ስሚ መስሚያ ካለሽ። ከሰማሽ ደሞ ተስማሚ፤ ወዲያ ሂጂልኝ እስቲ። ማነሽ እውነት ነኝ የምትይ፣ እስቲ ስሚን የስንቱን አለመስማት እንችላለን? መንግስት አይሰማን፣ ፈጣሪ አይሰማን፣ አንቺ አትሰሚን… ኸረ እስቲ አንቺ እንኳን?!! ማን ነበረ ስምሽ? “እውነት ” ነው አይደል? እውነቱን ልንገርሽ፣ በደረስኩበት ባትደርሺ ደስማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱ ካድሬዎቹ
ሁለቱ ካድሬዎች የማነ እና ዳንኤል ካድሬዎች ናቸው። ይሁኑዋ ታዲያ! ካድሬ በበዛበትሀገር እነገሌ ካድሬ ናቸው ማለት ምንድነው? የማነ እና ዳንኤል ጓደኛሞችም ናቸው፤ ውሏቸው አንድ ላይ ነው፣ ወሬያቸውም አንድ ዓይነት። ስለ ልማቱ ያወራሉ፣ ያደጉትም፣ ያላደጉትም ፣የማያድጉትም ከኢትዮጵያ መውሰድ ሰላለባቸው ተሞክሮ ያወራሉ፣ አዲስማንበብ ይቀጥሉ…
የዚህ ትውልድ አባል ነኝ!
በመውደድ ወይ በመጥላት አልፍቀውም። ያለፈው ትውልድ ውላጅ ነኝ። የመጪው ትውልድ ወላጅ ነኝ። ያለፈው ትውልድ “አዬ ልጅ” እያለ ያሾፍብኛል፤ መጪው ትውልድ ይኮርጅኛል( ወደፊት “አይ አባት” ብሎ ይስቅብኝ ይሆናል -ግድ አይሰጠኝም) ለሁሉ ፈጣን ነኝ። ሁሉን በፍጥነት አይቼ በፍጥነት አልፋለሁ። ችክ ማለት አልወድም።ማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት እህትማማቾች ወግ
የዛሬ ወር ተኩል ገደማ ለሳምንታት ቆይታ ወደ አሜሪካ ሄጄ ነበር፡፡ የጉዞ ሃሳቤን የሰሙ እዚህም አዚያም ያሉ ዘመድና ወዳጆቼ እኔ ‹‹ልዋጭ ልዋጭ›› የምለውን የእቃ ውሰጂና አምጪልን ጥያቄያቸውን ጀመሩ፡፡ በርበሬና ሽሮን በጋላክሲ ስልክና በሌቫይስ ጅንስ የመለወጥ ጥያቄ፡፡ ቡላና ኮሰረትን በናይኪ ስኒከርና በሬይባንማንበብ ይቀጥሉ…
በመጨረሻም…
በመጨረሻም ራሴን ላጠፋ ነው። ቃሉ ራሱ ደስ ሲል! ራስን ማጥፋት!! ፓለቲከኞች “የራስን ዕድል በራስ መወሰን ” እንደሚሉት ነው። ከህይወት ምን ቀረኝ? ምንም! አንድ የቀረኝ ነገር ራሴን የማጥፋት ድርጊት ብቻ ነው። ከዛ በኋላ ሀገሬ ሞት ነው። ከሞት ግድግዳ ወዲህ ምንም የሚጎትተኝማንበብ ይቀጥሉ…
የተደገሙ ወላጆች!
(ልጆቻችሁ፣ ልጆቻችሁ አይደሉም?) ካህሊል ጅብራን “The Prophet” በተባለ ስራው “ስለ ልጆች ንገረን” ለሚል ጥያቄ በነብዩ አንደበት ይናገራል። “your children are not your children” ምን? ልጆቻችሁ ልጆቻችሁ አይደሉም? እና የኛ ካልሆኑ የማን ናቸው? ነው ወላጆቻችን ናቸው? አትቀልዳ ካህሊል። እስቲ ትንሽ አብራራው።ማንበብ ይቀጥሉ…
ፈሪ ነኝ!
ፈሪ ነኝ! ሞዴል ፈርቶ አደር! ውሃ ውስጥ ሆኜ የሚያልበኝ። በርግጥ ውሃው “ፍል ውሃ” ከሆነ ማንም ሊያልበው ይችላል። እኔ ግን አጥንት በሚቆረጥም ውሃ ውስጥም ያልበኛል። መፅሀፉ፣ “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” ይላል። እኔ ግን “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ፣ መጨረሻውም ሁሉንም መፍራትማንበብ ይቀጥሉ…
ሆድ ሀበሻዊ ንጉስ…
የኛ ሰው ሆዱን በጣም በመውደዱ የሚወደውን ሰው እንክዋ ሲያቆላምጥ “ሆዴ” ብሎ ነው:: ግፋ ካለ “ማሬ” ቢል ነው:: ማርም የሚበላ ነው; ሆድም ምግብ ከታች ነው:: ምሳሌዎቹ እራሱ በሆድ ዙሪያ ድክ ድክ የሚሉ ናቸው:: -የወፍ ወንዱን የሰው ሆዱን አያውቁም! -ሆድ ያባውን ብቅልማንበብ ይቀጥሉ…
ድርብርብ ስቅላት
የመሲሁ ስቅየት ግርፊያ ስቅላቱ አምላክ ነኝ ስላለ በድምቀት ተሳለ የኛንስ ስቅላት ማነው ያስተዋለ? ተመልካች ጠፍቶ እንጂ ዐይን የሚለግሰን መውረድ እንደናፈቅን እኛም መስቀል ላይ ነን:: ዘውትር ዱላ እና አሳር ዘውትር ችንካር ሚስማር የሚገዘግዘን የሚጠዘጥዘን እኛም ክርስቶስ ነን እኔም ታዝቤያለሁ… ሺ ዱላማንበብ ይቀጥሉ…
ወጣትነቴን ያያችሁ
አላያችሁም አውቃለሁ! መጠየቅ፣ ልማድ ሆኖብኝ፣ ቁጭቴ ብሶት ጭኖብኝ የሄደች ወጣትነቴን፣ ያያችሁ…ያያችሁ እያልኩ፣ ባታዩም እጠይቃለሁ፡፡ * * * * ያያችሁ ወጣትነቴን? አፍለኛ፣ ማራኪ ወቅቴን? በጫት ጉዝጓዝ አፍኜ፣ ከፍኜ የገደልኳትን በማይገባኝ የፈረንጅ አፍ፣ አደንቁሬ የጣልኳትን ወጣትነቴን ያያችሁ፣ ሳልጨብጥ ያበረርኳትን፡፡ * * *ማንበብ ይቀጥሉ…