃገር እንዴት ነው ሰቆጣ›› ተብሎ የተዘፈነላት ሰቆጣ ትንሽ ግን ደማቅ ከተማ ነች። ሃሙስ እለት ገብቼ ስውልባት ለቅዳሜ የድጋፍ ሰልፍ ጠብ- እርግፍ ትል ነበር። ሰንደቅ አላማ ታከፋፍል፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ ምስሎች ያሉባቸውንማንበብ ይቀጥሉ…
አንድነትን ከ “ቦ ም ብ” እንማር!!
እስቲ አንድ ጊዜ ከታች ያለውን ምስል በትኩረት ተመልከቱት ጓዶች ! ቦንብ ነው! ቦንብ ምንድን ነው? ዊክፒዲያ ቦንብ? << በቅጽበት በውስጡ በሚፈጠር ኢነርጅ በዙሪያው ባለው አካባቢ ላይ ጭስ፣ ጨረር፣ ከፍተኛ ሙቀት፣ ተቀጣጣይ ነገር ወይም ተፈነጣጣሪ ጠጣር ነገሮች በመርጭት ውድመት የሚያስከትል የጦርማንበብ ይቀጥሉ…
የአልጋ ላይ ዱካ
ትላንት ማታ ክፉ ነገር ተፈጠረ። መልከ መልካሙ እና ገራገሩ እጮኛዬ ላይ ማገጥኩበት። ያች በልጣጣ ጓደኛዬ ትዕግስት ናት እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የከተተችኝ። ሁሌም ለሰኔ ሚካኤል ቤቷ ድል ያለ ድግስ ታዘጋጃለች። የምታውቀውን ሰው ሁሉ ትጋብዛለች። ከልክ በላይ ታበላለች። ከመጠን በላይ ታጠጣለች።ማንበብ ይቀጥሉ…
ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ግንባታ
“ለአዳም፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በጊዜ ውስጥ አይደለም የተፈጠሩት። ከጊዜ ጋር አብረው ነው የተፈጠሩት” የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ስነ ጽሁፍ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ የጸጋዬ ገብረመድህንና የአዳም ረታን ስራዎች ዋቢ በማድረግ ስለ ብሔርተኝነትና ሀገር ግንባታማንበብ ይቀጥሉ…