ስንቴ ገረዝኩት (ክፍል ሦስት)

እግሬና ሀሳቤ ሳይስማሙ እግሬ ቀድሞ ሬስቶራንቱ ውስጥ ተገኘ። ሲሳይ ቀድሞኝ ተገኝቷል። ልጨብጠው የዘረጋሁትን እጄን ሳብ አድርጎ አቀፈኝ። የምቀመጥበትን ወንበር ሳበልኝ። እራትና ወይን አዘዝን። ከእርሱ ጋር መጨቃጨቁ ትርፉ የሌላ ሰው ትኩረት ከመሳብ ያለፈ ስለማይሆን ዝም ብዬ የሚያደርገውን ከማየት ውጪ ተቃውሞም መስማማትምማንበብ ይቀጥሉ…

ስንቴ ገረዝኩት (ክፍል ሁለት)

“ዶክተር? ያው ሰውዬ ነው የላከልሽ………” ሲስተር ቀለም በፈገግታ በደመቀ ፊት ጠረጴዛዬ ላይ በፎይል የተጠቀለለውን ምሳ አስቀምጣው ወደ በሩ ተመለሰች “ሲስተር ከዛሬ በኋላ የሚያመጣውን ምሳ እንዳትቀበሉት።” አልኳት ለሁለተኛ ጊዜ ታክሞ ከሄደ ጀምሮ ሶስት ቀኑ ነው። የምሳ ሰዓት እየጠበቀ ምሳ ይልካል። ጠዋትማንበብ ይቀጥሉ…

ስንቴ ገረዝኩት?

“አንቺማ አትገርዢኝም። በስመአብ! ” አለ እያማተበ ለመቀመጥም ለመነሳትም በቀረበ አኳኋን አየሩ ላይ ተንጠልጥሎ። “አየር ላይ ነህ፣ አረፍ ትል?” አልኩት አኳኋኑ ሳቄን እያመጣው “የታለ ዶክተሩ ከምር? ” አለኝ ወንበሩ ላይ ተስተካክሎ እየተቀመጠ “እኔ ነኝ!!” አልኩት ምን እንደሚያስብ ለመገመት እየሞከርኩ ካርዱ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ

የሚከተለው ግጥም በሚታየው ታሪካዊ ፎቶግራፍ ንሸጣ የተፃፈ ነው፤ በፎቶው ላይ ሻምበል አበበ ቢቂላ የልምምድ ሩጫ ሲሮጥ ይታያል፤ ከሁዋላው አህያ እየነዳ የሚያልፍ አላፊ ጠፊ ገበሬ አለ፤ ግጥሙን የጣፍኩት ለዚህ አህያ ነጂ ገበሬ ነው፤ ) ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ ባሮጌው ጎዳና፤ በጮርቃውማንበብ ይቀጥሉ…

የመውሊድ ትዝታዎቼ

የመውሊድ በዓልን እያከበርነው ነው። በዚህ ጽሑፌ ስለበዓሉ አከባበር የማወጋችሁ ነገር የለም። ከዚያ ይልቅ ያኔ በልጅ ወኔአችን ከሰራናቸው “አድቬንቸሮች” አንዳንዶቹን አጋራችኋለሁ። ***** በህዳር ወር 1980 ነው። በወቅቱ እኔ (አፈንዲ)፣ መሐመድ አብደላ (ማመኔ)፣ ጆሀር ሀጂ ዩሱፍ (ጀዌ)፣ አድናን ዑመሬ (አግሽ)፣ እና አሕመዶማንበብ ይቀጥሉ…

ባዩ ቀብሩም ገሰሲ አለቁም!

‹‹ አብርሃም ›› ‹‹አቤት አባባ ›› አልኳቸው አከራየ ሻለቃ በላቸው ነበሩ በር ላይ ቁመው የጠሩኝ ‹‹ እየውልህ . . . ይሄ የሸምሱ ሱቅ ጋር መታጠፊያው ታውቀው የለም ? ›› አሉኝ በከዘራቸው ወደሸምሱ ሱቅ አየጠቆሙ ‹‹አዎ ወደ ኢንተርኔት ቤቱ መታጠፊያ አይደልማንበብ ይቀጥሉ…

ወደ እሷው ጉዞ

“ስሟ ግን ማነው?” አልኩት አቡሽን “እብድ ደግሞ ስም አለው? አንተ ልጅ ዛሬ ምን ሆነሃል? ልታብድ ነው እንዴ?” መለሰልኝ። ላብድ መሆኔን እኔም ጠርጥሪያለሁ። ማታ ሰክሬ ነው ብዬ ያባበልኩት ቅዠቴ አድሮ ከህሊናዬ ካልጠፋ ለማበድ እየተቃረብኩ መሆን አለበት።ባለፈ ለሊት ሰማይ ተቀዶ በሚወርደው ዶፍማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

(የሚያስተክዝ ወግ) ከየረር በር እስከ ቦሌ የሚሄድ ምኒባስ የመሳፈር እድል ያልገጠመው ሰው ስለ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ልተንትን ቢል ማን ይሰማዋል? እና ትናንት የተሳፈርኩበት ምኒባስ ካፍ እስከ ሰደፍ ሞልቶ ነበር፤ የምኒባሱ ነባር ወንበር የተሳፋሪውን ብዛት ባገናዘበ መልኩ ሽግሽግ ተደርግጎበታል፤ ወደ ሁዋለኛውማንበብ ይቀጥሉ…

አንዳንድ አሟሟቶች

ሀበሻ አሟሟቴን አሳምረው ይላል። አሟሟት ትልቅ የክብር ሞት ላይ የተንጠለጠለች አላቂ እቃ ነች። የሚደነቅ አሟሟት እንዳለ ሁሉ ግራ የሆነ አሟሟት አለ። ላልቃሽ ቤተሰብ የሚቸግር የሚመስል። ከሞተ የገዘፈ የሚመስል ሰውን ሞት ተኩነስንሶ እና ተልከስክሶ አንሸራቶ ይጥለዋል። ከሞቱ አሟሟቱ አስብሎ ያሳዝናል። ጊዜውማንበብ ይቀጥሉ…

ቂም የሸፈነው እውነት (ክፍል ሁለት)

“እሙዬ ነይ እስኪ……” “ምን ፈለግክ?” “አንቺን” “ሸርሙጣ አይደለሁም።” “ታዲያ እዚህ ምን ይገትርሻል?” “ቤቴ ነዋ…..” ብዬ የላስቲክ ቤቴን በእጄ ጠቆምኩት። “ስንት ዓመትሽ ነው?” “አስራ አራት” ከመኪናው ወርዶ እየተንገዳገደ ተጠጋኝ። “300 ብር እሰጥሻለሁ።” “ሸርሙጣ አይደለሁም አልኩህ እኮ……” “ሸርሙጣ ነሽ ማን አለሽ? ጎዳናማንበብ ይቀጥሉ…