መቶ ብር ከየት ወዴት?

ትናንት ኣመሻሽ ላይ፤ ከYohanes Molla ጋር ተቀጣጥረን ተገናኘን ፡፡ካልዲስ ገብተን እኔ ኣንድ ፍንጃል ቡና ሳዝዝ ፤ ዮሀንስ ሲያቀብጠው ኣንድ ቡና እና የባራክ ኦባማን ጆሮ የሚያህል ቦምቦሊኖ ኣዘዘ፡፡ በመጨረሻ ኣስተናጋጂቱ የእዳችንን ደረሰኝ ኣምጥታ ጠረጴዛው መሀል ላይ ኣኖረችው ፡፡እሱ እኔ እስክከፍል ሲጠብቅማንበብ ይቀጥሉ…

”በሥጋና በግብረስጋ ቀልድ የለም”

ዜና እናሰማለን፤ ዜናውን ከማሰማታችን በፊት ኣካባቢውን በስጋት ዞር ዞር ብለን እናያለን! ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሚያደርጉት ጉብኝት ጥንቃቄ ሲባል የቦሌና ያካባቢው ነዋሪዎች ሽሮሜዳ እንዲሰፍሩ ተደረገ፡፡ President Barak Obama, welcome to the land of fair and free erection! ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሸገርማንበብ ይቀጥሉ…

የዋለልኝ መኰንን አጭር የትግል ታሪክ

ዋለልኝ መኰንን በድሮው አጠራር በወሎ ጠቅላይ ግዛት በደብረሲና ወረዳ ከአባቱ ከአቶ መኰንን ካሣና ከእናቱ ከወይዘሮ ዘነበች ግዛው መጋቢት 11 ቀን 1938 ዓመተ ምህረት ተወለደ። ዋለልኝ መኰንንም በደሴ ከተማ በሚገኘው የንጉሥ ሚካኤል ተምህርት ቤት አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ከዚህም በመቀጠልማንበብ ይቀጥሉ…

ግርግር – አንድ

አውላቸው እባላለሁ … ተወልጀ ያደኩት እዚሁ ሰፈር ነው (ሌላ ምን መሄጃ አለኝ) ሰዎች ታሪክህን ንገረን ይሉኛል … ለማንም ታሪኬን ተናግሬ አላውቅም … እኔ,ኮ የሚገርመኝ እስቲ አሁን ማን ይሙት ይሄ ህዝብ ታሪክ ብርቅ ሁኖበት ነው የኔን ታሪክ ለመስማት የሚጓጓው ? …ማንበብ ይቀጥሉ…

ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህጻን

በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶችማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ስንኞች

ከጥቂት ኣመታት በፊት የሆኑ ሸበቶ ሽማግሌ እኔንና ኣብሮኣደጌን ኣንተነህ ይግዛውን ኣፈላልገው ኣገኙንና ለጠቅላይ ሚኒስተር መለስ የሚላክ ኣቤቱታ እንድንጽፍላቸው ማለዱን፡፡የሆነ ጉልቤ በድሏቸዋል፡፡ምሬት ኣባርሮት ወደዚህ ገጽ የመጣውን ኣንባቢ ተጨማሪ ምሬት ላለማካፈል የሰውየውን በደል ኣልጽፈውም፡፡ ተገናኝተን ስንጨዋወት ስለግጥም ተነሳና ኣንድ ግጥም በቃሌ እንድወጣላቸውማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ እኔ እና የመጀመሪያው ፍቅሬ

(ክፍል አንድ) ‹‹እጅ ወደ ላይ!›› ሎጋ ቁመናው ተስተካክሎ፣ ፍቅሩ የሚስብ አይኑ አባብሎ፣ …ላፈጣጠሩ እንከን የለው፣ አረ እንዴት አርጎ ነው የሰራው አረ እንዴት አርጎ ነው የሰራው›› ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከአሰልቺ የጎበዝ ተማሪነት ቀናት በአንዱ…. ለስምንት ሰአት ሃያ ጉዳይ ገደማ ከዶርም ወጥቼማንበብ ይቀጥሉ…

ሸሌ ነኝ

‹‹ነይ እዚህ ጋር ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ…ብርድልብሱ ላይ ተኚ›› ሲለኝ፤ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር፡፡ ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ጊዜ መሽኮርመም፡፡ ሰው እንጂ ሴት ያልሆንኩ መስሎኝ፡፡ ስጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ፡፡ ገንዘብ ተቀብዬ ደስታን ልሰጥ ያልመጣሁ መስሎኝ፡፡ አንገቴን እንደሰበርኩ ወደማንበብ ይቀጥሉ…

ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና

ልጁ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡ ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣ ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ባፍሪካ የመጀመርያው የሳቅ ትምርት ቤት››

ባለፈው፣በቤተ-መንግስት መውጫ፣ በሸራተን መውረጃ መንገድ ላይ የተሰቀለ ፖስተር አየሁ፡፡ ‹‹ባፍሪካ የመጀመርያው የሳቅ ትምርት ቤት››ይላል፡፡የዘመኑን መንፈስ ከሚያሳዩ ተቋሞች ዋናው መሆን አለበት ብየ አሰብኩ፡፡በዘመኑ ዝም ብሎ መሳቅ ከባድ ነው፡፡እንድያውም በዘመኑ ከልቡ የሚስቅ ሰው ከተገኘ እንደ ስድስት ኪሎ አንበሳ በቅጽር ከልለን ልንጎበኘውና ልናስጎበኘውማንበብ ይቀጥሉ…