ከያንዳንዱ የከሸፈ አብዮት ጀርባ

እዚህ ጓዳዬ ውስጥ የከሸፈ አብዮት አለ! የጓዳዬን አብዮት ለማክሸፍ፣ አድማ በታኝ አልተላከም! አስለቃሽ ጭስ አልተጣለም! ጥይት አልተተኮሰም! ከክሽፈቱ ጀርባ አንድ ነገር ብቻ ነበር፤ ሚስቴ!! አብዮት እባላለሁ። ወጣት ነኝ፤ አብዮት ውስጤ የሚፈላ ወጣት! “ተነሳ፣ ተራመድ ” በምልበት እድሜ፣ “ተኛ፣ ተቀመጥ ”ማንበብ ይቀጥሉ…

የቤተሰባችን ፎቶ

….አቤት የቤተሰብ ፎቶዋችን ማማሩ! የጥርሳችንንጣቱ! የሳቃችንድምቀቱ! አባዬ እበርበት ይመስል እኔን ጥብቅ አድርጎ አቅፏል፡፡ እማዬ ይበርባት ይመስል ናሆምን ጥብቅ አድርጋ አቅፋለች፡፡ እኔ እና ናሆም ያለን ጥርስ ሁሉ እስኪታይ ስቀን ከእናትና አባታችን ስር እንደጉልቻ ቁጭ ቁጭ ብለናል፡፡ የሚያስቀና አራት ጉልቻ፡፡ እዩት የእማዬንማንበብ ይቀጥሉ…

ስለችጋር

ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ ‹‹እየበሉ›› በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ ችጋር የሚያጠቃው ማንንማንበብ ይቀጥሉ…

“ገጽታ ግንባታ?”

ባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…

ገፅታ ሳይኖር፣ ለገፅታ መጨነቅ ውጤት የለውም!

“በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው ችጋር መጀመሪያ ነው፤ በመስከረምና በጥቅምት የዝናብ ወቅቱን ተከትሎ የሚመጣ ችጋር ገና መንገድ ላይ ነው፤ በአብዛኛዎቹ ገበሬዎች ላይ የሚደርሰው በመጋቢትና በሚያዝያ ነው፤ በድንቁርና ንግግርና በመመጻደቅ አይቆምም፤ አሁን የተከሰተውን ምልክት ለመቀበልና ዋናውን ችጋር ለመከላከል የሚያስፈልገውን እርምጃ በጊዜው መውሰድ ካልተቻለማንበብ ይቀጥሉ…

“ከጥላቻ ማህፀን የሚወለድ ሰላም የለም”

Bertrand Russell በ ‘The Proposed Road to Freedom’ ፣ የማርክስን “የኮሚኒስት ማኒፌስቶ” ሃሳብ (የዓለም ሰራተኞች ተባበሩ የሚለውን) ሲተች የሚከተለውን ይላል… ‘ There is no Alchemy by which a universal harmony can be produced out of hatred’ በአጭሩ…ከጥላቻ የሚገነባ ሁሉ ዓቀፋዊማንበብ ይቀጥሉ…

ኩልና ተኮላ

ተኮላ የተባለ ሰው አፍቅሬ በትዳር መኖር ከጀመርኩ አሁን ሰማንያ ሰባት ነው አይደል? አዎ አንድ አመት ተኩል አለፈኝ፡፡ በዚህ …. ማለት በቃ ከእሱ ጋር አንድ ቤት ውስጥ ሚስቱ ሆኜ በመኖሬ ደስተኛ ነኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በማያገባቸው መግባት የሚወዱ ወይም የማናቀፍ ጉጉታቸው ወሰንማንበብ ይቀጥሉ…

ሃሳብ የደንብ ልብስ አይደለም፤ ሲመሳሰል አያምርም

በሃይለስላሴ ዘመን፣ “የሃይለስ ስላሴ የሽልማት ድርጅት ” የሚባለው ተቋም፣ ከሸለማቸው ሰዎች አንዱ አኩራፊው ከበደ ሚካኤል ነበሩ። ጊዜው በ1957 ዓም ሲሆን፣ የሽልማቱ መጠን ደግሞ 7ሺ ብር፣ የወርቅ ኒሻንና ዲፕሎማን ነበር። ታዲያ ከቤ እንደሌላው ሰው ሽልማቱን በአደባባይ ለመውሰድ፣ አሻፈረኝ ብለው ቀሩ። የእምቢታቸውማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹አላውቅም›› ማለት ነውር የሆነበት አገር እየገነባን ነው ?

አገራችን ላይ ትልቁ ችግር የሚመስለኝ ….ታላላቆች በሁሉም ነገር ትልቅ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብና ‹ታናናሾች › በሁሉም ነገር ትንሽ እንደሆኑ አድርጎ ማናናቅ ነው …ለምሳሌ ሰፈራችን ውስጥ ያለን ታዋቂ አርቲስት …ህግም ፣ፍልስፍናም፣ መሃንዲስነትም ፣ የተበላሸ ቧንቧ ጥገናም ፣ ፖለቲካም ፣ስፖርትም ከሱ በላይ አዋቂማንበብ ይቀጥሉ…

ሄሊ እና የመንዝ ወርቅ

በዚያ ሰሞን ለአጭር ጊዜ ስራ የተቀጠርኩበት አንድ ቢሮ ፈረንጅ አለቃዬን ልተዋወቃት ቢሮዋ ሄድኩ፡፡ ‹‹ኦው!አዲሷ ኮንሰልታንት! ማነው ስምሽ?›› አለችኝ አየት አድርጋኝ፡፡ ‹‹ሕይወት እምሻው›› እኔን ሳይሆን የምታገላብጠውን የወረቀት ክምር አያየች ‹‹ኦህ…አጠር አድርጊውና ንገሪኝ ›› አለችኝ ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ‹‹ይቅርታ ምን አልሽኝ?›› አልኳትማንበብ ይቀጥሉ…