“ቤንዚን አይወጣበት-ነዳጅ አይቀዳበት-ነቲንግ!”

/እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በላይ ለሆኑ ብቻ/ ከጥቂት ጊዜ በፊት በዘመኑ የኣራዶች መስፈርት <ደረጃ 1> የሆነች አንድ ሞዴል ቺክ ጋር <ዴት> አደርግ ነበር…እንደዋዛ ተዋውቀን እንደዋዛ መገናኘቱን ደጋገምነውና ብዙም ሳንቆይ እንደዋዛ አልጋ ላይ ተገኘን…መቼስ በጊዜኣችን ፍቅሩም ፀቡም ስኬቱም ውደቀቱም እንደ መቶማንበብ ይቀጥሉ…

“አንቱ አጤ ሚኒሊክ ምን ያሉት ሰው ነዎት ?… “

የዛሬ አመት በዚህ ወቅት ነው …..አዳራሹ ካፍ እስከገደፉ ግጥም ብሎ በተሰብሳቢወች ተሞልቷል ! የኢሃዴግ ወጣቶች ሊግ ..የሴቶች ሊግ …ጥቃቅንና አነስተኛ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ የቀረ የለም ! ለዩኒቨርስቲ ተማሪወች ከሚሰጠው ስልጠና ጎን ለጎን የአገሪቱን ‹‹ነባራዊ ሁኔታ›› ለነዋሪውም ለማስገንዘብ የተዘጋጀ የሶስትማንበብ ይቀጥሉ…

አይ ቅዳሜ!

በማርና በወተት እንደ ጨዋ ያሳደጉኝ ወላጆቼ…ቢሉኝ ቢሉኝ አልሰማ ያልኩበትን የዚህ እድሜዬን <የግሮሰሪ አመል> አሜን ብለው ከተቀበሉ እነሆ ጥቂት ሰነባበቱ…ከሰፈራችን አንደበተ ርቱዕ ቄስ ባባቴ በኩል እስከምዛመደው ስመጥር የከተማችን መሃዲንስ ድረስ በብዙዎች ተመከርኩ…እኔ እቴ!…MD!…/መስሚያዬ ድፍን!/…እንዴት ችዬ በመለኪያ ልጨክን?…<ከሷ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት>ማንበብ ይቀጥሉ…

ቀሳፊ ምርቃት

ሰማሁ ምርቃትሽን …. ከእናት አንጀትሽ ቁልቁል ሲዥጎደጎድ ታየኝ ምድረ መልዓክ … ብራና ዘርግቶ ቃልሽን ሊከትብ ትከሻሽ ላይ ሲያረግድ በረካሁንልኝ …ከፍ ያርግህ በሰው ፊት … እድሜ ጥምቡን ይጣል ይቅና ማቱሳላ እርጅና እጁ ይዛል አካላትህ ይስላ ዝም ! እግርህን እንቅፋት ጎንህን ጋሬጣማንበብ ይቀጥሉ…

ኑሮ እና ብልሃቱ

የዘጠኝ አመቷን የጓደኛዬን ልጅ የአማርኛ ምሳሌያዊ ንግግር ላስተምር እየታተርኩ ነው። ሶስተኛው ላይ ነን። መፅሃፉ ላይ በተርታ ካሉት ውስጥ ለሷ የሚመጥነውን መርጬ አንብቢ አልኳት። ‹‹ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም›› ጮክ ብላ አነበበች። ‹‹ጎበዝ! ምን ማለት ይመስልሻል?›› ‹‹እ….እ….›› አለች እያንጋጠጠች። ‹‹ቀስ ብለሽማንበብ ይቀጥሉ…

ቅርንጫፉ እንደ ዛፉ

የጋምቤላ ክልል የትምህርት ቢሮን ጨምሮ ዘጠኝ የክልሉ ‹‹ስራ አስፈፃሚዎች›› በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሰበብ ተከስሰው መባረራቸውን ሰማን። በእውነቱ፤ በዚህ ዜና የሚገባውን ያህል ልደነግጥ ባለመቻሌ አዝኛለሁ። በስንቱ ልደንግጥ…? በተለይ በትምህርት ጉዳይ መደንገጥ ያቆምኩት፤ በዛ ዘሞን መንግስት እድሜ ጠገቡን ትምህርት ቤት ‹‹ለልማት›› ማፍረሱንማንበብ ይቀጥሉ…

ሸምበቆ እና ሸንኮሬ

አመት ከማይሞላው ጊዜ በፊት ለመስክ ስራ ወጣ ስል እግረ መንገዴን ‹‹የአባቴን ሀገር እና ዘመዶች ልይ›› ብዬ ከተወለደበት የገጠር መንደር ጎራ ብዬ ነበር። በቅጡ ያልወጠንኩት የእግረ መንገድ ጉዞዬ ወሬ አባቴ ዘመዶች ዘንድ ከብርሃን ፈጥኖ ደረሰና እኔን ለማስተናገድ ወጥነው ሲንገላቱብኝ ሰነበቱ። በተለይማንበብ ይቀጥሉ…

ገነት ይቅርብኝ

“እንለያይ?” ስላት አስቀድማ ውብ ከንፈሮቿን ገለጥ አድርጋ የሲኦል መቀመቅ ውስጥ ሰምጬ እንኳን ቢሆን ንዳዱን የሚያዘነጋኝን ጥርሶቿን አሳየችኝ። ቀጥሎ ግን የእውነቴን መሆኑን ስታውቅ ሳሳዝናት ደፍሬ ማየት የሚከብደኝ ውብ ዓይኗ ደፈራረሰ። “ማለት?” አለችኝ በተሰበረ እና የአፏን በር ለቆ ለመውጣት በሚቅለሰለስ ድምፅ “እንድንለያይማንበብ ይቀጥሉ…

የኢሬሳ/ኢሬቻ በዓል ትውፊትና አከባበር

የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አንድ ጽሑፍ እናበረክታለን ባልነው መሰረት ይህንን ኢትኖግራፊ ቀመስ ወግ ጀባ ልንላችሁ ነው። ታዲያ እኛ ባደግንበት አካባቢ በሚነገረው ትውፊት በዓሉ “ኢሬሳ” እየተባለ ስለሚጠራ በዚህ ጽሑፍ ውስጥም “ኢሬሳ” የሚለውን ስም መጠቀሙን መርጠናል። ወደ ነገራችን ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ የሚወሱትማንበብ ይቀጥሉ…

የመታወቂያው ጉዳይ (አራተኛው ሙከራ)

“ሚስተር ኤክስን ያያችሁ” መታወቂያዬ ላይ በግድ የተፃፈብኝን የብሔር ማንነት ዜግነት ኢትዮጵያዊ ለማስባል ጥረት ያደረግኩበትን የባለፈውን ሳምንት የሦስተኛ ቀን ሙከራዬን ትረካ ያበቃሁት ከክፍለ ከተማው (በዘልማድ እንደሚባለው አውራጃ) ፍርድ ቤት ወደ ፌደራል ፍርድ ቤት ጉዳዬን እንዳቀርብ መላኬን ገልጬ ነበር። የዛሬውን ሙከራዬን እነሆ፡-ማንበብ ይቀጥሉ…